January 3, 2018 Share
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ሰላም በልልኝ እንዳትሉኝ። ሌቤ እንጂ አካሌ ገና የጀግኖቹ መንደር አልደረሰም። አዎን! “በልብ ዉስጥያለ ሕልም አንድ ቀን ዕውን ይሆናል” ሲል ፅፏል ሪቻርድ ጎርደን። የዛሬ ሃያ ዓመታት ገደማ ሂዉስተን የሚገኘዉ ናሳ (NASA) የመንኮራኩር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ለጉብኝት ሄጄ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥ ያነበብኩት አባባል ነው። ሪቻርድ ጎርደን የአፓሎ ጠፈርተኛ የነበረ ሲሆን ጠፈር ላይም ሁለት ጊዜ ተራምዷል። ከኢራቁ ጦርነት በኋላ የበለጠ ዕውቅናን ያገኘዉ አሜሪካዊው ጀነራል ኮሊን ፓዉልም “ሕልም በተዓምር እዉነታ አይሆንም። ይልቁንም ዉሳኔንና ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል” ሲል ፅፏል። አምላክ የዉሳኔና የተግባር ሰዉ ያድርገን(ኝ)።
ወደ ሙታኖቹ ህወኣቶች ልመለስ። የተመኙት ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ቢሆንም የደደቢት ሙታኖች የነጣጥለህ ግዛ ሕልማቸዉን ዕዉን ይሆን ዘንድ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የጣዕረ ሞት መግለጫቸዉን ከጥቂት ቀናት በፊት አንብበዉልናል። በእዉነቱ ከሆነ መግለጫዉን በጣም ወድጀዋለሁ። ሁሌም ልቡ ለሚዋልልበትና ዘወትር የሙሉቀን መለሰን ናኑ ናኑ ነይ መጫዎት ለሚወድ ተላላና ፈሪ ተቃዋሚ ተብዬ መላወሻ ያሳጣ በመሆኑ ይመስገን ብያለሁ። ‘አንተ ትምክተኛ አማራ…… አንተ ጠባብ ኦሮሞ …..ከወደድክ የትግሬን የበላይነት ተቀበል አለበለዚያም ገደል ግባ’ የሚል በመሆኑ እኔን ተመችቶኛል። ተመስገን ደሳለኝ እንዳለዉ ‘የፈራ ይመለስ’ ብቻ ሳይሆን ዝም የሚል ይመለስ ያስብላል። ስለዚህ ተወደደም ተጠላም ህወኣት በኢትዮጲያ ሕዝብ ላይ ጦርነትን ማወጁን መቀበል አለብን። አለበለዚያ ጥቁር አፍሪካዊያን ከዓመታት በፊት ከጫንቃቸዉ ላይ አዉልቀዉ የወረወሩትን የባርነት ሰንሰለት ተቀብለን የዘመኑ ባሪያዎች ለመሆን የመረጥን መሆኑን እንመን። መልስ መስጠት የሁሉም ኢትዮጲያዊ ግዴታ ነው። ጥያቄዉ ባርነት ወይም ነፃነት ነዉ። ዝምታ ባርነትን መምረጥ ነዉ።

