ልዑል ዶ/ር አስፋ-ወሰን ዓሥራተ ካሣ፤ የአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች አማካሪ፣ ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ፤ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ያላቸውን ሥጋትና ተስፋ ያንጸባርቃሉ። አማራጭ የሚሏቸውን የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ።
መንስዔ – በዘር ላይ የተመሠረተ የፌዴራሊዝም ሲስተምና ለብሔራዊ ዕርቅ ምላሽ መንፈግ፤
ሥጋት – ሁላችንም ተሸናፊ ሆነን የምንቀርበት ጊዜ እንዳይመጣ፤
መፍትሔ – መንግሥት ችግር መኖሩን አምኖ ተቃዋሚዎችንና ግለሰቦችን ሰብስቦ በራሱ ፈቃድ አዲስ ሁኔታ የሚፈጠርበትን መንገድ ማድረግ አለበት፤
ተስፋ – የክርስቲያንና የእስላም አንዱ ኢትዮጵያ እንደገና እንድታሸበርቅ ያደርጋታል ብዬ በፅኑዕ አምናለሁ።
https://youtu.be/dVehBgfBmik