ከኢያሱ ኤፍሬም (ለንደን)
ታላቁን የጥቅምት 17 የሩሲያ አብዩት በግንባር ቀደምትነት ከመሩት ሰዎች መካከል ታላቁ ትሮትስኪ አንዱ እና አንጋፋ አብዮተኛ ሰው ነው (Leon Trotsky) ፡፡ አብዮቱን በማደራጀት እና በመምራት የሌኒን ቀኝ እጅ በመሆን እስከ እለተ ሞቱ ድርስ አልተለየውም፡፡ ምንም እኳን ትሮትስኪን ለስልጣን የሚያበቃው የአመራር ብቃት የትምህር እውቀት ቢኖረውም በአንድ ወቅት ከሌኒን የቀረበለትን የሩሲያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትርነትን ስልጣን ውድቅ አደረገው፡፡ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የሱ የዘር ማንነት ( ሩሲያ ጁ) በመሆኑ አዲስ የተቋቋመውን የሩሲያ መንግስትን የሚፃረሩ ሐይሎች የሱን ማንነት ምክንያት አድርገው ጨቅላውን አብዮተን እዳይጎዱት በአርቆ በማሰብ እና በማስተዋል ነው፡፡ ስልጣን ለአብዮቱ እቅፋት መሆን እንደሌለበት ለሌኒን አስረዳው፡፡ተቀባይነትም ቸገኝ፡፡
ሌላው ታላቅ የለውጥ መሪ የኩባው ቼ-ጎቬራ (Ernesto “Che” Guevara) ነው፡ የኩባን አብዮት ከካስትሮ ጋራ በመሆን የመራ እና ለድል ያበቃ እሰካሁን የነፃነት ምልክት ሆኖ የቀረው የአርጀንቲናው ተወላጅ ቼ ጎቬራ የኩባን አብዮት ካሳካ በኋላ የተደላደለውን ስልጣን አልፈልግም ብሎ ሌላ አብዮት ለማቀጣጠል ፋኖ ያለ ታላቅ ሰው ነው፡፡ ለእሱ ስልጣን የትግል ግብ ሳይሆን የሰው ልጆች ነፃነት ነበር፡፡ ለእዚህም ነበር ከካስትሮ ቀጥሎ ያለውን የኩባን የስልጣን መንበር ለቆ፡ አንዴ በአፍሪካ በመጨረሻም በላቲን አሜሪካ ፀረ-ጭቆና ትግል አካሂዶ የመጨረሻን ፅዋ የቀመሰው፡፡ የቼ ዋና አላማ ህዝቦችን ከጭቆና የማውጣት እንጂ ስልጣን እና የተደላደለ ኑሮ አልነበረም፡፡
ስልጣን የሰው ልጆች ወይም የለውጥ አራማጆች የመጨረሻ ግብ አይደለም ፡፡ ምንም እንኳን ዩናይትድ ኪግደም (እንግሊዝ) ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ ጥፋት ነው ብዬ ባምንም ፡፡ እንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት ለማስወጣት ግንብር ቀደም ሚና የተጫወተው የወግ አጥባቂው ፓርቲ ባልደረባ የሆነው ቦሪስ ጆንሰን Boris Johnson ስልጣንን በተመለከተ የወሰደውን እርምጃ ሳላደንቅ አላፍም፡፡ በወቅቱም ከሀዲ ብዬ ያቅሜን ያህል ወርፌዋለሁ፡፡ የእሱ ስልጣን አለመፈለግ ብዙ ትምህርት አስተምሮኝ ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ ቦሪስ ገና የዩንቨርሲቲ ተማሪ ሆኖ ነው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የታጨው፡፡ ዘ ኦኮኖሚስት ከአመታት በፊት ባሳተመው እትም ላይ የሽፋን ግፅ አድርጎ ስለ ቦሪስ የወደፊት የእንግሊዝ የቅላይ ሚኒስትርነት ዘግቧል፡፡፡ ነገር ግን ቦሪሰ የብሪክሲትን (Brexit) የዲሞክራሲ ጦርነት በድል ከተወጣ በኋላ ( አጭበርብሮም ቢሆን) እና ዴቪድ ካሜሮን (David Cameron ) በሽንፈት ስልጣኑን ሲለቅ ፡፡ ከዲቪድ ካሜሮን ስልጣኑን ይረከባል ተብሎ የተጠበቀው ቦሪስ ነበር፡፡ ነገር ግን በሚያስገር ሁኔታ ቦሪስ የኔ ሰአት አሁን አይደለም ብሎ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደ ማይወዳደር አሳወቅ፡፡ እነሆ ልፊ ያላት ሜይ ብሬክሲትን ለማሳካት ትዳክራለች፡፡ ቦሪስ የሚያውቀው ነገር ነበር ብሬክሲት የፓለተካ ጨዋታ እንጂ የምር አልነበረም ( ይህን ለታሪክ እተወው)፡፡ አሁን ቦሪስ አገለግልበታለሁ በለበት የስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦ ሀገሩን እያገለገለ ነው፡፡ ስም እና ዝና፡፡ ጥቅም እና ክብር ከአላማው ቦሪስን ዝንፍ አላደረገውም፡፡
