የሕወሓት መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለ40 ብ/ጄነራሎች፣ ለ14 ሜ/ጄነራሎች፣ ለ3 ሌ/ጄነራሎች፤ ለ4 ጄነራሎች ወታደራዊ ማዕረጎች ሰጡ:: ለጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ አራት ምክትሎች እንደተሾሙላቸውም ተገልጿል::

በዛሬው ሹመት አራት መኮንኖች የሙሉ ጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን የሳሞራ የኑስ ምክትል ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸው ወትሮም ከወ/ሮ አዜብ እና አባይ ወልዱ ግሩፕ ጋር ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ጄነራል ሳሞራ የኑስን ለመምታት ወይም ስልጣን ለማሳጣት የተደረገ ሴራ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ::

የሳሞራ ምክትል ኢታማዦር ሹም ሆነው የተመረጡት: 1. ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር 2. ሌ/ጄኔራል አብረሃ ወ/ማርያም ገንዘቡ
3. ሌ/ጄኔራል አደም መሐመድ ሟህመድ እና 4. ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለልቻ ናቸው::

ጄነራል ሰዓረ መኮንን ጀነራል ሳሞራ ለህክምና በሚወጡበት ወቅት ቦታቸውን ሸፍነው ሲሰሩ እንደቆዩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች የሚናገሩ ሲሆን ሳሞራ ድንገት ከቦታው ቢነሳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙን ቦታ እኚሁ ሰው ይይዙታል ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል::

በዛሬው ዕለት ሹመት ያገኙትን መኮንኖች ዝርዝር ይመልከቱት:: (ስለመከላከያው ምስጢራዊ መረጃ ለማየት እዚህ ይጫኑ)

 

የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ኮሎኔል ፍሰሃ ስንታየሁ ዕምሩ
2. ኮሎኔል አስረሴ አያሌው ተገኘ
3. ኮሎኔል ደዲ አስፋው አያኔ
4. ኮሎኔል ዓለማየሁ ወልዴ ጅሎ
5. ኮሎኔል በርሄ ኪዳነ ስራፍኤል
6. ኮሎኔል ዳዊት ወልደሰንበት አውግቸው
7. ኮሎኔል አስፋው ማመጫ ይርዳው
8. ኮሎኔል ጥላሁን አሸናፊ ማሞ
9. ኮሎኔል ግደይ ሀይሉ ገብረእግዚአብሄር
10. ኮሎኔል ሽመልስ አጥናፉ ድንቁ
11. ኮሎኔል ተስፋዬ ተመስገን አባይ
12. ኮሎኔል ደሳለኝ ዳቼ ኡልቴ
13. ኮሎኔል አባዲ ሰላምሳ አበበ
14. ኮሎኔል መኮንን በንቲ ቴሶ
15. ኮሎኔል ከበደ ረጋሳ ገርቢ
16. ኮሎኔል ታገሰ ላምባሞ ድምቦሬ
17. ኮሎኔል ነጋሲ ትኩእ ለውጠ
18. ኮሎኔል ዳኛቸው ይትባረክ ገ/ማርያም
19. ኮሎኔል ፍቃዱ ፀጋዬ እምሩ
20. ኮሎኔል ይርዳው ገ/መድህን/ ገ/ፀድቅ
21. ኮሎኔል ይልማ መኳንንት ተንሳይ
22. ኮሎኔል ብርሃኑ በቀለ በዳዳ
23. ኮሎኔል ጉዕሽ በርሀ ወለደስላሴ
24. ኮሎኔል አባተ ዓሊ ፍላቴ
25. ኮሎኔል አለሙ አየነ ዘሩ
26. ኮሎኔል ብርሃ በየነ ወልደንጉስ
27. ኮሎኔል ሀይሉ እንዳሻው አቶምሳ
28. ኮሎኔል ገ/ህይወት ሳሲኖስ ገብሩ
29. ኮሎኔል ከበደ ፍቃዱ ገ/መድህን
30. ኮሎኔል መኮንን አስፋው ቀልቦ
31. ኮሎኔል አለምሰገድ ወ/ወሰን በርሄ
32. ኮሎኔል ሰለሞን ቦጋለ መኮንን
33. ኮሎኔል ወ/ጂወርጊስ ተክላይ አስፋው
34. ኮሎኔል ተሾመ ገመቹ አደሬ
35. ኮሎኔል ሰይድ ትኩዬ አበጋዝ
36. ኮሎኔል መንግስቱ ተክሉ ተሰማ
37. ኮሎኔል ኑሩ ሙዘይን ኣራሮ
38. ኮሎኔል ዋኘው አለሜ አያሌው
39. ኮሎኔል ሓድጉ ገብረጊወርጊስ ገብረስላሴ
40. ኮሎኔል መኮንን ዘውዴ ዳመነ

