በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ዲሴምበር 2, 2017 በቤልጂየም ብራሰልስ ጉባኤ አድርገው ነበር:: በዚህ ጉባዔ ላይ በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው ወገኖች ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበው ነበር:: ከዚህ ቀደም በመድረኩ ላይ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ “ከኢሕአዴግ በኋላ የምትፈጠረው ኢትዮጵያ ምን መሆን አለባት?” በሚል ያቀረበውን፣ የገረሱ ቱፋን “የለውጥ ተስፋና ልንሻገራቸው የሚገባን ተግዳሮቶች” በሚል ያቀረበውን ንግግርና የአክቲቭስት መስፍን አማን “ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ያለች ሃገር እና ለውጥ አማራጮች” በሚል የቀረበውን ንግግር ማስተናገዳችን አይዘነጋም። ለዛሬው ደግሞ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ አቶ ባይሳ ዋቅወያ “እያንዣበበ ያለው አደጋና መፍትሄው” በሚል ያቀረቡትን ንግግር ይዘን ቀርበናል::