መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌአልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን በለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል።  በግል ጸብ ለሁለት መሰንጠቃቸው የአደባባይ ምስጢር ይሁን እንጂ፤ እርቅ እና ሰላም በአጀንዳቸው ውስጥ አልተካተተም። ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ወደጎን ትተው፣ “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” ሲባባሉ እንደከረሙ ነው እየተሰማ ያለው። ይህንንየማይታረቅ ቅራኔ ይዘው አብረው ስለማይዘልቁ የአንዱ ቡድን ማሸነፍ ግድ ይላል።

 በዚህ ‘ታሪካዊ’ ስብሰባ የሙስና እና የሌብነት ፋይሎች ተጠርዘው ቀርበዋል። ህወሃቶች አፍ አውጥተው “በስብሰናል“ም ብለዋል። እንደ አጀንዳ በቀረቡ በነዚህ የክስ ፋይሎች ላይ ድምጽ ተሰጥቶባቸው። ስብሰባውን እየረገጡ የወጡት ወንጀልሲዶለትባቸው የነበሩትት “ተሸናፊ” ህወሃቶች ነቸው። በሃብታቸው ብዛት “ቀዳማዊነቷ መቤት” የተባሉት አዜብ መስፍን የመጀመርያው ስብሰባ ረጋጭ መሆናቸውን ሆርን አፋየርስ ከውስጥ ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል። አዜብ ተከትለው ስብሰባውን እየረገጡ የወጡት የነ ስዬ አብርሃን ጽዋ ይቅመሱ አይቅመሱ ገና ባይታወቅም፣ ዛቻውና ጥርስ መናከሱ መቀጠሉን ግን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል።

 ወሩን ሙሉ መቀሌ ላይ ከትመው ሲጠዛጠዙ ውለው ሲጠዛጠዙ መሰንበታቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል። ግምገማው ቀድሞ እንደሚያደርጉት አንዱ ባንዱ ላይ ጣት መሰባበቅን አልፎ፣ በተራ ስድብ እና ዘለፋ የታጀበ ነው። አጀንዳቸውብሄራዊ ጉዳይ ቢሆን ባልከፋ ነበር። እጅግ የሚያሳፍረው ጸቡ እኔ እበልጥ፣ የግል መሆኑ ነው። ሌቦች የሚጋጩት ሲሰርቁ ሳይሆን ሲካፈሉ ነው ይባል የለ።

 አቶ ሀብቶም ገ/እግዚያብሄር የህወሃቱ ድረገጽ በሆነው አይጋ ፎረም ላይ ኢህአዴግ ያለበት መንታ መንገድ እና የሀገራችን እጣ ፈንታ! በሚል የለቀቁት ያልተለመደ ጽሁፍ ከወዲያ እየነደደ ያለውን እሳት ይጠቁመናል። አይቴ ሃብቶም ስለዛሬውመግማማትና የሌቦች ፖለቲካን ክፉኛ ይኮንናሉ። ዛሬ ብቸኛው የመክበሪያ መንገድ ወይ የመንግስት ስልጣን መያዝ ወይ ከመንግስት ባለስልጣን መጠጋት እሳቤ መሆኑን እና ለዚህም ሙሉ ተጠያቂው ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ነው ይላሉ።

 እርግጥ ነው። በህወሃት ውስጥ ሽኩቻ እና መጠላለፍ አዲስ አይደለም። የከዚህ ቀደሙን ተመክሮ እንዳየነውም፤ ስብሰባ ረግጦ መውጣት ለችግሮቹ መፍትሄ አልሆነም። ከ16 አመት በፊት እነ አቶ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ስዬ አብርሃ፣ ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳኤ የመለስን ሰነድ አንቀበልም ብለው ስብሰባ ረግጠው ነበር። እነ ስዬ በወቅቱ አብዛኛ ድምድ ነበራቸው። ግና ማኬቬሊያዊም መለስ ቀደማቸውና እንደወጡ በዚያው ቀሩ። አሁን መለስ የለም። ጸቡም የውስጥና የርስበርስ ብቻ አይደለም። ሽኩቻው ከሕዝብ ጋርም ነው። ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር። የከረረው ክፍፍል ከህዝብ እንቢተኝነት ጋር ተደምማሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ታምራት ገለቴን መጠየቅአያስፈልግም።

 ፋይዳ ላይኖረው፣ እንዲሁ ሲቀያየሩ መሰንበታቸው “ስልቻ ቀልቀሎ…” ይሁን እንጂ፣ የኑሮው ውድነት፣ ከጣና ኬኛ ፖለቲካ እና የሼኩያልጠጠበቀ መታሰር፣… ተደማምሮ ለውጥ ፈልጎ ለተነሳው ኃይል በር መክፈቱ ግልጽ ነው።