December 31, 2017 06:44

የኢሓኢደግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቋል። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው 9 ከህወሃት፣ 9 ከብአዴን፣ 9 ከደሃዴን እና 9 ከኦህዴድ ያሉበት ሲሆን፣ ከኦህዴድ 3 ( አቶ ድሩባ ኩማ፣ አቶ ወርቅነህ ገበየሁና አቶ ፍቃዱ ተሰማ)፣ ከኦህዴድ 3 (አቶ አለምነህ መኮንን፣ አቶ ከበደ ጫኔና አቶ አህበድ አብተው) ወደ ህወሃት የወገኑ መሆንቸው፣ ህወሃት 9ኙን አባላቱን እና ድሃዴኖችን ጨመሮ በኮሚቴው በኮሚቴው አብላጫ ድምጽ አለው። በመሆኑም ኦህዴድና ብአዴን በፓርላማው ያላቸው አብልጫ ድምጽ በመጠቀም ወይንም ከኢሕአዴግ ግንባር በመውጣት የጠየቋቸው ጥያቄዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ መስራት እንዳለባቸው ካላደረጉ፣ በኢሓዴብ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ምንም ለዉጥ እንደማይመጣ ብዙዎች ተንብየዋል።

“የሀገሪቱን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንዳሳለፈ የሚጠበቀው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ በስብሰባው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ ነገ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።” ሲል የዘገበው አይጋ፣ የስራ አስፈጻሞ ኮሚቴው የአገር ችግርን ለመፍታት ዉሳኔዎች እንዳሳለፈ ዘገቧል። ዉሳኔዎቹ ምን እንደሆኑ ገና አልታወቀም።

ከሃላፊነታቸው ለመነሳት መለቀቂያ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳም፣ ወደ ሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው ተመልሰዋል። የተመለሱት የጠየቁት ጥያቄ ተመልሶ ይሁን ሳይመለስ መግለጫው ሲወጣ የምናየው ይሆናል።
የአገሪቷ ችግሩ በዋናነት አንደኛ በሕወሃት/ኦህዴድ/ኦነግ የተዘረጋው የእር ፖለቲካና የዘር ፌዴራሊዝም መሆኑን ሁለተኛ የሕወሃት የበላያነትና ደህንነቱንና እና መከላከያዉን በመቆጣጠር አፍራሽና ነቃይ መሆኑ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። በዚህ ምክንያት የአገሪቷን ፖለቲካ de-ethnicized የሚያደደርግ፣ የኦሮሞ መሬት፣ የሶማሌ፣ የትግሬ የሚለው ቀርቶ ማንም ዜጋ በማንኛውም የአገሪቷን ክፍል በነጻነት እንዲኖር የሚያስችል እና መከላከያዉና የደህነነት መዋቅሩ ገለልተኛና ከአንድ አካባቢ የመጡ ቡዶችን ሳይሆን በትክክል የኢትዮጵያን ሕዝቡ ሁሉ የሚያገለግልና የሚያንጸባርቅ ይሆን ዘንድ ዉሳኔዎች መተላለፍ አለባቸው። አለበለዚያ የአገር ችግር የበለጠ እየተባባሰ ከመምጣቱም ባሻገር መንግስት ችግሮችን መቆጣጠር አቅቶት አገር ወደ ዘመነ መሳፍንት ልትሸጋገር ትችላለች።

ሌላው አንዳንድ ወገኖች የሚያነሱት ሐሳብ አለ። ህወሃት ኦህዴድ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ (አዲስ አበባ ላይ ያላቸው የኦሮሞን ጥቅም የማስጠበቅ ጥያቄ፣ በላቲን አፋን ኦሮሞን የፌዴራልና የአዲስ አበባ የስራ ቋንቋ ማድረግ ፣ ድሬዳዋና ሞያሌው ለኦሮሚያ ማስረከብ፣ ኦህዴድ ያለ ሕወሃት ጣልቃ ገብነት ክልሉን እንዲያስተዳደር መፍቀድ ……..) ኦህዴድን ከጎናቸው አሰልፈዉም ሊሆን ይችላል። አባ ዱላ የፓርላማ አባላት በአዲስ አበባ ጉዳይ የትጠራዉን ስብሰባ እንዲካፈሉ ለማግባባት ሲሞክር የነበረውም ከዚህ የተነሳ ሊሆንም ይችላል።

———————————————-///————————————–

አባዱላ ላለፉት 25 አመተት የሕወሃት አሽከር ሆኖ ያገለገለ ደም በእጁ ያለበት ወንጀለኛ ነው

ግርማ ካሳ

አባዱላ ላለፉት 25 አመተት የሕወሃት አሽከር ሆኖ ያገለገለ ደም በእጁ ያለበት ወንጀለኛ ነው። የቀድሞ ኦህዴድ ከሕወሃት ጋር በመሆኑ ብዙዎች ያፈናቀለ፣ ብዙዎች ያስገደለ ነው። አባ ዱላም የቀድሞ ኦህዴድ ቁልድ ሰው ነበር።

አባዱላ የድርጅታዊ ማእከላዊነት በመጻረር ፣ በኢሕአዴግ አፈንግጦ ከፓርላማው ለመልቀቅ መወሰኑን ገለጸ። ያንን በማድረጉ ብዙ ምስጋናና አድንቆት ተሰጠው። አሁን ደግሞ ተመልሶ በፍቃዱ ሃላፊነቱን ያዘ። ያን ያደረገው እነ ለማ መገርሳን በመካድ ከሕወሃት ጋር በማበሩ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ ከፍተኛ ወገዛ በሶሻል ሜዶያ እየቀረበበት ነው። መቀለጃ እየሆነ ነው። (ከዚህ በታች ያለው ፎቶ እንደሚያሳየው)
ሆኖም ግን አሁንም ባንቸኩል ጥሩ ነው ባይ ነኝ። የኢሃዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ስብሰባ መግለጫና ዉሳኔ መጀመሪያ ማንበብ አስፈላጊ ነው።

ሰዎቹ ባለህበት ረገጥ ከሆነ ዉሳኔያቸው ፣ ተራና ላይ ላዩን ጥገናዊ ለውጥ ለማድረግ ብቻ አስበው፣ ትልቅ እድል አመለጣቸው ማለት ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦርነት አወጁ ማለት ነው።

መግለጫው አቅጣጫ ቀያሪ መሰረታዊ ዉሳኔዎች መወሰናቸው ከገለጸና ዉሳኔዎቹም ተግባራዊ ከሆኑ፣ ምን አልባት አሁን የከረረው ፖለቲካ ሊለዝብ ይችል ይሆናል።