eeet
Pin
ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዴት ለፌዴራል ዳኝነት ተሾመ? እንዴትስ ዳኛ ሊሆን ቻለ? ከቀድሞው ፍትህ ሚኒስቴር (በአሁኑ ወቅት ተቋማችን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሚል የስም ለውጥ አድርጎና የስልጣን ጨምሮ እንደገና ተደራጅቷል) ስራውን እንዴት ለቀቀ? የሚለውን በአጭሩ ከመዳሰሴ በፊት ትግራዋይ የሆኑ ዳኞች እውን በህገ መንግስቱ እንኳን ለይስሙላ የተቀመጠውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የእኩልነት መብት እና የህግ የበላይነትን አምነው የተቀበሉ ናቸውን የሚለው ጉዳይ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅና በተለይም በአሁነ ወቅት መጠነ ሰፊ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የሙስና፣ የሰው ልጆች አካል ( በተለይም የኩላሊት፣ የአይን እና የልብ)ሽያጭ፣ የቼክ ማጭበርበር፣ የኮንትሮባን ንግድ፣ ህገወጥ የገንዝብ ዝውውር፣ ህገወጥ የመሬት ወረራ፣ የግድያ፣ ሴቶችን ለወሲብ ንግድ የማቅረብ ወንጀል፣ የጉምሩክና የታክስ እንዲሁም ሌሎች ሰፋፊ የኢኮኖሚ ወንጀሎችን የሚፈፅሙት የትግራይ ተወላጆች ሆነው ሳለ በግልፅ የሚታወቁ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር በተለይም በፀጋዬ በርሄ የእህት ልጅ በሚመራው ‹‹‹ጉዳይ አምካኝ ቡድን››› አማካይነት ጉዳዮች እንዴት ተድበስብሰው እንደሚቀሩ፤ ለፍርድ የሚቀርቡ ጉዳዮች አንኳ በዚሁ ጉዳይ አምካይ ቡድን ትዕዛዝ አማካይነት በአቃቤ ህግ እንዴት መዝገባቸው እንደሚዘጋ ወይም እንደሚቋረጥ፤ በፍርድ ቤትም የቀረቡ ጉዳዮችም ቢሆን በልዩ ልዩ ዘዴዎች ተከሳሽ ትግራውያን እንዴት ነፃ እንደሚለቀቁ፣ አንዳንዶቹም ከሌሎች እጅግ በተለየ ሁኔታ በጣም ቀላል ቅጣት ተጥሎባቸው እንዴት እንደሚፈቱ፣ በማረሚያ ቤትም የእስራት ቅጣታቸውን እንዲጨርሱ ውሳኔ የተሰጠባው ጥፋተኞችም እንዴት በልዩ ልዩ ዘዴ ከማረሚያ ቤቶች እንደሚዎጡ ዝርዝር ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ ፅሁፍ በዚህ ረገድ የሚሰሩትን ሴራዎችና እንዴት የፌዴራል በተለይም የዳኝነት ስርዓቱ አደጋ ላይ እንደሆነና ህወሃት የፍትህ አካላትን የማፈኛ ማዕከላት አድርጎ እንደሚጠቀም ለመተንተን እሞክራለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ያለምንም የወንጀል ጥፋትና ተሳትፎ የኦሮሞ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዴት ክስ እንደሚቀርብባቸው፣ በተለይም በማዕከላዊ፣ በቂሊንጦ እና በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች የሚደርሱ ሰቆቃዎች ምንነትና ይዘት የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ፅ/ቤት (በነገራችን ላይ ይህ ፅ/ቤት ከሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ሰነድ በፓርላማ ከመውጣት ጋር ተያይዞ የተቋቋመ ፅ/ቤት ሲሆን አሁንም በጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅ/ቤታችን አንድ የስራ ክፍል ሆኖ እየሰራ ሲሆን የኦሮሞ ተወላጅና የኦህዴድ አባል በሆነው አቶ ይበቃል ግዛው አማካይነት እየተመራ ይገኛል) በአንድ ወቅት ካዘጋጀውና ለጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጭምር ከላከው ሪፖርት አንፃር ማለትም በእነዚህ ተከሳሾች የሚደርሰውን አሰቃቂ፣ ሰብዓዊነት የሌለው፣ በተለይም የደም ዶሴ በሚል የልዩ አቃቤ ህግ ፅ/ቤት በአንድ ወቅት በሳተመው መፅሀፍ ውስጥ የተጠቀሱ የማሰቃያ ዜዴዎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ዘዴዎች በኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ላይ በእነዚህ ተቋማት እንዴት እየተፈፀ እንደሆነ ከሚዘረዝረው ርፖርት አንፃር በመተንተን ወደፊት በዝርዝር የማቀርበው ይሆናል፡፡


