T
Pin
Email
Share

መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

 

ዕለቱ ቅዳሜ ነዉ። ያለሁትም በሌሎች ሀገር ነዉ። ሆዱ የሞላ ስደተኛ ነኝ! እነሱ በርገር የጠገበ የሚሉኝ ዓይነት ነኝ። በነገራችን ላይ በርገር ለጤንነ ጥሩ ባለመሆኑ ከተዉኩት ዓመታት አስቆጥሪያለሁ። ቆሜ የእነሱን መጨረሻ ያሳየኝ ከሚል ጸሎት ጋር ለጤንነቴ መልካም ሳይሆን አልቀረም ።

ለማንኛዉም ቀዝቃዛዉ አየር እኔን ብቻ ሳይሆን ድመቶቼንም አጨብጧቸዋል። መጪዉ የገና በዓል ደርሺያለሁ ማለቱን የሚያበስረዉ በየቤቱ በር ላይ ድርግም ጭልም በሚለዉ ጌጣ ጌጥ ብቻ ሳይሆን ጣትና ፊትን እንደ እሳት ወላፈን በሚለበልበዉ ውርጩ ጭምር ነዉ። አዎ ገናም ትንሳኤም መጣሁ እያሉ ነው። ሁለት ሺህ አስራ ሰባትም የትናንት ሊባል የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ናቸዉ። የሕወአት/ኢሕአዴግም ዘመን እንደ አሮጌዉ ዓመት አያበቃለት ይመስላል። የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች በመጨረሻ የማልኮም ኤክስን “ማንም ነፃነጥን አይሰጥህም …ወንድ ከሆንክ አስገድደህ ተቀበላቸዉ!” የሚለዉ አባባል የተሰማቸዉ ይመስላል …. እናም የቆረጡ ይመስላል ። በአንፃሩ ደግሞ ወያኔዎች የዘመናችን ፊታዉራሪ መሸሻን መስለዋል።የጉዱ ካሳን ምክር እብደት ይሉ የነበሩት ፊታዉራሪ መሸሻ ፍቅርን ሲያባርሩ ከሚጋልቡት ፈረስ ወድቀዉ መጨረሻቸዉ ሆኗል። ወያኔዎችም በአማራና ኦሮሞ ፍቅር በመበሳጨት ግልቢያ ይዘዋል። ፍቅር ያሸንፋል ያለዉ ማን ነበር?

 

ያኔ ኢትዬጲያን እንቅልፍ ላይ ሳሉ እሳቸዉ ብዙ ነግረዉን ነበር። ብዙም ተስፋ ገብተዉልን ነበር። በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ ከዚያም ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ልብስም ትቀይራላች ብለዉን ነበር። በእዉነት ያኔ እኛም በአዛውንቱ ሜዠር (ይቅርታ መለስ ለማለት ፈልጌ ነዉ) ህልም ደስ ብሎን ነበር። በእርግጥ ዛሬ እሳቸዉ ስለሌሉ የሞተ ለመዉቀስ ባይዳዳኝም አልጋ ወራሾቻቸዉ (እነ ደብረ ሴይጣን) ግን አሉ። ኢትዮጲያን እንደ የጆርጅ ኦርዌሉ አቶ ጆንስ እርሻ ያልሙ የነበሩት መዥገር መለስ (ይቅርታ ሜዠር ማለቴ ነው) በሞት ተለይተዉ ያሉበት ቦታ ባይታወቅም እርሻዉ ግን እየታረሰ ሳይሆን እየታመሰ ነዉ። ሕዝቦቹም እንደተራቡና እንደታረዙ ነዉ። የአልባኒያ ኮሚንዝምና የሕወአት ሕልም ቅዠት ሊሆን ይሆን? አይደረግም!!….የእልፍ አእላፍ ተጋዳላይ ሕይወት ቀጥፎማ አይደረግም … የደደቢት ህልምማ እንዴት ትነጥፋለች!? ‘ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ እኩል ናቸዉ እንደ ትግሬ ባይሆኑም’ ነበር ያለዉ ኦርኤል?

