ይህንን ያልኩበት ምክንያት << ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል የሰው ልጅ ፍጻሜ ነውና>> መድሐፈ መክብብ 7:2::
ከዚህ እውነታ ተነስቼ ወደ ዛሬው ጹሑፌ ልንደርደር:: የሁለት ሺ ዘጠኝን ዓ/ም መባቻንና የሁለት ሺ አስርን መቀበያ በተመለከተ በዊጪ አገር ለሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ግልጽ ደብዳቤ በሚል አንድ ጹሁፍ ከትቤ ነበር::
በዛ ጹፉፌ << ጠፍረን እንሰረው ሁለት ሺ አስርን በአንድነት ገመድ
ወደ ሁለት ሺ አስራንድ እንዳይረማመድ>>
ትላንት ኦህዴድ ነፍስ አንደዘራ ጫጩት ከኢሀዴግ እቅፍ ውስጥ ለመወጣት ያልሞት ባይነት ትግል ውስጥ እንደገባው ሁሉ ዛሬ ደሞ የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የስራ መልቀቅያ ማስገባታቸውን ሰምተናል ይህ የሚያሳየው የዘመኑ አርብርኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች አገረንና ህዝብን ለማዳን በአንድነት የሰሩት ወጤት ነው ባይ ነኝ:: ትላንት ቡዙዎቹ ጥንታዊ ታሪካችንን ረስተው ሆዳቸውን አስቀድመው እድገት እያሉ ወደ ጥፋት; ዴሞክራሲ እያሉ አምባገንነት; እውነት እያሉ ሐሰት;ነጻነት እያሉ ህዝባችንና አገራችንን ወደ ባርነት አዘቅት ውስጥ በመክተት ሃገርንና ህዝብን እየገደሉ ነበር::
እንደ እውነቱ ከሆነ በነሱ ሃሳብና እምነት ዘላላማዊ ነን ስልጣናችንን ለልጅ ልጆቻችን እናሰተላልፋለን ይህ ደሞ የሚሆነው ለቀረው ኢትዮጵያዊ የመቶ አመት የቤት ስራ ሰተነዋል በማለት የጭቆና መረባቸውን ከቤተሰብ እስከ ህብረየሰብ ዘርግተው ነበር::
ይህን ስንመለከት አምባገነን መሪዎች ምንግዜም ቢሆን ከተሪክ እንደ ማይማሩ ነው የሚያስረዳው: ታሪክ እንደሚነግረን በዚህች ዓለም ላይ እውነት የማይመስሉ እውነቶች ተደጋግመው ተፈጽመዋል:: የሩቁን ትተን የቅርቡን ብንመለከት የግብጹን መሪ ሙባረክን; የሊቢያውን መሪ ጋዳፊን እንዲሁም አገራችን ለዚህ ዓይነት ምስቅልቅሎሽ አብቅተው ወደ ሶስት ክንድ መቃብር ያዘገሙት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትርን አቶ መለስን መጥቀስ ይቻላል:: እ.ኤ.አ በ1815 ታላቁ የፈረንሳይ ንጉስ ናፖሊዮን ሲሞቱ ለፈረንሳዮች የሚታመን አልነበረም ሞቱንም ለመቀበል በእጅጉ ተቸግረው ነበር:: ይህንን ያሰተዋለው የዘመኑ ታላቁ ደራሲ ፌዩዶር በጹሁፉ << no man on the earth has the right to turn away and ignore what is on this planet. There are supreme reason for that>> እንግዲህ ይህንን ስናጤነው ዘላለም ቋሚ አገርና ህዝብ እንጂ ቋዋሚ መንግስት እንደሌለ ነው::
ይህ እውነታ ለህወሃት መሪዎችና ደጋፊዎች ይዋጥላቸው ይሆን? መልሱን ለነሱ ትቼ ለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የማቀርበው << በንግግር ወቅት ማመዛዘን ከአንደበተ ርቱእነት ይበልጣል>> እንደሚባለው አሁን አገራችን ባለችበት ሁኔታ ላይ የምንናገረውም ሆነ የምንጽፈውን ከወትሮው ለየት ባለ ጥንቃቄ እየተመለከትን ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል ምክንያቱም አገራችን መንታ መንገድ ላይ ደርሳለች የሚል እምነት አለኝና ነው::
በሌላ በኩል ታዋቂ ሙህራኖች ስለ ጥንቃቄ ስናገሩ<< ጥንቃቄ ያልታከለበት ታላቅ ችሎታ ወደ አሳዛኝ መጨረሻ መጓዝ እምብዛም አይቀርለትም::>> ይላሉና አገራችን ኢትዮጵያ እንደ አገርነት; ህዝባችንም እንደ ህዝብነት እንዲቀጥል የእያንዳንዳችን ሀላፊነት ነው ባይ ነኝ ምክንያቱም በአሁኑ ሰዓት መንግስት አለ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገር ስለማይቻል:: ስለሆነም ከላይ ማለት እንደፈለኩት በዊጪ አገር የምትገኙ የመገናኛ ቡዙሀንና እንደዚሁም ከየቤታችሁ ሆናችሁ በፊስ ቡክ ላይ አገራዊ ጉዳይ የምታስደምጡ ወንድሞችና እህቶች እስከ ዛሬው ድረስ የምታስተላልፉት መልካሙን በመልካምነቱ መጥፎውንም በመጥፎተቱ ገምግማችሁ ከአሁን ቦሃላ ለምታስተላልፉት የበለጠ ጥንቃቄ እንድ ታረጉ ልመናዪ ከወዲሁ ነው:: ለምን የምትሉ ካላችሁ <<ንብ ከሌሎቸ እንሰሳት የበለጠ የምትከበረው ሰራተኛ ስለሆነች ሳይሆን የምትሰራው ለሌሎች ስለሆነ ነው::>> ይለናል ቅዱስ ክሪሶስቶም
በመጨረሻም ለይቅርታ የፈጠንን ለቂም በቀል የዘገየን እንሁን እያልኩ ለዛሬ በዚህ ላብቃ::
