January 3, 2018 06:14

 

በአቃቤ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ እና የተፈረደባቸው የተለያዩ ፖለቲከኞች እና ሌሎች ግለሰቦችም የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 25 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቀመንበሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመንግስት የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በመግለጫው ላይ ከተነሱት፦
“የህዝባችንና የወዳጆቻችንን ስጋት እየቀረፍን የጠላቶቻችን ከንቱ ምኞት፣ ድባቅ እየመታን ለዚሁ በቅተናል። ለውድቀት የታጨን አይደለንምና ለጊዜው ባጋጠመን ተግዳሮች ውስጥ እንኳ ብናልፍ በአሸናፊነት እንወጣለን።”
“በአቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ እና የተፈረደባቸው የተለያዩ ፖለቲከኞችም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስነኗል::”
“በደርግ ዘመን በምርመራ ስም ልዩ የጭካኔ ተግባር ሲፈጸምበት የነበረውና በተለምዶ ማዕከላዊ በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማእከል እንዲዘጋ ተደርጎ ሙዝየም እንዲሆን ተወስኗል።
በምትኩ “በዓለም አቀፍ ደረጃ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር መሰረት አዲስ የምርመራ ተቋም ተቋቁሞ በሌላ ህንፃ ስራ ጀምሯል።”