29 January 2018

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ለሳምንት የዘለቀው ግጭት ቀጥሎ ከጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ እየተደረገ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቶችና መንገዶች መዘጋታቸውን ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አላካት ወደ ከተማው ሲገቡም ተስተውሏል፡፡ በወልዲያ ከተማ የሚሠሩ አንድ መምህር ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና እንዲሰጥ ታቅዶ የነበረው ከሰኞ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም በአመጾቹ ምክንያት ፈተናዎቹ የመሰጠታቸው ዕድል  አናሳ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ከየትምህርት ቤቱ እየወሰዱ መሆኑንም መምህሩ ተናግረዋል፡፡