ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል።
የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ የሚገኝበት ነው።“ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ። ጭንቅላታቸው መጠኑ በጣም ያነሰ ነው። እጅና አይናቸውም ተጎድቶ ይወለዳሉ። ሰው ታሞ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄድ ከ ‘ነርቭ‘ ጋር የተያያዘ ችግር ነው ይባላል።” በማለት የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ዱቤ ጋሸራ ሚጁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በዚሁ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት እኚህ አዛውንት “ድሮ ይህንን የሚመስል ችግር አልነበረም“ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-42266025
“መንግሥት የወጣቱን ቅሬታ ከመስማት ውጭ ምንም የለወጠው ነገር የለም።“
አይናቸው ከማምረቻው ውስጥ በሚወጣ ኬሚካል መጎዳቱን እንዲሁም በአግባቡ ቆመው መሄድ እንደሚያቅታቸው ነግረውናል። በተጨማሪም ከዚሁ ችግር የተነሳ በከብቶች እና በዱር እንስሳት እየደረሰ ያለው እልቂት ለትልቅ ችግር አጋልጦናል ይላሉ።
‘ሳናይድ‘ እና የአካል ጉዳተኝነት
የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ ወርቅና ነሐስ በሚያመርትበት ወቅት ወርቁን ለማፅዳት የሚጠቀምበት ኬሚካል ‘ሳናይድ‘ ይባላል። ይህ ኬሚካል ራስ ምታት፣የልብ፣ የአእምሮ እና የነርቭ ህመሞች እንደሚያስከትል የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጦና ዋሬ ነግረውናል። ከዚህም ባሻገር የሰው አጥንት ለማጠንከር የሚረዱ እንደ ብረት(አይረን) ያሉ ንጥረ ነገሮች ከሰው እና ከእንስሳት አካል ውስጥ መጠኑን ይቀንሳል። ይህም ለአጥንት መሳሳት እና መሰባበር እንደሚያጋልጥ አቶ ጦና ዋሬ ያስረዳሉ። የወርቅ ማምረቻው የሚገኝበት ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥም የአካል ጉዳተኝነት ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። የቢቢሲ ሪፖርተር በአካል በቀበሌው ተገኝቶ አንድ ኪሎ ሜትር ባልሞላ መንደር ውስጥ ሶስት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናትን አይቷል። በህፃናት ላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት በቀበሌው ውስጥ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ነዋሪዎች ወልደው ለመሳም እየተሳቀቁ እንደሆነ ይናገራሉ። ወ/ሮ ደምበሊ ሔጦ የአካል ጉዳት ያለባት ህፃን አላቸው፤ “ልጆቼ በታመሙ ቁጥር ስጋት ያድርብኛል። ሌላ ተጨማሪ ልጅ ለመውለድ እንደዚሁ ልጅ ይሆንብኝ ይሆን ስል እሰጋለሁ” ይላሉ። በተጨማሪም ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን ወልደው ከአካል ጉዳት ነፃ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ማርገዛቸውን እንደሚደብቁ፣ የአካል ጉዳት ያለበትን ህፃን የወለዱ እናቶችም ከሰው አይን ከልለው በቤት ውስጥ ደብቀው እንደሚያሳድጓቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም የሳይናይድ ኬሚካል የተቀላቀለበት ወራጅ ውሃ የሚጠጡ እንስሳት ወዲያውኑ እንደሚሞቱ፣ የተበከለ አየር ውስጥ የሚቆዩት ደግሞ ከወደቁ በኋላ መነሳት እንደማይችሉ፣ አጥንታቸውም በቀላሉ እንደሚሰበር የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።
“ድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ይደርስብኝ ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።“
https://www.bbc.com/amharic/news-42266025