January 31, 2018
የኢህኣፓ ኣባል የነበረው ኣቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ትግራይ ስለማስገንጠል ያወራል። እንደማውቀው ኢህኣፓ ኢትዮጵያን ገነጣጥሎ ስለማፍረስ ዓላማው ኣልነበረም።
ታድያ የድሮ ኣባሉ ኣቶ ሙሉወርቅ ከጳጳሱ በላይ(ከህወሓት በላይ) ልሁን ያለበት ምክንያት ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው።
የቐዳማይ ወያነ ባመፁበት ወቅት እንግሊዝ ኣግኝታ የትግራይ_ትግርኚ መንግስት ብትመሰርቱ እንግሊዝ ሙሉ ድጋፍ ያደርግላቹሃል። ኣላቸው።
በኢትዮጵያውነታቸው ኩራት የሚሰማቸው ኣባቶች ኣሻፈረኝ ኣሉት።
ኣዋጅ ሲያስነግሩ ደሞ “ባንዲራችን የኢትዮጵያ ባንዲራ” ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ የጠላ ትግራዋይ ካለ መረብን ተሻግሮ ኤርትራ መኖር ይችላል።
ማንኛውም ኣካል ትግራይን የመገንጠል ሙኮራ ቢያደረግ የመጀመርያ ጥይት የምትተኮስበት ከትግራይ ህዝብ መሆንዋ ሊያውቅ ይገባዋል።
እኛ ተጋሩ የምንፈልገው ኣምባገነኑ የኢህኣዴግ ስርዓት በዲሞክራሲያዊና ህዝብ በመረጠው መንግስት እንዲተካ፤ ንፁሃን ተጋሩ፣ ኦሮሞ፣ ኣማራና ሌሎች ዜጎች የገደለ፣ የዘረፈና ያጠቃ በነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርዱን እንዲቀበል ነው። ከዚህ በዘለለም ሃገራዊ እርቅ ተደርጎ ይቅር ይቅር ተባብለን ወደ ሰላምና ፍቅር መመለስ ነው።
ጨቋኝና ፀረ ህዝብ ኣካል በተነሳ ቁጥር ኣገር እናፍርስ የሚል የፈሪ ተግባር የትግራይ ህዝብ ኣያስተናግድም።
የኣፄ ዮውሃንስ ኣንገት፣ የራስ ኣሉላ ጀግንነትና ትግል ለኢትዮጵያ ሃገራችን ኣንድነት ነው።
ዓንቀፅ 39 የሰጠችን መብት ተጠቅመን እንገነጠላለን የምትሉ የዋሆች ደግሞ በህገ መንግስቱ ከሰፈሩት 106 ዓንቀፆች ኣንድ እንኳን ባልተከበረባት ሃገር ለብቻዋ የምትተገበርበት ተኣምር የለም።
እቺ ዓንቀፅዋ ለማስከበር ከፈለጋቹ የተቀሩት 105 ዓንቀፆች ሳይሸራረፉ ማስከበር ይኖርባቹሃል። እምቢ ካላቹም እኛም እንደ ሞኝ እምቢ ብለን እናሸንፋቹሃለን።
ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንገነባለን!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !