January 28, 2018

ስለወያኔ ብዙ አወራን፡፡ ብዙ የሚያወሩም ከተራ እስከ ምሁር የመገናኛና ማሕበራዊ ገጾችን ሞልተው እንሰማቸዋለን፡እናያቸዋልን፡፡ ይህ እንደ አሸን የሞላን የወሬ ቡደን ብዛት ለወያኔ እንደጥሩ መሳሪያ እያገለገለ ያለ ግብዓት እንጂ ስጋቷ አደለም፡፡ አንድ ተራ ሰው በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን  አድርጎ በተራ አስተሳሰብ ሲያጉር ይውላል፡፡ ይህ ሁሉ ወሬ ተናጋሪ ሲኖር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ሊታደግ የሚችል አንድ አነስተኛ ግን ቁርጠኛ ሆኖ አሁን ያለውን የሕዝብ ኃይል በማቀናጀት ወያኔን ከግብዓተ ቀብር ሊያደርስ የሚችል አካል ጠፋ፡፡ ተቃዋሚ ተብለው የሚጠሩትን ታዘብን፡፡ በሕዝብ እልቂትና ሥቃይ ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ዋና ተቃዋሚ ለመሆን እንጂ አንድም ቁርጠኛ የሆነ እርምጃ ሲወስዱ አናይም፡፡ አንዳንዶች ተቃዋሚ ነን የሚሉትም በእጅ አዙር የወያኔ ተቀጣሪ የሆኑም አልጠፉም፡፡ በተመሳሳይ የወያኔ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሚመስሉ የሚዲያ ዲስኩረኞችም ሆን ብለው ወሬዎችን ወያኔን እድሜ በሚሰጥ መልኩ ከሌሎች ቀድመው በመንዛት መደረግ ያለበትን እንዳይደረግ በውዥንበር ለማኖር ተሰልፈዋል፡፡
አሁን በአለው ሁኔታ ወያኔን መጣል የከበደው በወሬ ብዛት ስለደነዘዝን ማሰብ ስላአቃተን እንጂ ወያኔ ያለችበት ሁኔታ ጠንክሮ አደለም፡፡ እስካአሁን ገዳይ አጋዚዋን ትተማመን ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን ሕዝብ እሱንም እንደማይፈራውና ከጊዜ ወደጊዜም በገዳዩ ላይ ራሱ ጥቃት ማድረሱን እየጨመረ ስለሆነ የሆነ ቦታ ሲደርስ መከላከያ የተባለው ውስጥ የታመቀው አድፍጦ የተቀመጠው ቦንብ እንደሚፈነዳ ወያኔ ገብቷታል፡፡ በየ አገሩ ያለ ኢትዮጵያዊ በዘረኞችና ወሬኞች መርዝ ደንዝዞ በአገር ቤት ምን አስተዋፅዖ እንደሚኖረውም እየገባው አደለም፡፡ በየቀኑ ወሬ ይፈጥሩለታል እሱኑ ሲያራግብ እንዲሁ እድሜ ይጨርሳል፡፡ አጋጣሚውን ነጋዴዎች ይጠቀሙበታል፡፡ የመገናኛ ብዙሀን የሚባሉት የማህበራዊ ገጾችን ጨምሮ በሚፈጥሩት ወሬ ምን ያህል ሰው እንደሳቡ እንጂ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ ምናቸውም አደለም፡፡ ቀን ከቀን ሩጫቸው ምን ያህል ሰው ላይክ አደረገ፣ ምን ያህል ሼር፣ …. በሚል ከዛ የሚገኘውን ልቅምቃሚ ጥቅም ለማግኘት የችርቻሮ ንግድ ላይ ስለሆኑ አገርና ሕዝብ አይታሰቡም፡፡
ሌሎች ደግሞ አገር ቤት ያለውን ትግል እናግዛለን በሚል ከሕዝብ ገንዘብ መሰብሰብን እንደ ልዩ ንግድ የያዙት ትንሽ  አደሉም፡፡ ሌሎች እርስ በእርስ የግል ቅራኔን ሳይቀር በትልቁ በማግዘፍ ለሌላው በማድረስ በእነሱ ተራ የግል አተካራ ብዙውን እንዲሳተፍ ማድረግን እንደልዩ ጸጋ የቆጠሩት አሉ፡፡ ብቻ ምን አለፋን አገርና ሕዝብን ያለ አንደም አካል በመጥፋቱ ወያኔ አሁንም ለመኖር እድል ኖሯታል፡፡
