የ79 ዓመቱ አዛውንት የአሜሪካ ስለላ ድርጅትን ለ 29 ዓመታት ያገለገለው ” Bill Oxley ” የተባለ የስለላ ድርጅት አባሉ በጤና ቀውስ በሆስፒታል ሳምንት ዕድሜ ብቻ አለህ የተባለው ግለሰብ ቦብ ማሪን መግደሉን ተናዘዘ!

ይህ ግለሰብ የስለላ ድርጅቱን 29 ዓመት በአሳሽ ገዳይነት ባገለገለበት ወቅት በመጨረሻዎች ሃያ ዓመታት ብቻ 17 ግለሰቦችን በታዘዘው መሠረት መግደሉንም አረጋገጠ!!

ለእነዚህ የግዲያ እርምጃ ትዕዛዝ ተቀብሎ ግዳጅን በመቀበል ግዴታውን ለመወጣት መግደሉን እንጂ ግለሰቦቹ ስለሚገደሉበት ምክንያት ለማወቅ ደንታም አልነበረኝም አለ! ሆኖም በአብዛኛው የአሜሪካንን ደህንነት ስጋት ውስጥ የከተቱ ሰዎች እንደሆኑ ብቻ ነው ግንዛቤ ያለኝ ብሏል ፤
ከነዚህ የግድያ እርምጃ ከወሰድኩባቸው ሰዎች እጅግ ልቤን የነካኝና የዘወትር የህይወቴ ዘመን ፀፀት የሆነብኝ የ 36 ዓመቱ ለግላጋ ወጣትና የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ ቦብ ማሪሊይ ብቻ ነው ብሏል!

በዚህም ይንን እጅግ ህዝብን ያተራምስ የነበረውን ሙዚቃውን በሰማሁበት ጊዜ ሁሉ በዓይነ ሂልናዬ ውስጥ እየመጣ ሲረብሸኝ ነበር የኖርኩት ሲል ይፀፀታል።

ቦብ ማሪሊን የአሜሪካንን ህልውና የሚፈታተኑ ሙዚቃዎች በመጫወት ከጥይትም ይሁን ከቦምብ ጥቃት በላቀ በሙዚቃው እልፍ አዕላፍ ደጋፊዎቹን ሁሉ ያንቀሳቅስ ነበር ብሏል! አልፎም በበርካታ የአለም አገሮችን ፀረ አሜሪካ ተግባራት ውስጥ በሙዚቃው ውስጥ እያጣቀሰ ወጣቱን ያነሳሳው ነበር ብሏል፤

ቦብ ማሪሊንን ኒዬርክ ከቤቱ ሲወጣ በድብቅ ቦታ ጠብቀን በሦስት ጥይት መትተነው ነበር ፣ ነገር ግን ትከሻውንና ክንዱን ተጎድቶ ከዚህም ተርፎ ሆስፒታል በመግባት አገግሞ ወደ አገሩ በመመለስ በአንድ ተራራማ ሥፍራ በሚገኝ ቤቱ መኖር ጀመሮ ነበር የሚለው ገዳዩ ቀጥሎም!

በአንድ ወቅት የሚኖርበትን ሥፍራ በጥንቃቄ በማጣራት የኒዬርክ ጋዜጣ ፎቶ ግራፍ አንሺ ነኝ በማለት መታወቂያና በአንገቴም የጋዜጤኛ መለያ በማንጠልጠል ካሜራዬን በመሸከም ቤቱ ሄጄ አገኘሁት ፤ በዚህንም ወቅት መጠነኛ ስጦታም በማበርከት ቅርበቴን ካመቻቸሁኝ በኃላ አንድ በርሱ ቁጥር የገዛሁትን ጫማም አበረከትኩለት።

ይህንን ጫማ ሰጥቼው ሊሞክረው የግራ እግሩን እንዳስገባ  አንድ ነገር ወግቶት ሲያስደነግጠው አይ ነበር ።

ጫማው ውስጥ ትንሽ የካንሰር በሽታን የተሸከመች ደቃቅ መርፌ እግሩን እንድትወጋው በማድረግ ለሞት አመቻችቼው ተለየሁት በማለት ይቀጥልና፡ በኋላም የካንሰር ታማሚ በመሆን ፈረንሳይ ሃገርና አሜሪካም መጥቶ ሆስፒታል ተኝቶ ከደዌው ፈፅሞ ማገገም አልቻለም ነበር !  እጅግ ከስቶና ሰውነቱ ሁሉ አልቆ ፎቶውን በመጨረሻዎቹ ጊዜ አይቼ ውስጤን እጅግ ረብሾኝ ነበር ።

በመጨረሻም ማያሚ ፍሎርዳ እንደሄደ እዚያው ነው ህይወቱ ያለፈው። በማለት ከገደላቸው ሰዎች ሁሉ ማንም ያዘንኩለት የለም ነገር ግን ዘንካታውና ለግላጋው ወጣት የሬጌ ሙዚቃ ንጉሥ ቦብ ማሪሊ ግን የተለየ ፍጡር ነው የሚለው የ 79 አመት  አዛውንትና የአሜሪካዊ የስለላ ድርጅት ጡርተኛ በጠና ታሞ ሊሞት የቀረው የሳምንት ግዜ እንደህነ ሲነገረው በማሳቹተስ ስቴት ሆስፒታል ይህንን በመናዘዝ ተሰምቶ የማያውቀውን ሚስጢር አጋልጧል።

በአበባየሁ አሉላ