ዞሮ ዞሮ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዴት ከቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ከአቃቤ ህግነት ስራው ለቀቀ፤ እንዴትስ ለዳኝነት ተመረጠ የሚለው ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡ ዘርዓይ ወልደወንበት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ሲቀላቀል እኔ እና የኔ ባች የሆኑ ባለሙያዎች በተቋሙ አንድ አመት ያህል ካገለገልን በኋላ የተቀላቀለ ባለሙያ ስለነበር ባህሪውንም ሆነ የትምህርት ብቃቱን ለማወቅ ከባድ አልነበረም፡፡ ዘርዓይ ወልደሰንበት በምስራቁ የአገራችን ክፍል ከአዋሽ ማዶ የተገኘሁ ነኝ የሚልና በተለይም የጥርሱ መወየብ (በተለምዶ እጣን ጥርስ አይነት) መሆን ስለሚያሳብቅበት ፈታ ያለ ልጅ እንደሚሆን በማሰብ በማናቸውም ሁኔታ በተለይም የአንድ ተቋም ስራተኞች በመሆናችን (አቃቤ ህግ) ስናገኘው የሞቀ ሰላምታ እና የጓደኝነት መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ እናወራ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ግን በተለይም እነ ዘርዓይ ወልደሰንበት በተቀጠሩበት ዓመት ለሴት ተማሪዎች፣ ለአናሳ ብሔረሰቦችና የድርጅት አባላት እድሚያ ተሰጥቶ የአቃቤ ህግ ምልመላው እንደሚካሄድ ሲታወቅ በተለይም ባምቢስ በሚገኘው የፍትህ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት የሚገኙ ወጣት ባለሙያዎች አቃቤያን ህግ መቀጠር ያለባቸው በሙያ ብቃታቸው፤ በትምህርት ውጤታቸውና ሌሎች ግልፅ በሆኑ መመዘኛ መስፈርቶች እንጂ በዚህ መልክ መሆን የለበትም በሚል በየስብሰባው ጥያቄ ያቀርቡ የነበረ ቢሆነም በምልመላው ሂደት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የኢህአዴግ አባላት የሆኑ ተማሪዎችና በተለይም ትግራዋይ የሆኑ እና ከግል ኮሌጆች የተመረቁ ልጆች ጭምር በቀጥታ የተቀጠሩበት ዓመት ነበር፡፡ ለይስሙላም የአቃቤ ህግ ምልመላ ተካሂዷል ቢባልም ትግራዋይ የሆኑ ልጆች በወቅቱ የአቃቤ ህግ አስተዳደር ጉባኤ ሰብሳቢ በነበረው ትግራዋይ ሃላፊ አማካይነት በቀጥታ ተቋሙን እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከእነዚህ ልጆች መካከል የተወሰኑት ዳኝነት ጭምር ተሾመው የስርዓቱ ማገርና ቋሚ ሆነው እያገለገሉና የታዘዙትን የፍርድ ውሳኔ እየፃፉ ይገኛሉ፡፡ ዘርዓይ ወልደሰንበትም በዚህ ሂደት የተቀጠረ ሲሆን ለተወሰነ ግዜም ቢሆን በመምህርት የሰራ መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡

ዘርዓይ ወልደሰንበት በዚህ ሁኔታ በቆርቆስ ፍትህ ፅ/ቤት ተመድቦ እየሰራ ባለበትና እየቆየ ሲሄድ እውነተኛ ባህሪው እየተገለጠና ቀድሞ እንደሚያደርገው አብረውት የሚሰሩ ባለሙያዎችና ሌሎች የተቋሙ ባለሙያዎች ጋር መልካም ግንኙነት ከማዳበር ይልቅ የትግራዋይ አቃቤያን ህግ የመብት አቀንቃኝ በመሆንና በአብዛኛው ከትግራዋይ አቃቤያን ህግ ጋር ብቻ ግንኙነት በመፍጠር ከሌሎች ብሔር ተወላጆች ጋር በአይነ ቁራኛ መተያየት ደረጃ ደረሰ፡፡

