ለምን ያህል ቀን እንደሚቆይ ይፋ ያልተነገረለት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ መቀመጡ ተሰማ። የግንባሩ ልሳኖች እጅግ ጠንካራ ውሳኔ እንደሚወሰን አስታውቀዋል። መረጃው አለን የሚሉ ግንባሩ ሊፈርስ እንደሚችልና አሃዳዊ ፓርቲ ለመሆን መዘጋጀቱን እየጠቆሙ ነው። በብቃትና በውሳኔ አሰጣጥ ችግር የተገመገሙት አቶ ሃይለማሪያም እጣቸው ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።

ህወሃት ሁለት ወር የፈጀ ስብሰባ ማድረጉና በግምገማው ወቅት ከፍተኛ የተባለ መጠራረብ እንደነበር ይታወሳል። በዚሁ የሰላ መወራረፍ ያኮረፉና ስብሰባ ረግጠው የወጡም ነበሩ። ከግምገማው በሁዋላ በተደረገው ጥገናዊ ለውጥ በአሸናፊነት የወጡት ዶክተር ደብረጽዮን የመሩት የህወሃት አዲሡ ስራ አስፈጻሚው የራሱን ውይይት ካደረገ በሁዋላ ዛሬ እንደተሰማው ግንባሩ ስብሰባ ተቀምጧል።

ሁሉም እሀት ድርጅቶች ሲፈጠሩ የነበራቸውን ቅርጽ በመቀየራቸው፣ በተለይም በኦሮሞያና በአማራ ክልል የህወሃትን የበላይነት የመቀበሉ ጉዳይ እያከተመ በመሆኑ ከዛሬ አራ ሁለት ዓመት በፊት በሃዋሳ ቀርቦ የነበረውን አጀንዳ ዳግም ሊያነሳ እንደሚችል ለመረጃው ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። Related image

አቶ መለስ ይመሩት በነበረው የሃዋሳው የግንባሩ ጉባኤ፣ ኢህአዴግ ግንባር መሆኑ ሊቆም ይገባል በማለት ሃሳብ የሰጡት አቶ ተፈራ ዋልዋ ነበሩ። አቶ ተፈራ ይህ አጀንዳ ቀድሞ የተያዘ ቢሆንም ተግብራዊ ያልሆነበት ምክንያት ገልጽ እንዳልሆነም ተናግረው ነበር። የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ሽመልስ ሃሰኑም ተጨማሪ አቅርበው በጉዳዩ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

ከህወሃት መካከልም በድጋፍ አስተያየት የሰጡ ቢኖሩም አቶ መለስከሁለት ዓመት በፊት ስራ አስፈጻሚው ይህንን አጥንቶ በወቅቱ ለተካሄደው የግንባሩ ጉባኤ ማቅረብ እንደነበረበት፣ ይሁንና ተግባራዊ አለማድረጉን አመላክተው አዲስ አጥኚ ተዋቅሮ ከሁለት ዓመት በሁዋላ በአዳማ በሚካሄደው የግንባሩ ስብሰባ ላይ ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጠው አረጋግጠው ነበር።

በዚሁ ጉዳዩ ቢታለፍም እንደተባለው ከሁለት ዓመት በሁዋላ ተደርጎ በነበረው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ሳይነሳ ቀረ። ይህንኑ ተከትሎ እንደ ምክንያት የቀረበው፣ ግንባሩ ከፈረሰና ደርጅቶቹ ከተዋሃዱ ካፒታላቸው ስለሚቀላቀል የኤፈርት ሃብት ጉዳይ እንዴት ይሆናል የሚለው በህወሃት በኩል ስጋት በመፍጠሩ ነበር።

ሶስቱ እሀት ድርጅቶች በኮንጎ ጫማ ቸርቻሪነት እየዳከሩ ማእድን ማምረት ከጀመራ፣ ፋብሪካ ከተከል፣ የውጪና የአገር ውስጥ ንግዱን ከተቆጣጠረውና ካፒታሉ ከአፍሪካ አንደኛ ከሆነው ኤፈርት ጋር እንዴት ሃብታቸውን ይቀላቅላሉ? የሚለው ጉዳይ መልስ ሳይገኝለት አቶ መለስም ሄዱ፤ ጉዳዩም በእንጥልጥል ዛሬ ድረስ ቆየ።

መርጃ እንዳላቸው የሚናገሩና ለኦህዴድ ቅርብ የሆኑ እነድሚሉት የእነ አቶ ለማ መገርሳ፣ አባ ዱላ ገመዳ ንግግር፣ የኦህዴድና የብአዴን ቅርርብ የዚሁ ግንባሩን የማፍረስ ስራ አካል እንደሆነ ይናገራሉ። እነዚሁ ክፍሎች አሁን ያለው የብሄርና የጎሳ ፖለቲካ አደጋው የከፋ ከመሆኑ በፊት ህዝብ የሚፈልገውን ማድረግ አማራጭ ስለሌለው ኢህአዴግ የዘራውን የጎሳ መርዝ ለመስብሰብ የሚያስችለው ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁም ጋር በተያያዘ የሩዋንዳን የጄኖሳይድ አዋጅም ሊመክርበት እንደሚችል ግምታቸውን ሰጥተዋል። ለዚሁም እንደማስረጃ የዶክተር ወርቅነህን የሩዋናዳ የቅርብ ጊዜ ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ያስታውሳሉ።

ዛጎል ዜና