ሰሞኑን የብሮድካስት ባለስልጣን የተባሉት ግለሰብ ሲያወሩ መቼም ብዙዎች ሰምታችኋል፡፡ ሲጀምር የብሮድካስት ባለስልጣን ተብሎ የተቋቋመበት ዓላማው ምን እንደነበር አስተውሉ፡፡ ሰውዬው እኛ በነገሮች እንደነዘዝን ስለአወቁ መሰለኝ ለሚናገሩት ነገር ትንሽ እንኳን አያፍሩም፡፡ የኦሮሚያን ቴሌቪዥን የሐጫሉን ዘፈን እንዴት በቀጥታ ለቀቀ ብለው ደነፉ፡፡ ይገርማል! በአማራ ክልልም የቴዲ ዘፈን አንዴት ይዘፈናል፡፡ የእኛን ባንዲራ የሚያብጠለጥለው ቴዲ ሲሉ አላፈሩም፡፡ ወደራሳቸው ሚዲያዎች(ዛሚና፣ ኢኤንኤን) ሲመጡ በሚገርም ሁኔታ የተጠቀሙበት ቃል ምን ያህል አድማጩን ቢንቁት ነው ያሰኛል፡፡ ዛሚና ኢኤንኤን የራሳቸው ጥሩ ነገር ቢኖረውም ሲሉ ነው የጀመሩት፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሚዲያዎች የወያኔ የሽብር ማሰራጫዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የሐጫሉን ዘፈን ሕዝብን ከሕዝብ ሊያጫርስ አሉት እንደውም ከዘፈኑ በኋላም የተከሰተው በማለት ልክ ሐጫሉ በመዝፈኑ ሕዝብ ከሕዝብ የተላለቀ አድርገው ሊስሉት ሞከሩ፡፡ እውነታው ግን የሆነው በተቃራኒው እንደነበር ያውቁታል፡፡ ሐጫሉን ኦሮምኛ የማስሙ ሁሉ ወደ አማርኛ ተተርጉሞላቸው ሰምተውት ብዙ ሕዝብ ደጋግሞ ሲያደምጠው ነበር፡፡ ሐጫሉንም ጀግና በሚል ውዳሴ ሲያወድሰው፡፡ የሐጫሉን ዘፈን በመልካም ግብዓትነቱ ሲተነትኑት ከሰማኋቸው ሚዲያዎች አንዱ የማራ ሕዝብ ራዲዮ የሚባለው ነበር፡፡ ቴዲ አፍሮ የወያኔን የጥንቆላ የአውሩው ምልክት ያለበትን ባንዲራ ያልሆነ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ብቻ የሆነ ባንዲራ ተጠቅሞ ኮንሰርት እንዴት ያስተዋውቃል ነው፡፡ በእርግጥም በማስታወቂያ ብቻም ሳይሆን በኮንሰርቱም ላይ የነበረው ሕዝብ የያዘው  አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ብቻ የሆነውን ባንዲራ ነው፡፡ ሰውዬው አይናቸውን በጨው የታጠቡ ትግሬ ወያኔ ስለሆኑ ንግግራቸው አይገርመኝም፡፡ ሌላም አሉ የአውሬው ምልክት ያለበትን ባንዲራ እንዴት ሲቃጥል ዝም አላችሁ ሲሉም የአማራ መገናኛን ወረዱበት፡፡ ሕገ መንግስቱን (የመለስ የጥንቆላ መጻፍ) ማቃጥል ነው ሲሉም እየተንገበገቡ ተናገሩ፡፡ እንግዲህ ይህን ሁሉ ስንሰማ ሰውዬው የተሰጣቸው መልስ እንዳለ ሆኖ እነዚህን ጉዳዮች ከእንግዲህ አያገባህም ያላቸው የለም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች አንኳን ከራሳቸው መጣ እንጂ አዎ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ የጥንቆላ ሰነድና የሰይጣን ምልክት አይመራም ሊባሉ በተገባ፡፡ አዎ ትግላችንም ለዘመናት ሕገ መንግስቱን ለመናድ እየተባልን የተገደልንበተን ለአውሬው ግብር የተደረግንበትን የወያኔ ሰነድና የአውሬ ምልክት ከነአገልጋዮቹ  ማቃጥል ነው፡፡  በቃ አላማችን ይሄው ብቻ ነው፡፡
