28 December 2017
በእነ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ለተከሰሱ 22 ሰዎች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ መጥሪያ የደረሳቸው የኦሮሚያ ክልል
ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ
ድርጅት (ኦሕዴድ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓቢይ አህመድና (ዶ/ር) የለገዳዲ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በተጠሩበት ቀን ለምስክርነት መቅረብ ስለማይችሉ ተለዋጭ ቀን እንዲሰጣቸው የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ፍርድ
ቤቱ ንበአክብሮት በደብዳቤ ጠየቀ።
ጽሕፈት ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው የጠየቀበት ምክንያት ለምስክርነት የተጠሩት የሥራ ኃላፊዎች በአገራዊ ጉዳይ
ላይ ውይይት እያደረጉ ነው በማለትነው።
በተመሳሳይ ለዚሁ የክስ መዝገብ በምስክርነት የተጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በጽሕፈት ቤታቸው
በኩል በሥራ መደራረብ ምክንያትመገኘት እንዳልቻሉ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።