Saturday, 27 January 2018 12:04
Written by  አለማየሁ አንበሴ
 በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ቫግነር ጋር መወያየታቸው ታውቋል፡፡

ዶ/ር መረራና አምባሳደር ቫግነር በጀርመን ኤምባሲ ጽ/ቤት ሐሙስ ባካሄዱት ውይይት፤ በሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮችና በእስረኞች መፈታት በስፋት መወያየታቸውን ሂደቱን የተከታተሉ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡ዶ/ር መረራ ከእስር በመፈታታቸው ሀገራቸው ደስታ እንደተሰማት የጠቆሙት አምባሳደሯ፤ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ለሚያደርጉት ትግል አክብሮት እንዳላቸው ገልፀውላቸዋል፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ ጀርመን ከታሰሩ ጀምሮ ጉዳያቸውን በመከታተል ላደረገችው አስተዋፅኦ አመስግነው፣ በኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት መጎልበት የሚደረገውን ጥረት መደገፏን አጠናክራ እንድትቀጥል መጠየቃቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