ከአስራ ሰባት ቀናት ጭቅጭቅ በኋላ ህወኣት ‘የምታመጡትን አምጡ’ በማለት ሁለቱ ታላላቅ ብሔሮች ላይ አላግጧል። ከዓመታት በፊት እራሱ ጠፍጥፎ የሰራቸዉ አህያና ፈረሶቹ ሰዉነታቸዉ ከተቀበረበት ሕይወት ቢዘራ ከበረት አምልጠዉ መጋለብ ጀመሩ። ሰዉ ሰዉም ሸተቱ። ፍቅርንም ተነፈሱ ። የህወኣትን እርኩስ መንፈስንም አሰቃዩ። ሊሸነፍ የማይችልንም አብሮነት ዘመሩ። ህወኣትም ደነገጠ ። መሸነፉንም በመግለጫዉ አመነ። መቆሚያ መቀመጫ ቢጠፋዉም በኢትዮጲያዊ ልብ ዉስጥ የሞተዉን ፓለቲካዊ ሕይወቱን የሚዘራ መስሎት የንፁሐንን ሕይወት ለመቅጠፍ ተዘጋጅ። እንግዲህ እኛም ያለን አማራጭ እንደ ፍቅር እስከ መቃብሩ ተበጀ በለዉ እምቢ ብሎ በጊዜዉ አይደፈር የተባሉትን ማንበርከክ አልያም ማንነትን ተቀብሎ ሙኩትና ምርጥ ምርጡን ለሙታኖች የሚያቀርብ ሎሌ መሆን። ለሁላችንም ምርጫዉ ከሁለት አንዱ ነዉ። አዎ ዝምታ ሎሌነት ነዉ።
ህወኣት ለዘመናት የሚጠየቅበትን ምርጫ በግልፅ ነግሮናል። በቄሮዎች ይሁን በፋኖዎች …በአርበኞች ግንቦት ሰባት ይሁን በዉስጥ አርበኞች …..በኦሮሞዉ ይሁን በአማራዉ …..በወለጋ ይሁን በአምቦ……በጎንደር ይሁን በሐረርጌ ለሚጠፋዉ የማንም ኢትዮጲያዊ ሕይወት (ትግሬንም ጨምሮ) ተጠያቂ ነዉ። ይህን ያልተረዳ ካለ ወይ የዋህ ነዉ አልያም ፈሪ ነዉ ካልሆነም በአንፃራዊ ሰላም ተብዬ ስም ከሰዉ በታች ሆኖ ለማደር የመረጠ አስመሳይ ነዉ ፤ አለበለዚያም ትግሬ ነዉ። ለአባባሌ ማንንም ይቅርታ አልጠይቅም። ‘የትግሬ የበላይነት ወይንም ሞት!’ ብለዉ ያለሕግ ሊያንበረክኩንና ሊገድሉን ለመረጡ የደደቢት አናሳዎች ‘ኢትዮጲያ ወይም ሞት’ ብለን ብዙሃንነትና ሰፊነት ጎርፍ ሆነን መልስ በመስጠት ሲተኩሱ ተኩሰን ልንጠራርጋቸዉ ይገባል። አዎን! ለነፃነት መቆምን ካስፈለገ ማንኛዉንም መስዋህትነትን ለመክፈል መቁረጥ አለብን። ስለዚህ ከእንግዲህ በኋላ ምርጫዉ የእያንዳንዱ ኦሮሞና አማራ እንዲሁም ተበድያለሁ ብሎ ያመነ መላዉ ኢትዮጲያዊ በሙሉ ነዉ።
ስብሰባና ተዐድሶ የሚባሉት ማስመሳዬች ማብቃታቸዉን መግለጫዉ አብስሮናል። አንዴና ለመጨረሻ ጊዜም አክትመዋል። ወደድንም ጠላንም ‘የኢትዮጲያ’ የሚባል መንግስት የለም። ከትግራይ በመጡ ዘረኞችና የእርኩስ መንፈስ ማደሪያዎች ተቀፍድዳ የተያዘች ሀገርና ሕዝብ ጦርነት ታዉጆበት ግን አለ። ስለዚህ ምርጫችን በአንድ ወቅት ለኤርትራዊያን የቀረበ ዓይነት ነው። ነፃነት ትፈልጋለህ ወይስ አትፈልግም?
