Skip to content
1 ዲሴምበር 2017
አሁን ግን ስለኤች አይቪ በማይወራበት ጊዜ ለአካለ መጠን በመድረሳቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነዋል ይላሉ አቶ ዳንኤል።
“እነዚህ ወጣቶች በአብዛኛው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በትላልቅ የአበባ እርሻዎች፣ በፋብሪካዎች እና በኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ የሚገኙ ናቸው።” እናም በኢትዮጵያ ከአፍላ ወጣቶች ግንዛቤ ማነስ ጋር በተያያዘ የኤች አይቪ ስርጭትም በዚሁ የእድሜ ክልል ከፍተኛ ምጣኔ ይታይበታል ።
አቶ ዳንኤል ጨምረው እንደገለፁት በኤች አይቪ የሚሞቱ ሰዎች እንደሀገር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ዝምታንና መዘናጋትን ፈጥሯል። በተቃራኒው ደግሞ በወጣቶች መካከል ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ጨምረዋል።
ስለዚህ ምንም እንኳ ዛሬ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም የአጋላጭ ሁኔታዎች እየጨመረ መምጣት ግን ነገ የስርጭት መጠኑ እንዲጨምር ያደርገዋል። አቶ ዳንኤል “መዘናጋቱ ነገ ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ይገልፃሉ። ከነዚህ ወጣቶች ባሻገር ለኤች አይቪ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት እና የስርጭት መጠኑ ከፍ ያለው በወሲብ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ሴቶች፣ የረጅም ርቀት መኪና አሽከርካሪዎች እና በማረሚያ ቤት የሚገኙ ግለሰቦች ላይ ነው። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ በየጊዜው የኤች አይቪ ምርመራ እና ክትትል የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥርም አነስተኛ ነው ሲሉ አቶ ዳንኤል ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ።
ከዚህም በተጨማሪ ምንም እንኳን የትምህርት ሚኒስቴር ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በቋንቋ፣በሥነ-ዜጋ፣ በሥነ-ሕይወት የሥርዓተ ትምህርቶች ውስጥ ቢካተትም የተጠበቀውን ያህል ለውጥ እንዳልመጣ አቶ ዳንኤል ይገልፃሉ።
በየአመቱ ህዳር 22 የሚከበረው የፀረ ኤች አይቪ ቀን የዘንድሮ መሪ ቃል “አሁንም ትኩረት ለኤች አይቪ መከላከል” የሚል ነው።
Like this:
Like Loading...