የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የሚባል ለክልሉ አልቀረበምደብረፅዮን

የወልቃይት ጥያቄ ተመልሶ አድሯልካሳ ተ/ብርሃን

የወልቃይት ማንነት አልተጠየቀም ከተጠቀ ግን ይመለሳልሀይለማሪያም

የወልቃይት ማንነት ጥያቄ ደረጃውን ጠብቆ መታትየት ስላለበት ወደ እናንተ መርተነዋልያለው አባተ *ፌደሬሽን ም/ቤት)

የትግራይ ክልል የወልቃይት ጥያቄ አልቀረበልኝም ማለቱ ሸፍጥ ነውየትግራይ ክልል ም/ቤት የ2009 ዓ.ም የ6 ወር የስራ አፈፃጸም ሪፖርት

እነዚህ ሁሉ ንግግሮች እና የፅሁፍ ልውውጦች የተፈፀሙት በአንድ በህገ መንግስት እተዳደራለው ብሎ በሚደሰኩር የህገ ወጦች ስብስብ የሆነ አስተዳደር ውስጥ ነው።

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መልኩ ህጋዊ መስመሩን ጠብቆ ተጠይቆ እስካሁንም ግን በህወሃት እብሪተኝነት እና በብአዴን አገልጋይነት ሳይመለስ ለሰዎች እስራት፣እንግልትና ህልፈተ ህይወት እየዳረገ ያለ ጥያቄ ነው።ጥያቄው ቀላል ነገር ግን የማይመለስ መሆኑን በተከታታይ በመሪዎች ንግግር ተመልክተናል።

በዚህ ጥያቄ ምክንያት እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው አማራዎችና ይህ ጥያቄ ለምን አይፈታም ባሉ ሌሎች አማራዎች የስርዓቱ የእስርና ስደት ሰለባ ሆነዋል። ከዚህም በላይ ፋይላቸው ከአመታት በፊት የተዘጉ እና ከግለሰቦች ጋር የማይገናኙ መዝገቦች ሁሉ ተዘጋጅተው የወልቃይት አማራዎች ለማሸማቀቅ ሲከሰሱ እናያለን።

ሰሞኑን አንድ ወዳጀ የደብረፅዮንን ንግግር የሚጣረስ ሰነድ ከትግራይ ክልል ም/ቤት የ2009 ዓ.ም ሪፖርት ላከልኝና የወልቃይት አማራዎች ሪፖርቱን በከፊል ተረጎሙልኝ።

የም/ቤቱ ሪፖርት የሚያሳየው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ተገቢና መመለስ ያለበት መሆኑን፣ ህወሃት ይህ አልቀረበልኝም ማለቱ ሸፍጥ መሆኑን በግልፅ አስፍሯል። የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን ደብረጽዮን በበኩሉ ጥያቄው እንዳልቀረበለት በሚከተለው ንግግሩ ከአመት በፊት መናገረ ይውታወሳል። (የደብረጽዮን Audio ስለሆነ ንግግሩን አድምጡ። https://www.facebook.com/ayalewmenber/videos/1617146935037092/

የምክር ቤቱ ሰነድም ተለጥፏል) ሁለቱንም አያይዣቸዋለው።

“ትግራይ ክልል ናይ ወልቃይት ሕቶ አይቀረበለይን ዝብል ሽፍጥ እዩ። ናይወልቃይት ሕቶ ዋላ 5% አይኹን ንዙይ ዝለዓሉ ሰባት ከምዞሎው ይፈልጥ እዩ፡፡ ፖለቲካሊ ተርእዩ መፍትሔ ክንዲ ምሃብ ብሰላማዊ ሰልፊ ንምዕፍን እዩ ተሞክሩ እዙይ ድማ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ተግባር እዩ። ንዙይ ዘልዓሉ ዝተፈላለዩ ወልቀ ሰባትተአስሮም እዮም። ንአብነት፤ ናብ ፌዴሬሽን ክጠርዑ ዝመፁ ዝነበሩ አብ ፍቸተአሲሮም እዮም ዝብል ብናይ ቢአዴን ብፆት ቀሪቡ እዩ።” ይላል።

ትርጉሙ፡-

“የትግራይ ክልል የወልቃይት ጥያቄ አልቀረበልኝም ማለቱ ሸፍጥ ነው። የወልቃይት ጥያቄ ምንም 5% አይሁን ይሄንን ያነሱ ሰዎች እንዳሉ ያውቃል። ፖለቲካሊ ታይቶ መፍትሄ እንደመስጠት በሰላማዊ ሰልፍ ለማፈን ነው የተሞከረው፣ ይሄ ደግሞ ፀረ ዲሞክራሲያዊ ተግባር ነው። ይሄንን ያነሱ የተለያዩ ግለሰቦች ታስረዋል፣ ለምሳሌ ወደ ፌደሬሽን ሊያመለክቱ ይመጡ የነበሩት ፍቸ ላይ ታስረዋል የሚል በብአዴን ታጋዮች ቀርቧል።”

ከኣብ ፍሉይ ዞባ ህወሓት ቤት ፅሕፈት ናይ 6 ወርሒ 2009 ዓ/ም መደባት አፈፃፅማ ሪፖርት ከገጽ 6 – 7 የተወሰደ

ከሪፖርቱ እንደምናየው የትግራይ ክልል እና የፌደራል ካቢኔ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ላለመመለስ ብዙ ርቀት ተጉዟል። ሰዎችን ከማሰር አልፎ ለመግደል እስከመሞከር ደርሷል። ምክር ቤቱ ካቢኔውን እንደማያዝዘው ግን ይህ ሪፖርት ማሳያ ነው።

ም/ቤቱ ሌላው ያነሳው ነገር የአማራ ገበሬ ከብቱን እየሸጠ መሳሪያ እየገዛ ነው። ይህንን ፈቃድ የሰጠው የአማራ ክልል መንግስት ነው። ይህ ሲሆን ፌደራል መንግስት ምን ይሰራል? ሲል ይጠይቃል።

“የአማራው ገበሬ ከብቱን ሳይቀር እየሸጠ ብዙ ህገወጥ ትጥቅ እንዲገዛና እንዲታጠቅ በክልል መንግስት ፈቃድ ሲሰጥ የፌደራል መንግስት ምን ሲያደርግ ነበር? የፀጥታው ሃይልስ ለምን ዝም አለ? ለምን እጁን አላስገባም”

ሙሉ ሰነዱን ማያያዝ ይቻላል።

የሆነው ሆኖ የክልሉ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄን አሁንም ክህደት በፈፀመውና የራሱን አስቀምጦ ስለ ቅማንት ሲፈተፍት በሚውለው ደብረጽዮን እየተመራ የሚመልሰው አይመስልም። ይህንን ባለመፈፀሙ የህዝቡ ምላሽ ግን አስከፊ ይሆናል።

#ወልቃይት_ሆይ_ብረሳሽ_ቀኘ_ትርሳኝ