ንዳዶች «መቀሌ፤ የሚባል፤ የሚደረግበትን እንዳትሰማ-እንዳታይ የተዘጋባትን ስብሰባ አስተናገደች» ይላሉ፤ አድዋ ተሾመች። ሌሎች የመለስ ቡድን «ሲፈርስ»-የስብሐት ቡድን «ሲነግስ» አይነት አባባል አላቸዉ።
የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ነባር መሪዎቹን ሽሮ አዳዲስ ሾሞ ማራቶን ጉባኤዉን አጠናቅቋል። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መሥራች እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፈዉ የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ወር በላይ በፈጀዉ ጉባኤዉ «ሥር ነቀል»ግምገማ ማድረጉን አስታዉቋል። የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ፤ የባለሥልጣናቱ ሹም ሽር እና ቃል ኢትዮጵያን ለሚያብጠዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ መፍትሔ ይሆን ይሆን?
በ1984 የያኔዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን)የመጀመሪያዉን የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመሠረተበት ስብሰባ ባሕዳር ዉስጥ ሲጀመር ስብሰባዉ ለጋዜጠኞች ዝግ ይሁን ክፍት የሚለዉ ሐሳብ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ተሰብሳቢዎችን አካራክሮ ነበር።የስብባዉ መሪ የነበሩት ባለሥልጣን ለሕዝብ ታግሎ፤ ሕዝብን አታግሎ እዚሕ የደረሰዉ ኢሕዲን-ኢሐአዴግ ከሕዝብ የሚደብቀዉ የለም» አሉ። ወሰኑ።ሹማምንቱ መሿሿም-መፋተጋቸዉን፤ ጋዜጠኞቹም ማነፍነፍ መዘገባቸዉን ቀጠሉ።
1984 በርግጥ 2010 አይደለም።እንኳንስ ዘመኑ ፓርቲዉም ከኢትዮጵያነት ወደ ብሔርነት፤ ከሐገር አቀፍነት ወደ አማራነት፤ ከኢሕዴንነት ወደ ብአዴንነት ተለዉጧል።አድጓል ወይም ወድቋል።ኢሕዲን አልነዉ ብአዴን-ሕወሐት አይደለም።ግን የሕወሐት አምሳያ፤ እሕት፤ ወይም አጋራነቱ አንድ ሁለት የለዉም።
ሰሞኑን መቀሌ ላይ የሆነዉን፤ ከሩቅ የሰማነዉ ከ26 ዓመታት በፊት ባሕር ዳር ላይ ካየን እና ከሰማነዉ የሚቃረን መሆኑ ግልፅ ነዉ።በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ከተደረጉ የፖለቲከኞች ጉባኤዎች ሁሉ የመቀሌዉ አንደኛዉ ባይሆን ከረጃጅሞቹ አንዱ ነዉ።አንድ ወር ካንድሳምንት ግድም ፈጀ።
ጉባኤተኞች በስብሰባቸዉ ማብቂያ ባወጡት መግለጫ የጉባኤያቸዉን ጠቃሚነት ፓርቲያቸዉ «ክልላዊና አገራዊ ተልዕኮዉን ከመወጣት አንፃር» በማለት ገልፀዉታል።ለሐገር እና ለክልል የሚጠቅም ያሉት ጉባኤቸዉ ግን እስከ ዉሳኔያቸዉ ድረስ ከሕዝብም
ከመገናኛ ዘዴም ዝግ ነበር።
አንዳዶች «መቀሌ፤ የሚባል፤ የሚደረግበትን እንዳትሰማ-እንዳታይ የተዘጋባትን ስብሰባ አስተናገደች» ይላሉ፤ አድዋ ተሾመች።ሌሎች የመለስ ቡድን «ሲፈርስ»-የስብሐት ቡድን «ሲነግስ» አይነት አባባል አላቸዉ።የእሳቸዉም አስተያየት ተመሳሳይ ነዉ።
እኝሕኛዉ ሁለተኛዉ።