ኒዉስ ዊክ በኖቨንበር 2015 እትሙ ‘የነፃነት ታጋይን እንዲታገል የሚያደርገዉ ምንድን ነዉ?’ ሲል በሚጠይቅ ርዕስ በአሁኑ ሰዓት እያንዳንዳችን ኢትዮጲያዉያን ልንመልሰዉ የሚገባ ጥያቄ አቅርቧል። እንዳርጋቸዉ ፅጌንና ብርሃኑ ነጋን ወደ ትግል ሜዳ ሄደዉ ነፃነትን ይሹ ዘንድ ምን አስገደዳቸዉ? …… ሁለቱን ወንድማማቾች (መንግስቱ ነዋይና ገርማሜ ነዋይ) በቃ ከንጉሱ ስልጣን በላይ ነፃነቴን ይሉ ዘንድ ምን አደረጋቸዉ?…… ከመኳንንት መሃዕድ በላይ የመኳንንት ዉብ ልጅ ለጋብቻ የተቸረዉ ያ የኮሶ ሻጭ ልጅ ነፃነት ወይም ሞቴን ይል ዘንድ ምን ገፋፋዉ?…. እስክንድርን ……አንዱዓለምን…… መረራ ጉዲናን …….በቀለ ገርባን ……ርዕዬት ዓለሙን …..ሲሳይ አጌናን …..ኦልባና ሌሊሳን ነፃነቴን ብለዉ በደልን ይቀበሉ ዘንድ መምረጣቸዉ ከብዙዎቻችን የተለየ ምን ቢኖራቸዉ ነዉ? ይህን ሁላችንም እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል።
ነፃነት ነፃ አይደለም ይባላል። ነፃነት በርካታ ሚሌዬኖችን በፈረንሳይ ፣ በሩሲያ፣ በአሜሪካንና በበርካታ ሀገሮች እምሽክ አድርጓል። በአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ብቻ (American Civil War) የትግራይን አንድ እምስተኛ የሚሆን ሕዝብ ተገድሏል። ጦርነት አስከፊ ቢሆንም የሰዉ ልጅ ይዋል ይደር እንጂ የራሱን ሕይወት ጨምሮ ማንኛዉንም ነገር ለነፃነት ሲል ይከፍላል። ተታሎ ይባል እንጂ አዳም ከሄዶም ገነትም የወጣዉ ለነፃነቱ ሲል ነዉ።
የአስራ ዘጠኝ ዓመቱ የዩክሬን ተወላጅ ‘ሩሲያዎችን ለቤቴና ለተወለድኩባት ምድር ስል ልታገላቸዉ ጠመንጃዬን አንስቻለሁ። ያለነፃነት የማንም የበታች ሆኜ ከምኖር ሞትን እመርጣለሁ”ሲል መልሷል ለኒዉስ ዊክ ጥያቄ። አያይዞም “አሁን ሰላም ሳይሆን ነፃነት ነዉ የምንፈልገዉ። ሰላም ከነፃት በኋላ ይመጣል” ብሏል። የሰባ ሰባት ዓመቱ ቲቤታዊም የቀድሞ ምንኩስናዉን ጥሎ እንዴት ጠላቶቹ ቻይናዊያንን ሊዋጋ እንደወሰነ ሲናገር “ቻይናዉያን ሴቶቻችንን ሊደፍሩና እኛን የበታች አድርገዉ ሊገዙ ነዉ የመጡት። ስለዚህ መዋጋት የግድ ነዉ። ቄስ ስለነበርኩ በመጀመሪያ ቃታ ስቤ ቻይናዊ ለመግደል ተቸግሬ ነበር። እየቆየ ግን ግፍ ሲበዛ መግደል መጀመሬን ወደድኩት። እነሱ ከመግደል አይታቀቡም። ስለዚህ እኔም ለሀገሬና ለሕዝቤ ስል መግደል አማራጭ የሌለዉ መሆኑን ተቀበልኩ። በኋላም እነሱ ከገደሉት በላይ መግደል ጀመርን። ብዛታቸዉ ግን እንደ ጉንዳን ሰለነበር ተቸገርን ” ብለዋል።
ብዙ የስነ ልቦና ሙሁራን ነፃነትን የቀመሰ ብዙ ይርበዋል ሲሉ ይደመጣሉ። ታዲያ እኛ ኢትዮጲያውያንን ገዢዎቻችን ለዘመናት አኮላሽተዉን ይሁን እፍኝ በማይሞሉ የደደቢት ደደቦች ለዚህ ሁሉ ዓመታት አንገት ደፍተን መኖራችን? ወይስ ብዙ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸዉ ፅጌዎች ስለሌሉን? ደደቢቶች በግልፅ ቋንቋ ተናግረዋል። የአባቴ የስጋ ዘመዶችን (ኦሮሞዎች) አእህያና በቅሎነታቸዉን እስከተቀበሉና የሚሰጣቸዉን ፍርፋሪ በፅጋ ተቀብለዉ ሆዳቸዉን እንደ አባ ዱላና ዲሪባ ኩማ እስከሞሉ ድረስ በሰላም የቤት ዉስጥ አሽከር ሆነዉ መኖር ይችላሉ። የእናቴ የስጋ ዘመዶችም (አማሮችም) እንደዛዉ። እኔም ብሆን የዳያስፓራ ኢንቨስተር-ተብዬ የተማረ አሽከ። አበቃ!! ስልቻ ቀልቀሎ።ቀልቀሎ ስልቻ ።
ምርጫዉ የእያንዳችን ነዉ።