ዘርዓይ ወልደሰንበት በወቅቱ በቄርቆስ ፍትህ ፅ/ቤት ካሉ ባለመያዎች ጋር ቢሆን በልዩ ልዩ የህግ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲካሄድ ያለእኔ ሌሎቻችሁ ህግ የማታውቁ ናችሁ በሚል እብሪት የሌሎችን የህግ ትንተና ባለማዳመጥና አሳማኝ ሀሳቦችን ጭምር ባለመቀበል በተለይም የፍትህ ፅ/ቤቱን ሃላፊን በአቃቤያን ህግ ፊት እንዲሁም በባለጉዳዮች ፊት የማዋረድና የመሳደብ ድርጊት በተደጋጋሚ መፈፀም ጀመረ፤ የሃላፊዎችንም ትዕዛዝ ባለማክበር ያላስፈላጊ ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት ጀመረ፡፡ በዚህም ያለእኔ አዋቂ የለም በሚል እብሪት ጭምር አብረውት ከሚሰሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ጋር የተካረረ ፀብ ውስጥ እስከመግባት ድረስ ደረሰ፡፡ በዚህም መሰረት የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ያገለሉት ሲሆን ኦሮሞዎች እና አማራዎች አላሰራኝ አሉ፤ ተቋሙንም በወቅቱ ይመራ የነበረው ሚኒስቴር አቶ ብርሃን ኃይሉ የሚባል የአማራ ተወላጅ ባለስልጣን ስለነበር ይሄ ነፍጠኛ አማራ ሆነ ብሎ በፅ/ቤቱ ሃላፊ በኩል እያስጠቃኝ ነው፤ ስራየን እንዳልሰራ እየተደረኩ ነው ወደሚል የስም ማጥፋት ድርጊት መግባቱ ተሰማ፡፡ በሌሎች ፍትህ ፅ/ቤት የምንሰራ ባለሙያዎችም በምናገኘው ጊዜ ከሰላምታ ያለፈ ውይይት ማድረጋችንን አቆምን፡፡