 

ወያኔ ጫካ ሆኖ ርዕዮተ ዓለሙን ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ አርባ ዓመታት አልፎታል። በእነዚህ ላለፉት አራት አስርተ ዓመታት ታዲያ ዓለም በብዙ መልኩ ቢቀየርም እነ ስብሃት፣ ደብረ ሴይጣን፣አቦይ ፀሐዬ የመሳሰሉት ግን አንደ እባብ ቆዳቸዉን እየቀያየሩ አንዴ አዲስ አባብ ሌላ ጊዜ ደግሞ መቀሌ እየተመላለሱ በተዓድሶ ስም ያረጀና ያፈጀ የብሔር ብሔረሰብ ገበጣቸዉን መጫወት ቢፈልጉም ሕዝቡ ግን በቃኝ እያለ ነዉ። እነርሱ ሊለወጡ ባይፈልጉና ባይችሉምለዉጥ ግን የግድ ነዉ። እንኳን የሚበላዉና የሚለብሰዉ ያጣ ሕዝብ ቀርቶ የሞላለት ሰዉ እንኳ ባሪያ ወይም ጭሰኛ ሆኖ መዝለቅ አይችልም ምክንያቱም ያለ ነፃነት መኖር የሰዉ ልጅ ባሕሪ አይደለም። ስለዚህም ለውጥ ግድ ይላል።

 

በነበረና ባልነበረ ታሪክ አንዱን ከአንዱ እያፋጁ መኖር ለዚህ ትዉልድ የማይመጥን ተራና ያረጀ የደደቢት ደደብ ቀልድ መሆኑን ሊረዱ አሁንም አቅም ቢያንሳቸዉም የለዉጥ ማዕበሉ ግን ለዉጥን መፍጠሩ አይቀሬ ነዉ። አሁን የእነርሱ ምርጫ ሁለት ብቻ ነዉ። ወይ ይህን የመሰለን ማስጠንቀቁያ ሰምቶ እየመጣ ካለዉ ማዕበል ማምለጥ አልያም እንደ ጋዳፊና መሰሎቹ የማዕበሉ ሰለባ መሆን። ምርጫዉ ይህ ብቻ ነዉ። እንደቀድሞዉ የኦሮሞን ወጣት ግራ በተጋባ የኦሮሞ ወታደር አልያም በሱማሌ ልዩ ኀይልና በአጋዚ አንገቱን የምታስደፋበት ዘመን አብቅቷል። በተመሳሳይም አማራው በቃኝ ብሏል። ይህ ደግሞ ቀላል ቁጥር ያለው ሕዝብ አይደለም። አጥፍቶ ለመጥፋት እንኳ የሚከብድ ቁጥር ነዉ። ስለዚህ በግል ብዙ መማር ባትችሉ እርስ በእርስ ተረዳድታችሁ በእናንተ እና ቆመንለታል በምትሉት ሕዝብ ላይ አየመጣ ያለውን የሩዋንዳ መንፈስ አስወግዱ። እንኳን የሰዉ ልጅ ፈጣሪም በቁጣ ምድርን ከሕዝቡ ጋር ዶጋመድ እንደሚያደርግ በሰዶምና ጎሞራምድር አሳይቷል። ዓይኖቻችሁ እና ሐሳባችሁ የመቀሌን ዳንቴል በመስራት ተወጥሮ ስትቅበዘበዙ የቁጣዉ እሳት እንዳያከስላችሁ በጊዜ ንቁ። አሁን ጊዜው ለመቀሌ ዳንቴል መስሪያ ጊዜ አይደለም።

 

የትግራይ ሕዝብም ለሃያ ሰባት ዓመታት የደሃ ባላባት ሆኖ ከኖረበት የአስተሳሰብ ድህነት ወጥቶ እራሱን ማዳን ይጠበቅበታል። ለዚህ ደግሞ የትግሬ ሙሁራንና በሚዲያ ላይ ያሉ የትግሬና ትግራይ ጆሮ አደንቋሪ አክቲቪስቶች የሕወአት አፈ ቀላጤነትን አቁመዉ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ጋር መጠጋት ይበጃቸዋል። አለበለዚያ አንቦና ጎንደር የተነሳዉ እሳት ተከዜ ሲደርስ ይጠፋ ከመሰላቸው ሞኝነት ነው። በመቶ ሺህ የሚቆጠር የአማራና ኦሮሞ ንፁሐንን የቀጠፈዉ የደደቢት ደደብ ሕልም… በመቶ ሺህ የሚቆጠር የአማራና ኦሮሞ ንፁሐንን በእስር ቤት ያሳጎረዉ ሰንካላ የጥቂት ትግሬዎች እኩይ መንፈስ ከሞት በሃላ ለሚመጣዉ ሲሆል ብቻ ሳይሆን እየቀረበ ላለውም ምድራዊ ሲሆል ይዳርጋቸዋል። ጆሮ ያለዉ ትግሬ ይስማ። ይህ ወንድሚያዊ ማስጠንቀቂያ ነዉ።

ፈጣሪ እየመጣ ካለዉ አስፈሪ ማዕበል ይሰዉረን።