November 7, 2017 06:16

መቼም ሰሞኑን የዶላር፥ ጫትና ቡና ኮንተሮባንድ ዜና ከተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች እየተሰማ ነው፡፡ ከትላንት ወዲያ (26/02/08 ዓ.ም) ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት መኪና (ታርጋ ቁጥር ET64594) 54 ሰዎችን ጭኖ #ከጅማ_ወደ_አዲስ_አበባ እየተጏዘ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ መኪናው ወደ ጅማ ሲሄድ በርቀት አይቼው ነበር፡፡ ለየት ያለች ብራንድ ነገር ስለሆነች በቀላሉ ትለያለች፡፡ በወሊሶ ወረዳ ፖሊሶች ጉሩራ አከባቢ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ፍተሻ ሲደረግበት በጎንና ጎን ኪሶቹ 11ኩንታል #ቡና አጭቆ ይዟል፡፡ መኪናው ኮንትሮባንድ መጫኑ ሳያንስ #ሹፌሩ ራሱ መንጃ ፍቃድ የለውም፡፡

እና እላችኋለሁ፣ #Falcon_Coach የተባለችው መኪና ከቡናና ሹፌሯ ጋራ በወሊሶ ወረዳ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውላ ጉዳይዋ እየተጣራ ነው፡፡ እንደው ግን ሰሞኑን የኮንትሮባንድ ዜና በየቦታው ለምን የበዛ ይመስላችኋል? እኔ ልንገራችሁ፡፡ በእርግጥ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የዶላር፥ ጫትና ቡና ኮንትሮባንድ በየቦታው እየተያዘ ስለሆነ #በጣም_ቀንሷል፡፡ ለብዙዎቻችን ኮንትሮባንዱ ጭራሽ የተባባሰ፥ የጨመረ የሚመስለን የኦሮሚያ ፖሊሶችና #ቄሮዎች ኮንትሮባንዲስቶችን እየያዙ ለህዝብ እያጋለጧቸው ስለሆነ ነው፡፡ የኮንትሮባንዱ ንግድ ግን ላለፉት 25 አመታት ከዚህ በባሰ ሁኔታ ሲካሄድ ነበረ፡፡ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በየአቅጣጫው እየተያዙ ስለሆነ የኮንትሮባንዱ ንግድ በጣም ቀንሷል፡፡ ስለዚህ አሁን እየተያዙ ያሉት ኮንትሮባንዲስቶች በጣም የጠረረባቸውና በኪራይ ሰብሳቢነት የናወዙት ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት፣ ባለፉት አመታት በኦሮሚያ ሲካሄድ የነበረው የኮንትሮባንድ ንግድ ከአሁኑ በጣም የሚበልጥ እንደነበረ፣ አሁንም በሌሎች ክልሎች እየተካሄደ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ “ካልተያዙ በስተቀር #ሌብነት ሥራ ነው!” በሚል መርህ ለሚመራ የፖለቲካ ቡድን ኮንትሮባንድ መደበኛ ሥራው ነው፡፡ ብርቅ የሆነብን ይህን መረዳት የተሳነንና ጉዳችንን በቅርቡ የሰማን ነን፡፡