January 29, 2018
ሀገርን መከፋፈል እንዲሁም መገንጠል የሚችሉት ፖለቲከኞች ወይም ነን ባዮችና የዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ ካድሬዎች ናቸው።ሕዝብ በሀገሩ ዕጣ ፈንታ ላይ ወስኖ እያውቅም። ለዚህ ሻዕቢያና ወያኔ ቁንጮ ምሳሌ ናቸው። ሻዕቢያ ኤርትራን አስገንጥሏል። የኤርትራ ሕዝብ በዚህ ውሳኔ ላይ ነፃነት ተሰጥቶት አልወሰነም። ጀበኻና ሻዕቢያ የነበሩ የኤርትራ ክፍለሀገር ተወላጅ ኢትዮጲያዊያን ስንት ነበሩ? ሁለቱ ሽፍቶች በርግጥ ሕዝባዊ ውክልና ነበራቸው ወይ?
እነርሱ ወንበዴ ሐሳብ አፈለቁ፣ ወንበዴነታቸውን ነዙ፣ የገዛ ወገናቸው ላይ ጦር መዝዘው እየገደሉ…ኤርትራን በህወሓትና አሜሪካ አስተባባሪነት ገነጠሉ። የሻዕቢያ ባሪያ ወያኔዎች በበኩላቸው በተመሳሳይ ቋንቋ የሚሰበከውን ሸፍጥ ሲሰሙ ያደጉ፣ እነደ እነ ወዲ አፎምን መሆን የሚፈልጉ ነበሩ። የአሉላ አባነጋን ኢትዮጲያዊ ገድለ ታሪክ ሳይሆን የእነ ኢሳያስ አፈወርቂን የአፍራሽነት ትርክት ጭራ ሆነው ተከተሉ። መለስ ዜናዊ “ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?” ሲባል “ኢሳያስ አፈወርቂን” ይል ነበር ብለው የሚሳለቁበትም በዚህ እውነት ምክንያት ነው። በአንድ ወቅት በተደረገለት ቃለ ምልልስም ይህን አረጋግጧል። ከኢሳያስ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ማሳለፍ ብዙ መጽሐፍ ማንበብ ነው ሲል።
እነ መለስ ሻዕቢያን መከተል ብቻ ሳይሆን ሸፍተው የሻዕቢያ አመራሮች ተልዕኮ ፈጻሚ በመሆን የትግራይን ወጣት አብረኸን ሸፍት እያሉ እስከመግደል ደረሱ። ያ ጭካኔ ለዓላማቸው ማሳኪያ ስላልበቃ “ሓውዜን መሽገናል” ብለው ለደርግ የተሳሳተ መረጃ እንዲደርሰው በማድረግ ሕዝቡን አስጨፈጨፉት። ዓላማቸው ተሳካ። ትግራይን ገነጠሉ።
ነገርግን የተገነጠለች ትግራይን ስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ሲያስቧት ደነገጡ:: በኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው
ቢገነጠሉ እንደሚሻል አሴሩ። ከኢትዮጲያ ከተገነጠሉ ለአለቆቻቸው ሻዕቢያዎች ጠቃሚ እንደማይሆንም ቁንጥጫ ደረሳቸው። የኢትዮጲያ አንጡራ ሀበትን ማጓጓዣ ድልድይ ይጠፋል። አቶ ኢሳያስ ለኢሳትም ሆነ ለኦ.ኤ.ምኤን ከሰሞኑ ባደረገው ቃለምልልስ “ህወሓት ትግራይን እንዳይገነጥል የመከርነው እኛ ነን” ሲል እርሱ እንደሚለው ለኛ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ረጅም ና ዘለቄታዊ ጥቅም ብቻ እንደሆነ ይገባኛል። እንደዚያ ካልሆነ ኤርትራን የገነጠለ ሰውዬ “ትግራይ እንዳትገነጠል ያደረግነው እኛ ነን” ሲል ደንቆሮ ሆኑልኝ እንደማለት ነው::
