ይኽንን ቢያንስ ለ 6 አመታት አድርገውታል። ባንድ ወቅት ዘመነ ካሴ ላውንቸር ይዞ ፤ ኮስሞስ [ ቴዲ ] ከበስተኋላው ሆኖ የሚያሳይ አንድ ፎቶ ተለቆ ነበር ። በግንቦት ሰባት በኩል። የሚገርመው ነገር በዚያ ፎቶ ላይ ከሚታዩት ውስጥ አንዳቸውም ዛሬ ከድርጅቱ ጋ አይደሉም! አሁንም እንዲህ ያለውን ወራዳ ነገር በመለጠፍ፥ የአዲስ አበባ ወጣቶችን አማሎ ፥ አንዳች ስራ ያልተሰራበት የትጥቅ ትግል እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ነው። ይቺን የሰማያዊ ፓርቲ ልጅም የሚለማመጧት እርሷን የሚያውቁ ወጣቶች ተ አዲስ አበባ ተግተልትለው ኤርትራ በርሃ ይገባሉ በማለት ነው። ብሬ የአዲስ አበባ ልጅ ቢሆን ኖር የአዱ ገነት ልጅ ስነ ልቦና ይገባው ነበር! ግን በምርጫ 97 ስለሸወደን ሁሌ የሚሸውደን መስሎት ከሆነ ተሳስቷልም ስቷልም !

ኤርትራ [ አስመራ ] ውስጥ ሳምሶናይ ይዞ ላይ ታች ከማለት ያለፈ አንዳች ፋይዳ ያለው ነገር እየሰራኽ እንዳልሆነ አጠገብኽ ያሉት የትግል ጓዶችህ ነው የሚነግሩኝ! ስለዚህ ማርሽ ቀይር! እውነቱን ተናገር! ወጣት በማይሆን ነገር ማስጨረሱን ትተት ወጣቱን በሚሆን ነገር እንዲደራጅ እርዳ! የስልጣን ሱሱን ተወው በቃ! እኔ ልሙት አንተ የኢትዮጵያ መሪ አትሆንም! ከሰማይም ከምድርም አልተመረጥኽም! ይኽንን ስል እየደበረኝ ነው! ግን እውነት ነው!

አንተ ዛሬ ረስተኸው ሊሆን ይችላል ፥ ግን በአንድ ስብሰባ ላይ በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ኮንቬንሽናል ጦርነት ድርጅታችን ይጀምራል! ብለኽ ስትል በነሲብ የሚመሩት ደጋፊዎችኽ አዳራሹን በጭብጨባ አቀለጡት። በሁኔታው በጣም አፈርሁ። ያ ስድስት ወር ስድስት አመት ሆኖታል ዛሬ!

አንዳርጋቸው በተያዘ ማግስት « አፀፋዊ እርምጃ እንወስዳለን !» ብለህ ስትል ፥ ሳን ሆዜ አተገብኽ ነበር ቁጭ ብዬ ንግግርህን የሰማሁት። አ ንተ ግን አንዳርጋቸው ከተያዘ ሰሶስት አመት በኋላ ፥ ቃልኽን ከመተበቅ ይልቅ ፥ የአንዳርጋቸው ነው ብለኽ ያልኸውን ሬንጀር ሲያትል ለጨረታ አቅርበኽ ስታሻሽጥ አየንህ! ቃልኽን አለመጠበቅኽ ሳይሆን ፥ ትናንት ምን ብሎን ነበር ብሎ የሚጠይቅ ተከታይ እንደሌለህ ሳውቅ አፈርኹ! ያለ አውነት ፥ በግብዝነት የሚሆን ሁሉ ፍፃሜው ውርደት ነው! ይኽ ያንተ እና የድርጅትኽ ፍጣሜ ስለመሆኑ የምናያቸው ነገሮች ሁሉ ምስክር ናቸው!

ታማሪካ ተሳፍረው የሄዱት ጥቂቶቹ ተሳፍረው ተመልሰዋል! አንዳንዶቹ ካልተመለስን ሲሉ እንዲገደሉ ተደርገዋል! የገባኽበት ወንጀል እንጂ ነፃ የማውጣት ሂደት እንዳልሆነ እናውቃለን!

ከዚያ ባለፈ በአመት አንዴ አገሩን እየዞራችሁ የህዝቡን ተስፋውን ብቻ ሳይሆን ገንዘቡን መጥጣችሁ ፥ ሌላ ተግባራዊ ትግል እንዳይረዳ እንደ ካንሰር ሆናችሁበታል! ለውጥ በመጣበት ቦታ ሁሉ አለን ትላላችሁ! በበሽታ የሞተውን እርምጃ ወሰድንበት እያላችሁ ትወሸክታላችሁ! ድሮም እግዚያብሄርን ከማይፈራ እና እምነት አልባ የ 60ቹ ሽል ምን ይጠበቃል?! ምንም!

የግርጌ ማስታወሻ

«እነርሱ ቢያንስ በርሃ ገብተዋል» የሚሏት ፤ ልክ ወያኔዎች ቁስላቸውን ስትነካ « በርገር እየበላኽ» ከሚሏት ጋ የምትስተካከል መሞገቻ ነች። በርሃ ውስጥ መኖር ብርቅ አይደለም ! የወባ ትንኝም በርሃ ውስጥ ነው በብዛት የሚኖረው! ቁም ነገሩ « አለን!» ብለው ባሉበት አሉ ወይ ? ቁም ነገሩ ፥ የትውልድ ተወካይ ነን ብለው የትውልድ ህልም ከማምከን ባለፈ የሰሩት አንዳች ነገር አለ ወይ ? ቁም ነገሩ ፥ አስመራ ሄዶ « ትግረኛ መናገር ወይም መልመድ » ብርቁ የሆነበት መሪ ሳይሆን ፥ ለለውጥ የሚሆን ድርጅት ማቋቋም የሚችል ባለ ራዕይ መሪ ማግኘት መሰለኝ። እነ ዘመነ ተገፍተው ወጥተው ዛሬ የት ናቸው ? እነ ዘመነን ገፍቶ ያስወጣው ፥ ሌላ አዲስ ዘመነዎችን ቢያገኝ የሚያመጣው አንዳች ለውጥስ አለ ወይ ? መፍራት ሌላ ፥ እውነት ሌላ!

ሻዕቢያ በወያኔ ውስጥ አመራን የመጥላት ፍሬውን የቀበረ ነው! ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ ልዕልና እንደ ቀንበር ነው! ወያኔ ሌላ ስል ቢላ ነው! ብርሃኑ ደሞ ግራ የገባው ባዛኝ ነው!

ትግሉ የህዝብ ነው! ህዝብ ነው የሚያመጣው! እነ ብሬ ግን በርሃ መቀመጣቸውን ቀብድ አድርገው ለውጡን በ ፕሮፖጋንዳ ቦንድ ሊገዙ ያደቡ ናቸው! ይኽ ደሞ አይሆንም! ፔሬድ!