በዚህ መኃል የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሰዎች የተከሰሱባቸውን መዘግብትን ለማድበስበስ እና ምክንያት በመፈለግ በወ/ስ/ስ.ህ/ቁጥር 41/1 መሰረት በቂ ማስረጃ የለም በሚል ብዛት ያላቸውን መዛግብት በመዝጋቱ የፖሊስ መርማሪዎች ጥያቄ በማቅረባቸውና ሌሎች አቃቤያን ህግ መዛግብቶቹም በማየት ውሳኔውን በመሻር ጉዳዮቹን ለክስ ሲያቀርቡ የለየለት የብሔር ጦርነት ውስጥ በመግባት በተለይም በወቅቱ የማዕከል አቃቤ ህግ ከነበረውና በአሁኑ ወቅት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዘዳንት ከሆነው አቶ በሪሁ ተወልደብርሃን፣ ኤርትራዊ እንደሆነ ከሚነገርለትና በፌዴራል ማዕከል ይሰራ ከነበረው ዘረሰናይ ምስግና፤ ቀደም ሲል የንፋስ ስልክላፍቶ ፍትህ ፅ/ቤት ከነበረው አቶ ሃይለማሪያም እና ሌሎች ትግራዋይ ከሆኑና በዋናነት በሃላፊነት ከሚሰሩ ትግራዋይ አቃቤያን ህግ ጋር በመሆን እኛ ትግራዋይ ተበድለናል፤ እየተጠቃን እንገኛለን፤ ኦሮሞ እና አማራ የሆኑ አመራሮች ትግራዋዮችን አላሰራ አሉ ወደሚልና የብሔር ይዘት ወዳለው እንቅስቃሴ ገባ፤ በተለያዩ ስብሰባዎችም ግልፅ ወገንተኝነት የታየበትና ንቀት በተሞላበት ሁኔታ በአመታዊ ስብሰባዎች ጭምር ሚኒስትሮችን የሚኮንኑና ከአንድ ባለሙያ የማይጠበቁ ንግግሮችን ማድረግ ቀጠለበት፡፡ በዚህ ሁኔታ ስራውን ሲሰራም በተለይም የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች ተከሳሽ በሆኑባቸው ጉዳዮች የተለየ ትኩረት በመስጠት ጥፋተኛ ለማሰኘትና የቅጣት ጣሪያውን ለማስወሰን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ሌሎች አቃቤያን ህግ ብቻ ሳይሆን ተቆርቋሪ የሆኑ ዳኞችም ጭምር በትዝብት እንዲያዩት ከማድረጉም በላይ ትግራዋይ ሰዎች ሲከሰሱ በነፃ ጭምር እንዲለቀቁ፣ ጥፋተኛም ሆነው ቅጣት ሲጣል እንኳ በተቻለ አቅም ዝቅተኛው ቅጣት እንዲጣል ምንም ተቃውሞ የማያሳየው ለምን በኦሮሞና አማራ ተዎላጆች ላይ ይሄን ያክል የአድሎና የጥላቻ ሁኔታ ያሳያል በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ ስንገኛኝ ይገልፁልን ነበር፤ ይሄም ጉዳይ ለተቋማችን አመራሮች ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት በጭምጭምታ ሰምተናል፡፡
የሆነ ሆኖ ከፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ጭምር መገለል የደረሰበት ዘርዓይ ወልደሰንበት ተቋሙን የሚመሩት ሚኒስትሮች እኛ ትግራዋይ ለሆንን ባለሙያዎች ጥሩ አመለካከት ስለሌላቸው መልቀቅ አለብኝ፤ በዚህም ጫና ስለማሳድር ሚኒስትሮቹ ጠርተው ማናገራቸው ስለማይቀር እንደፈለኩ እናገራለሁ ስለሆነም መልቀቂያ አስገብቼ የሚያደርጉትን አያለሁ በማለት ሲዝት ታዝበናል፡፡ መልቀቂያ ማስገባቱን በሰማን ማግስትም አንድ ወሬ ብቅ ይላል፡፡ ይኸውም ‹‹‹
ዘርዓይ መልቀቂያ እንዳስገባ ሚኒስትሩ ወዲያው መልቀቂያው ላይ ፈርሞ መልቀቅ ይችላል››› አለው ተባለ፤ በዚህም ዘርዓይ እንደዛ በትዕቢት እንዳልተናገረ፤ ለምነው ቆይ ይሉኛል እንጂ መልቀቂያዬ ላይ አይፈርሙዋትም፤ እኔም ልክ ልካቸውን ነግራቸዋለሁ ብሎ እንዳልፎከረ በአንድ ግዜ ኩምሽሽ ብሎ የአንድ ወር ደመወዙን የዓመት እረፍቱ ተጠቅሞ በመቆየት አንድ ወር በኋላ የመልቀቂያ ፎርማሊቲውን አሟልቶ ሊለቅ ችሏል፡፡

ከዚያም በኋላ የጥበቅና ፈቃድ በማውጣት ለመስራት የሞከረ ቢሆንም ብዙም ስኬታማ እንዳልነበር ቀድሞ ይሰራበት የነበረው ፍትህፅ/ቤት የስራ ባልደረቦቹ በስፋት ያወሩ ነበር፡፡ ከዚህ በመቀጠል ውሎውን በሙሉ ከአሁኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዘዳንት አቶ በሪሁ ተወልደብርሃን ጋር በማድረግ ዳኝነት እንሚሾምና አቶ በሪሁ የፌዴራል ፍትህ አካላትን ለሚያሽከረክረውና ትግራዋይ የሆኑ ሰዎች አስመላሽ ሉቄ( እውር) ብለው ከሚጡሩት አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ጋር ተነጋግሮ ሊያሾመው እንደሆነ እና አስመላሽ ወልደስላሴም ማረጋገጫ እንደሰጣው በአደባባይ ማውራት ጀመረ፡፡ በዚህ ንግግሩም ሁሌም ሲናገር ይደጋግማታል የምትባል አንድ ንግግረ ነበረች፤ እሱም ‹‹‹‹‹ ይህ የፍትህ ስርዓት በትግራዋይ ደምና አጥንት እንዳልተገነባ የአሮሞ አክራሪዎች እና የአማራ ነፍጠኞች ስርዓቱ ውስጥ ገብተውና በዳኝነት ስም ተሰግስገው ለስርዓቱ አደጋ እየሆኑ ነው፤ ስለዚህ እኛም ትግራዋያን ገብተን ይህን ጠባብ እና ትምክተኛ ሃይል ማሽመድመድና በማኛቸውም ሁኔታ ስርዓታችን ላይ አደጋ የሚጥለውን በህግ ልክ ማስገባት አለብን››› የሚል ነበር፡፡

