
የአንድነት ሐይሎች ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል
አሁድ ዴሴምበር 17፣ 2017፤ 3 አገር አቀፍ ፓርቲዎች በአሜሪቻ መናገሻ ከተማ፤ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ትልቅ ሕዝባዊ ስብሰባ በመጥራት በትግሉ ውስጥ በብቃት ለመሳተፍ አስፈላጊ ነው ያሉትን አሰላለፍ ለሕዝብ ይፋ አደረጉ። ድርጅቶቹም ሰማያዊ ፓርቲ፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ና የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ሲሆኑ፤ ረዘም ላለ ጊዜ ሲመካከሩና ሲነጋግሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዚህ ዕለት ተባበሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውን አብሰረዋል።
ሸንጎ የዛሬውን ስምምነት በርካታ ፋይዳዎች የሚያመላክት አንደ ከፍተኛ አገራዊ ክንዋኔ ይቆጥረዋል። በአንድ በኩል አሁን በአገራችን ውስጥ ተቀጣጥሎ ካለው ሕዝባዊ ትግል አኳያ ሲታይ ይህ ስምምነት የተቃዋሚውን ጎራ የሚያደምቅ፤ ሌሎች ስምምነቶች፤ ሌሎች ሕብረቶች፤ ሌሎች ውሕደቶች አንዲፈጠሩ ፈር ቀዳጅ ክስተት ነው።
በሌላ በኩል ይህ ክንዋኔ ከሕዝብ በኩል በተቃዋሚው ጎራ ላይ ለሚቀርቡት አግባብ ያላችው ቅሬታዎች በከፊልም ቢሆን መለስ የሚሰጥ ነው። አንደ አድል ሆኖ፤ አንዳንዴም አፋኙ ስርዓት በሚፈጥረው አሻጥር አማካኝነት በፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ተስፋ የሚያስቆርጡ በርካታ መሰነጣጠሮች ታይተዋል። ስምምነቱ ይህን አዝማሚያ የሚቀለብስ፤ አብሮ መስራትን የሚያጎለ
ብትና መደመርን የሚያበረታታ ድርጊት ነው። 3ቱ ድርጅቶች በዚህ ብቻ ተወስነው የሚቀሩ ሳይሆን ወደፊት በሚያደርጉት ጉዞ በአነሱና ከሌሎች ተቃዋሚ ሃይላትም ጋር ሰፋ ያለ ትብብር፤ ህብረትና ውህድት መፈጠር አንዳለበት አጥብቀው ያምናሉ።
አንዲያም ሲል የተዳከመው የተቃዋሚ ጎራ፤ የውስጥና የውጭ፤ ቀኝና ግራ፤ በሳልና ጥሬ ሳይባል በአንድነት ቆሞ ያለውን የሰው ሃይልና ቁሳዊ ጥሪት አንዲያሳድግ ያስችለዋል። የተቃዋሚው ጎራ ድርጅታዊ ጉልበት በጨመረ ቁጥር አምባገነኑን ስርዓት ለመቋቋም ያለው ብቃት አያደገ ከመምጣቱ ባሻገር አራሱን ከጥቃት ለመከላከልና ብሎም ህዝብን ለመምራት ከሚያስችለው ደረጃ ላይ ይደርሳል።
አምባገነኑን መንግስት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት፤ ከሞላ ጎደል ከሱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሃይል ማሰለፍ አስፈላጊ አንደሆነ ግልጽ ነው። ለዝህ ደግሞ በየቦታው ተንጠባጥቦ ያለውን የተቃዋሚ ሃይል ማሰባሰብ፤ ማቀናጀት ለነገ የማይባል ተግባር አንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህ ስምምንት ይህንኑ በስራ ለመተግበር የታለመ አንደሆን ስንገልጽ በታላቅ ደሰታ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘለዓልም ትኑር
የተባበረ ሃይል ያሸንፋል
Like this:
Like Loading...