ለአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ኢትዮጵያውያን በግንቦት ሰባትና የድርጅቱ ልሳን ነው ብለው ባመኑበት ኢሳት ሚዲያ ላይ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ግንቦት ሰባት ለአማራው ምንም ሳይፈይድለት አማራው ግን በግንቦት ሰባት ስም በማያውቀው ድርጅት ስም በወያኔ እየታደነ ፍዳውን እያየ ነው የሚል አቤቱታ ከማቅረብ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራሮች በከተሞች በሚኖሩ የአማራ ሕዝቦች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈፀም እያነሳሱ ነው ሲሉ ይከሳሉ።

የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪዎቹ እንደሚሉት አማራን አገለለ ካሉት የሽግ ግር ወቅት ቻርተር ተቃውሞ የቀጠለው ግንቦት ሰባት ያልበሰሉ ካድሬዎችን በስድብ ላይ በማሰማራት እንዲሁም ከሻእቢያ የሚሰጠውን ፀረ አማራ ፕሮፓጋንዳ በመያዝ በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል እንዲፈፀም ለወያኔ ድጋፍ ሆኗል ሲሉ ይወነጅላሉ። በኢትዮጵያ የ አማራ ተወላጆች ከግንቦት ሰባት ጋር ንክኪ አላቹህ በሚል በአሸባሪነት መከሰሳቸው ሲታወቅ ወያኔ ሕዝቡን ለማጥመድ ያመቸው ዘንድ ግንቦት ሰባት የተባለውን ድርጅት በአሸባሪነት የአዋጅ ነጋሪት ጎስሞበታል፤ ይህንንም ተገን አድርጎ የ አማራውን ሕዝብ በግንቦት ሰባት ስም እየጨፈጨፈ ይገኛል።

የ አማራውን ሕዝብ ትግል ለመንጠቅ የትግል ሽሚያ ያደርጋል ብለው የወነጀሉት ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ግለሰብ አዲስ አበባ ከ አማራ ክልል በመጡ አማሮች ተወላለች ማለታቸው ከቀድሞ የባሰሰ ጥርስ መነካከስ ላይ ሲደርስ የሕወሓት የደህንነት ተላላኪ ነው የሚሉት ግለሰብ በኢሳት ላይ ቀርቦ የሚያራምደው ሃሳብ ጸረ አማራ ነው ሲሉ ይናገራሉ።

ሰሞኑን ኢሕ አዴግ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ባወጣው መመሪያ መሰረት ኢሳቶች ህወሃትን አቅጣጫ እያስያዙት ነው ሲሉ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪዎቹ ይወነጅላሉ። ወቀሳቸውንም እንዲህ በማለት ይገልጻሉ

የአቶ ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ ለብቻው መታየት አለበት ። ህወሃቶች መግደል የለባቸውም ከተባለ ለሌላውስ የመግደል መብት አለው ያለው ማን ነው ሲሳይ አጌና ፥ ልብ በሉ ወያኔ ኮሎኔል ደመቀ ላይ ሰው በመግደል ወንጀል ብሎ ያቀረበው ክስ ራሱን የመከላከል ርምጃ በመሆኑ ተብሎ ውድቅ ተደርጏል

ኤርትራ ውስጥ የመሸገ የታጠቀ ሃይል ባለበት ሁኔታ ህወሃት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መፍታት ለነሱ ሞት ነው ተብሎ ሊወሰድ አይችልም፡ መሳይ መኮንን

አቶ ደመቀ ዘውዱን መልቀቅ ለህወሃት ብቻ ሳይሆን በትግራይ ህልውና ጋ ይያያዛል ። አሁን ያለውን ውጥረት የበለጠውኑ የሚያጠናክር ነው ። የአቶ አንዳርጋቸውንም ጉዳይ በዚሁ ነው የማየው ። ኤርሚያስ ለገሰ

አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ አይፈልጉም ብያችሁ ነበር ። አቶ ደመቀም የአማራን ትግል ሊመራ ይችላል ብለው የሚሰጉበት ግለሰብ ነው ። https://www.facebook.com/ESATtv/videos/1762299330468808/?hc_location=ufi

 

በተከታታይ ወቀሳዎች ቢኖሩም የተለያዩ ተቃውሞዎች በአማራ እክቲቭስቶች ቢቀርቡም ከኢሳት ጋዜጠኞች የተለየ ምላሽ እስካሁን አልተሰማም። የግንቦት ሰባት ካድሬዎች ከፍተኛ ንቀት የተቀላቀለበት ስድብና ትችት በ አማራ ተቆርቋሪዎቹ ላይ ማሰማታቸውን መቀጠላቸውን ተነካን ያሉ አክቲቭስቶች ይናገራሉ ። ከዚህ ቀደም ጃዋር መሃመድ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ መብት ሲቆረቆር የሚያንቋሽሹትና ምንም አያመጣም ሲሉ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ጃዋር ከደረሰበት ነገም ያልተደራጁት የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪዎች ከሚደርሱበት ታጋይነት ማንም ሊያግዳቸው አይችልም ሲሉ የአማራ ብሄርተኞች ይናገራሉ።

Konjit Sitotaw