ሌላው ብዙ ተቃዋሚዎች ድርድር ምናምን ይላሉ፡፡ የሚገርም ነው፡፡ ለመሆኑ ድርድሩ አሁም ጫፍ የደረሰው ን የሕዝብ ትግል በድርድር ስም ወደኋላ ለመመለስና ለወያኔ ትንፋሽ ለመስጥት ነው ወይስ ወያኔን አያውቁምና የሕዝብና አገርን ጥያቄ ለመመለስ? እንኳን ድርድር ወያኔ ራሷ ጨንቋት የፖለቲካ እስረኛ እለቃለሁ ባለችበት አሁንም በሌላ መልኩ ሕዝብ የተዘናጋላት መስሏት በየቦታው ምን እያደረገኝ ነው፡፡ በእርግጥም በክልሎች አካባቢ ያለው እንቅስቃሴ ከመግለኛው በኋላ  የመዘናጋት ነገር ታይቶበታል፡፡ ይሄ ነበር የወያኔ አላማ፡፡ ኦቢኤንና አማራ መገናኛ ኢላማ ተደርገው ነበር፡፡ እንደሰማችሁትም የብሮደካስቱ ባለስልጣን አያፍሬ ንግግርም ወቅት እነዚህ ሚዲያዎች እንዳይገኙ ተደርጎ ነበር፡፡ ዛሚና ኢኤንኤን ግን ዋና ተጋባዥ ነበሩ፡፡
እውነታው ወያኔ አረመኔያዊነትና፣ በአረመኔያዊነት ሕዝብን በማሸበር ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት አቅም ኖሯት ለዚህን ያህል ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ እድል ኖራት እንጂ እኛ አንድ ብንሆን አቅሟ ከሳምን ከዚያም በታች ሊሆን በቻለ፡፡ ልብ በሉ ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምራ እጅግ አረመኔ የሆነ ቡድን መሆኗን በትግራይ በባዶ ስድስት፣ ከሌላው አረመኔ ኦነግ ጋር በመተባበር በበደኖና በአርባጉጉ በአማራው፣ በጉራፈርዳም ያው ነው፣ በሱማሌ (የኦጋዴ አማጺ በሚል)፣ የአብዲ ኢሌን የሽብር ቡድን በመፍጠር ብዙ ዘግናኝ  ግፍ፣ ይሄው የአብዲ ኢሌ ወያኔ የዘጋጀችው ገዳይ ቡድን አብዲ ኢሌን ከፍ በማድረግ ዛሬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየሆነ ያለውን ሁሉ ወያኔ አለኝ የምትለው ስልት ነው፡፡ በጋምቤላም እንዲሁም በየጊዜው በተለያዬ በኢትዮጵያ ከተሞች አጋዚ በተባለው ሰው በላ ቡደኗ ወያኔ አረመኔያዊነቷን እያሳየች የተፈራች ሆና ለመኖር ነው፡፡
ድሮም የሚመራው አጥቶ እንጂ ወያኔን እንደጉድፍ የሚያየው የወሎ ሕዝብ ሰሞኑን የደረሰበትን የወያኔ አረመኔያዊ ተግባር ተንተርሶ አሁን እልህ ገብቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ሰላማዊ ሰለፍ የሚባል ተቃውሞ አያስፈልግም፡፡ ውጤት ያለው የወያኔን የጥንቆላ ሕግና ተዋናዮቹን ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ እንጂ፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ! አሜን!