ብዙሃኑ የቀድሞው ፍትህ ሚኒስቴር በአቃቤ ህግነት የምንሰራ ባለሙያዎች ለዳኝነት በተወዳደርንበት ዓመት ዘርዓይ ወልደሰንበትም ከጠበቃነት ወደ ዳኝነትነት ሽግግር ለማድረግ ተወዳደረ፡፡ በሂደትም ብቃት ያላቸው፣ ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸው፣ የትምህርት ዝግጅታቸውም እስከ ሁለተኛ ድግሪ እና ሌሎች ድግሪዎች ያሏቸው ባለሙያዎች በተለይም አማራና ኦሮሞ የሆኑ ባለሙያዎች ሳይሾሙ እነ ዘርዓይ ወልደሰንበትና ሌሎች ትግራዋያን፣ የዴህዴን እና ሌሎች የአጋር ድርጅቶች አባላትና አንዳንድ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑና ለስርዓቱ ወገኝተኛ የሆኑ እና በሙያ ብቃታቸውም ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ባለሙያዎች ተሾሙ፡፡ ዘርዓይ ወልደሰንበትም ለዳኝነት ሹመት እንደታጨና እንደሚሾም ካረጋገጠ በኋላ እኔ እእንደሆነ መሾሜ አይቀርም፤ ጠባቦችና ነፍጠኞች ግን እንተያያለን እንዳላቸው ለሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ፍርድ ቤት አካባቢ ስንገኛኝ በስፋት የምናወራው ጉዳይ ነበር፡፡ እንዳለውም ቃለመሃላ ፈፀመ፤ ዳኝነትም ተሾመ ነገር ግን ዘርዓይ ወልደሰንበት የዳኝነት መርህንና ስነምግባር እንዲሁም የህግ የበላይነት መርህን በመፃረር በችሎት ውስጥ ሳይቀር በኦሮሞና በአማራ ተወላጅ ተከሳሾች ላይ ሰይፉን ማሳረፍ ጀመረ፤ አቃቤ ህግ እያለ የጀመረውን የሁለቱን ብሔሮች የመጉዳት አባዜ ዛሬም በዳኝነት ስም የህውሃት መሳሪያ በመሆን ዜጎች በፍርድ ሂበት ውስጥ ያላቸውን መብት እንዳይጠቀሙና ከህግና ከስነ ስርዓት ውጭ በእነዚህ ብሔሮች ተወላጆች ላይ እርምጃውን ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን ዘርዓይ ወልደሰንበት ዛሬም በየመሸታ ቤቱ እምበር ተጋዳላይ እያለ ከትግራዋይ ሰዎች ጋር በመሆን በትዕቢት ጠባቦችን እና ነፍጠኞችን ልክ እናስገባለን ይላል፤ ይኸውንም በችሎት ፊት ከቀም ሲልም በአቃቤ ህግነት ዛሬም በዳኝነት ካባ በችሎት ፊት ጭምር እየገለፀው ይገኛል፡፡

እኛም በዚህ ፍትህ ስርዓት ውስጥ ለውጥ ማምጣት ቢቻል በሚል እየሰራን እንገኛለን፤ ነገ ሌላ ቀን ሆኖ የህግ የበላይነትን የምናይበት ቀን ይመጣ ይሆን ወይስ የህግ ትምህርት መማራችን ውሉ ጠፍቶብን እየኳተንን እንቀጥል ይሆን?

 

(ከውስጥ አዋቂው)