December 8, 2017 05:58

ኣለም ገብረዋህድ ከሚመራው የህወሓት ቢሮ ከሚገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፣ በትግራይ ክልል ኣስተዳደር ካሉ ዋና ቢሮዎች እስከ ቀበሌ ኣስተዳዳሪዎች እና ተጓዳይኝ ኣካላት የተዘረጋው የሙሱና ፣ጸረ መልካም ኣስተዳደር የክልሉ ህዝቦች የጎዱ ፣ በጥቀመኝ ልጠቅምህ፣ በኣካባቢ ፣በቲፎዞኝነት ፣የተቦዳደኑ ኔትዎርክ (ሰንሰለት ) ሊመቱ 5 ሳምንታት የፈጀው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ውሳነ በማስተላለፉ የኣባይ ወልዱ ቡዱን ኔት ዎርክ በስጋት እንደተጨነቀ ከወዲሁ ይነገራል ።

ኣንድ ኣንድ ወገኖች ደግሞ በትግራይ ክልል ያለው ሙሱና ፣የመልካም ኣስተዳደር ሽግር ፈጣሪው የኣባይወልዱ ቡዱን ብቻ ነው ? ሁሉ ህዝብ እንደሚያውቀው በትግራይ የሚፈጸሙ ሁሉ በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣብላጫ ድምጽ ነው። ኣሁን ለኣባይ ወልዱ ኔት ዎርክና ቡዱን ብቻ ወንጀለኛ ኣድርጎ መታዬቱ ለምን ? ሏበይ ሏብሮማ ኣሉ የትግራይ እውቅ ኣቦይ ካሳ ደበስ ።

ይህ ካልኩ ፣ የነስብሃት ነጋ ፣ኣባይ ጸሃዬ ፣ ስዩም መስፍን፣ኣዲስኣለም ባሌማ፣አርከበ ዕቁባይ በዬነ ሞክሩ ፣ ኪሮስ ቢተው፣ብርሀነ ገ/ክርስቶስይ ፣ቴድሮስ ሓጎስ፣ ወዘተ ንጹሃን ናቸውን? ማን የሁሉም ኮር ሆነና ?

በእኔ እምነት የኣባይ ወልዱ መዋቅር በኣካባባዊነት ፣በሙሱና ፣ደብቀኝ ደብቀኝ (እከከኝ እከከኝ ) እያሉ የክልሉ ኣመታዊ ባጀት ፣ ተከፋፍለው ሌላ ሃብት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ እደኣካበቱበት የትግራይ ህዝብ ያውቀዋል ። በመሆኑም እኔ የኣባይ ወልዱ ሰንሰለት ቢበጣጠስ ደስታው ኣልችለውም ።

እኔ እምለው ያለሁ ዋናው የሙሱናም የመልካም ኣስተዳደር ፣የኣድልዎ የታጠቀ እና ስፋትና ጥልቀት ያለው ኮር ያለው በማኸል ኣገር እና በኣዲስ ኣበባ ነው ። ስለሆነ የህወሓት መሪዎች ግምገማቸው ሃቀኛ ከሆኑ ዋናው ከርም መምታት መቻል ኣለበት ።

ከኣስገደ ገብረስላሴ ፣

መቀለ