የሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ሥዕልታቦተ ጽዮን (ጽላተ ሙሴ) ወንድማማቾቹ ነገሥታት አብርሃ እና አጽብሐ (ኢዛና እና ሳይዛና) 4ኛው መቶ ክ/ዘ በአቡነ ሰላማ

 ከሳቴ ብርሃን አማካኝነት ክርስትናን በተቀበሉ ጊዜ ወደ አክሱም ከመወሰዷ በፊት በደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ ጣና ሐይቅ ላይ በሚገኘው በጥንታዊ የግእዝና የዕብራይስጥ መጠሪያ ስሙ “ደብረ ሳላሕ (ሳሕል)” በአሁን አጠራሩ “ጣና ቂርቆስ” በተባለው ስፍራ ከእስራኤል ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ የነበረችበት ታላቅ ቦታ መሆኑን ድርሳነ ጽዮን የተባለው መጽሐፍ፣ ከበርካታ ምዕት ዓመታት በኋላ ወደ አክሱም መወሰዷን ደግሞ ስለገዳሙ ታሪክ የሚያትተው የብራና መጽሐፍ ይናገራል፡፡

ይህች የምትመለከቷትን የጽዮን ማርያምን ሥዕል እዚህ ታላቅ ገዳም ላይ በታነፀችው የጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የመቅደስ ግድግዳ ላይ 3. 2. በሆነ መጠን የዛሬ 8 ዓመት የሣልኳት ሥዕለ ጽዮን ማርያም ነች፡፡ እናታችን ጽዮን ማርያም ከበዓሉና ከቦታው በረከት ትክፈለን! አሜን!!!

ይህችኑ ሥዕል በባነር (በሸራ ኅትመት) አዲስ አበባ ኮተቤ ኪዳነምሕረት ከሌሎች ሁለት ሥዕሎቸ ጋር ማለትም ከጌታ ራት (ምሴተ ሐሙስ) እና ከአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ የእረፍታቸው

ሥዕሎቸ ጋር ቅኔ ማሕሌቱ ላይ ታገኟታላቹህ፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com