 

የሜጀር ጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ብ/ጄነራል አታክልቲ በርሀ ገብረማርያም
2. ብ/ጄነራል ያይኔ ስዩም ገብረማርያም
3. ብ/ጄነራል አስራት ደኖይሮ አህመድ
4. ብ/ጄነራል ዘውዱ በላይ ማለፊያ
5. ብ/ጄነራል ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት
6. ብ/ጄነራል ፍሰሃ ኪ/ማርያም ወ/ሂወት
7. ብ/ጄነራል ኩምሳ ሻንቆ ደስታ
8. ብ/ጄነራል ዋኘው ኣማረ ደሳለኝ
9. ብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ህካ
10. ብ/ጄነራል በላይ ስዩም አከለ
11. ብ/ጄነራል መሓመድ ተሰማ ገረመው
12. ብ/ጄነራል አብዱራህማን እስማኤል አሎ
13. ብ/ጄነራል መሰለ መሰረት ተገኝ
14. ብ/ጄነራል ክፍያለው አምዴ ተሰማ

 

የሌተናል ጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ሜጀር ጄነራል መሐሪ ዘውዴ ገ/ማሪያም
2. ሜጀር ጄነራል ሞላ ሐይለማርያም አለማየሁ
3. ሜጀር ጄነራል ሓሰን ኢብራሂም ሙሳ

 

የጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር
2. ሌ/ጄኔራል አብረሃ ወ/ማርያም ገንዘቡ
3. ሌ/ጄኔራል አደም መሐመድ ሟህመድ
4. ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለልቻ

 

በዚህ ዜና ዙሪያ የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አስተያየት:
በትላንትናው ዕለት ለ61 ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ተሰጥቷል። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አንጻር ብዙ ጄነራሎች ያሉዋት ሀገር እየሆነች ነው። 1ነጥብ 5ሚሊየን ለሚሆነው የአሜሪካን ሰራዊት 231 ጄነራሎች ሲኖረው ከ200ሺህ ሰራዊት ያልበለጠ ያላት ኢትዮጵያ ከ400 በላይ ጄነራሎች እንዳሏት መረጃዎች ያሳያሉ። አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት የተሰጡት ወታደራዊ ማዕረጎች፡ ከእሳቸው ሞት በፊት በነበሩት 21 ዓመታት ከተሰጡት በብዙ እጥፍ ይበልጣሉ።

ወታደራዊ ሳይንስ አካዳሚ ደጃፍ ሳይረግጡ፡ ይህ ነው የሚባል የዘመናዊ ውጊያ ልምድ ሳያካብቱ፡ ኮዳና ቀለብ በመቁጠር ሰራዊቱ ውስጥ የቆዩትን ሰብስቦ በማዕረግ ማንበሽበሽ የትግራይ ህዝብ ነጻአውጪ ግንባር የስልጣን ማረጋጊያ ስትራቴጂ የሆነ ይመስላል። እንደሰማነው በመከላከያ ውስጥ ጋዜጣና ደብዳቤ በማመላለስ ለዓመታት የቆየ አንድ ወታደራዊ መኮንንም የብርጋዴየር ጄነራልነት ማዕረግ ተሰጥቶታል። በዚህ ከቀጠልን ከቡና፡ ቆዳና ሌጦ በተጨማሪ ጄነራሎችን ኤክስፖርት የማድረግ አቅም ላይ መድረሳችን የማይቀር ነው።