ይሁን እንጂ የህወሓቶች ከሻዕቢያ ጋር የነበረው የአለቃና ምንዝር ግኑኝነት ሌላውን ኢትዮጲያዊ እየመዘበሩ አቅም ሲያገኙ ጌቶቻቸው ላይ አሳመጻቸው። የሚጓጓዘው ጤፍ፣ቡናና ወርቅ ወደ ኤርትራ ሳይሆን ወደ ትግራይ ዞረ።ከዚያም በላይ ትግራይ ባላት የተፈጥሮ ሀብት ራሷን እንደማትችል ስለተገነዘቡ ሳይገነጠሉ ኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው ለትግራይ የሚሆን መሬት ከአጎራባች ክፍለሀገሮች ለምሳሌ ወልቃይት፣ ራያና ቆቦ ከአማራ፣ ጨውና ማዕድን ያለበት የአፋር አካባቢ ላይ ዐይን ጣሉ፣ ከቤንሻንጉልም እንደዛው መሬት እየወሰዱ መበልጸግን መረጡ። ቤንሻንጉል ውስጥ በሱዳን ድንበር ላይ ያለውን የዕጣንና የጥሬ ዕቃ ንግድ እንዲሁም ኢንቨስትመንት ላይ ማን እንደተሰማራ ወደዚያ ተጉዛችሁ አረጋግጡ ወይም የአካባቢው ነዋሪ ጠይቁ:: የእርሻ መሬትንና የተፈጥሮ ሀበትን ምንጭን ጥያቄ በዚህ ሁኔታ በማሳካት ትግራይን በኢንዱስትሪ ማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ በመስማማት ተግባራዊ አደረጉ። አዜብ መስፍን ሟች ባሏ በተለያት ማግስት መለስ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል አደረጋለሁ ብሎ ሕልሙን ሳይጨርስ መሞቱ እንዳንገበገባት መግለጿ ለዚህ ማረጋገጫ ነው። ሕልሙንም ከግብ ለማድረስ በገባችው ቃል መሠረት በርካታ የኢንዱስትሪ ስምምነቶች ከውጭ ሀገር መንግስታትና ድርጅቶች ጋር በመፈራረም ተገባራዊ አደረገች። በላፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ8 በላይ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል፣ ግንባታ ጀመረዋል። ከትግራይ ልማት ድርጅት ኃላፊነት ተባረረች የሚለው የህወሓት የውስጥ ሽኩቻ፣ ምናልባትም እንደታቀደው አልተሰራም ከሚል የዘለለ ሊሆን አይችልም።
እስካሁን በእቅዳቸው መሠረት ዓላማቸውን አሳክተዋል። ኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው ኢትዮጲያዊያንን ከፍለው፣ ሌላ ሀገር ለብቻቸው እየገነቡ ቆይተዋል። ኢትዮጲያ የሚለውን ስም መጠየፍ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጲያን ማንነት ገላጭና ታሪካዊና ባህላዊ እሴትና ቅርሶቿን በነሱ ትርክት ሲቀይሩ፣ሲፈቀፍቁ፣ሲያጠፉ የከረሙበት ምክንያት ይኸው ነው፣ ጥላቻ። ባንዲራው ምስክር ነው። ኦሮሞን ለዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ በሚገባ ተጠቅመውበታል የሀገር ዋልታና ዋርካ ሳይሆን ሁሉጊዜ በተጠቂነት ስሜት እየማቀቀ የበታችነት ስሜት ውስጥ እንዲኖር አድርገዋል::
ለዚህ ሴራቸው እንቅፋት የሆኑትን ሁሉ ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እስከ ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያንን በግፍ እያሰሩ፣ እየገደሉ፣በሐሰት እየመሰከሩ፣ የዝንጀሮ ፍርድ እየሰጡ ሰቆቃ ፈጽመው በአረመኔነት ለመግደላቸው ምክንያት ለዓመታት የሸረቡት ይኸው እኩይ ሴራ ነው::
