ቢቢሲ

ቢቢሲ ከወራት በፊት ለኢትዮጵያና ለኤርትራ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በትግርኛ የድረ-ገፅና የፌስቡክ ገፅን በመክፈት ዜና፣ ወቅታዊ ጉዳዮችንና ሌሎች መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ከሰኞ ጥር 21/2010 ዓ.ም ጀምሮ በሦስቱም ቋንቋዎች የሬዲዮ ስርጭት ይጀምራል።

የቢቢሲ የሬዲዮ ስርጭት ከሰኞ እስከ አርብ ከምሽት 2፡30 እስከ 3፡30 የሚቀርብ ይሆናል።

በዚሁ መሰረት ምሽት ከ2፡30 እሰከ 2፡50 በአማርኛ

ከ2፡50 እስከ 3፡10 በአፋን ኦሮሞ

ከ3፡10 እስከ 3፡30 በትግርኛ

ዜናና ወቅታዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ። ሦስቱም ቋንቋዎች በየክፍለ ጊዜያቸው ማጠናቀቂያ ላይ ያሉትን አምስት ደቂቃዎች ጠቃሚ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ዝግጅት ይኖራቸዋል።

እርስዎም የቢቢሲ አማርኛን ድረ-ገፅና የፌስቡክ ገፅን ከመጎብኘት በተጨማሪ የሬዲዮ ስርጭታችንን እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል። እንዲሁም ለወዳጅ ለዘመዶችዎ ቢቢሲ አማርኛ የሬዲዮ ስርጭት ሊጀምር መሆኑን ይንገሩ።

ቢቢሲ አማርኛን በሬዲዮ ለማድመጥ

በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ምሽት ከ02፡30 እስከ 02፡50 በአጭር ሞገድ በ7595፣ 11720 እና 12065 ሜጋ ኸርዝ

በድጋሚ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ምሽት ከ03፡30 እስከ 03፡50 በአጭር ሞገድ በ9855 እና 15490 ሜጋ ኸርዝ

እንዲሁም በሳተላይት

በአረብሳት (ባድር4) – 11.966 GHz፣ ሆሪዞንታል – ትራንስፖንደር 15

በናይልሳት 201 – 11.843 GHz፣ ሆሪዞንታል – ትራንስፖንደር 7

በሆትበርድ 13D – 12.597 GHz፣ ቨርቲካል – ትራንስፖንደር 94 ስርጭቱ ይተላለፋል።

ምንጭ     –    ቢቢሲ አማርኛ