ነገርግን ፍጻሜው አላምር አላቸው፣ ግፋቸውና ውሸታቸው ሞልቶ ፈሰሰ። “ፈሪ፣ሽንታም ትውልድ” የተባለው፣እየተባለም የተሸናበት ወጣት አንገት ደፈቶ አምቆ የያዘው እሳቱ ፈንድቶ ወጣ። ያቃጥላቸውም ጀመር።
ከ3 ዓመታት በፊት በአምቦ የጀመረው ሕዝባዊ ቁጣ እየነደደ ኮንሶን አዳርሶ በጎንደር አሳብሮ ባህርዳርን አቃጥሎ መርሳ ደርሷል። በነዚህ 3 ዓመታት “አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ ሲወነጀሉ፣ ሽብርተኞችና ፀረ ሠላሞችና ፀረ ልማቶች ሲባል፣ እደገቱ ያመጣው ፍላጎት ነው ሲባል፣ ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል፣ ታችኛውና መካከለኛው አመራር ሕዝብ በድሎ ነው፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ጥልቅ ተሐድሶ …” እየተባለ እነደብረጺዮን “ጥፋተኞች ነን:: እስረኞች እንለቃለን፣ ሀገራዊ መገባባት …” እስከሚለው ሰምተናል። በዚህ ሁሉ የማዘናጊያ ኑዛዜ ውስጥ በ10 ሺዎችየሚቆጠሩትን አስረው፣ ሺህ ዜጎቻችንን እየገደሉ ነው።
ይህም ሆኖ እሳቱ ላይ ቤንዚን አርከፈከፈ እንጂ ሊያጠፋው አልቻለም።ስለዚህ የመጨረሻው ካርድን ለመሳብ እያቆበቆቡ ነው፣”እንገነጠላለን።”
የትግራይ ካድሬዎች “ንብረት ስለወደመ እንገነጠላለን” የምትል ተመሳሳይ ዜማ ይዘው መጥተዋል። የሕዝቡን ልብ ለመፈተሽ መሆኑ ነው። ሆኖም አካሄዱ ይበልጥ አደገኛና የማያስቡት ቅርቃር ውስጥ እንደሚከታቸው አላወቁትም።
27 ዓመታት እንዲነጠል ያደረጉትን የትግራይ ሕዝብ ወደየት ይዘውት ሊሄዱ ነው? ፣ የትግራይ ሕዝብስ እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ ካድሬዎች እስከመቼ ይጋልቡታል?
ከላይ ከኤርትራ ከታች ከአማራ ከጎን ከአፋር ከሁሉም አናድፈውት የት ሊያደርሱት ነው? መልሱ ያለው የትግራይ ሕዝብ ጋር ነው።
ሌላው፣ የህወሓት አፓርታይድ አገዛዝ ሰለባ ኢትዮጲያዊ ግን ግልጽ ጥያቄና መልስ አለው። “የትግራይ ሕዝብ ሆይ እባካህ ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ ደሜን እያፈሰሱ ፣ የልጄን አስከሬን ሜዳ ላይ እየጣሉ ነውና እባክህ አብረኸኝ በቃ በላቸው” እያለ በጨዋነት ይጠይቃል።
ሌላው፣ የህወሓት አፓርታይድ አገዛዝ ሰለባ ኢትዮጲያዊ ግን ግልጽ ጥያቄና መልስ አለው። “የትግራይ ሕዝብ ሆይ እባካህ ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ ደሜን እያፈሰሱ ፣ የልጄን አስከሬን ሜዳ ላይ እየጣሉ ነውና እባክህ አብረኸኝ በቃ በላቸው” እያለ በጨዋነት ይጠይቃል።
“ትግራይን እንገነጥላለን” ሲሉ ለሚያስፈራሩት ካድሬዎቹ “ትግራይን ከገነጠላችሁ እኮ ቆየ፣ ከተለያየን 27 ዓመት ተቆጠረ” የሚል መልስ ይሰጣል። አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል:: እወነታው ይኼ ነው።