ከእነዚህ ሶስት ታላላቅ የፓለቲካ ሰዎች የምንማረው ብዙ ነጥቦች አሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ፓለቲከኞች በተለያየ ዘመን የተከሰቱ ሲሆን፡፡ አንዱ በሩሲያ በ1900 ዎቹ መግቢያ ላይ የተገኘ፡፡ ሌላው በላቲን አሜርካ በ1900 ዎቹ አጋማሽ ላይ የተገኘ፡፡ ልላው በአውሮፓ 2000 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተገኘ ፡፡ ይህን ስንመለከት የምንማረው ነገር ቢኖር ቦታው እና ግዜው ቢለያይም የፓለቲካ ፍልስፍና አንድ መሆኑን ነው፡፡ ያም ማለት ለውጥ የማታመጣበትን ስልጣን ለስም ብለህ አትወስድም ከወስድክም የሚደርስብህ ሌላው ቢቀር የስብእና ሽንፈት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጥልቀት ስናየው እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ስልጣን እና ፓለቲካን ለይተው እና አበጥረው የሚያውቁ መሆናቸውን ነው፡፡ የሚሰጣችው ስልጣን የሚፈልጉትን አላማ ለማራማድ ወደ ኋላ
የሚጎትትባችው ከሆነ፡፡ ስላታን ብቻውን ዋጋ እንደሌለው ተረተዋል፡፡ ስልጣናቸው ለውጥ የማያመጣ ሆኖ ስላገኙት ያ የተሰጣችውን ስልጣን አንፈልግም ብለው ትተዋል፡፡ ነገር ግን ትሮትስኪን ስንመለከት ታግሎ የሚያታግልበትን መድረክ ነው የፈለገው እና የወሰደው፡፡ ቼን ብንመለከተው ወንበሩን ለቆ ፋኖ ነው ያለው፡፡ ለሚያምንበትም አላማ ሞተ፡፡ ቦሪስን ብንመለከተው ውጤት ሊመጣበት የሚችልበት ቦታ እና ሊሰራበት የሚያስችለውን ስልጣን ነው የወሰደው፡፡እስካሁንም የሚገባውን ክብር እና ዝና አግንቶ ይኖራል፡፡ግን ትክክለኛ ግዜውን ይጠብቃል፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ከመታያነት ከስም እና ከዝና የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ ይህ በኃይለማሪያም ቁልጭ ብሎ የታ ጉዳይ ነው፡፡ ኃይለማሪያም እዚህ ግባ የሚባል ስራ ኤደለም ንግግር ሳያደርግ ነው ስልጣን በቃኝ ያለው ወይም በቃህ የተባለው፡፡ የልጅ ልጆቹ አያታችን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበረ ይሉ ይሆናል እንጂ ከተወሰነ ግዜ በኋል የኢትዮጵያ ህዝብ ከነመፈጠራችው የሚያስታውሳቸው አይመስለኝም፡፡
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በራሱ የሚወስንበት አቅም የለውም፡፤ አሁን ባለው የፓለቲካ ስርአትሀገሪቱ የምትመራው በወል አመራር፡፡ በአንድ እርዮተ አለም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ዶክተር አይደለም አምላክ እራሱ እኳን ቢሆን የኢሕአዴግን አሰራር መሸራረፍ አይችልም፡፡ ይህ በሆነበት ሰአት አቅም እና ችሎታን፡፤ የተከበረን ስም በታሪክ ለማጉደፍ ካልሆነ በቀር አርቆ የሚያስተውል ማናችውም ሰው በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያን ጠቅላይሚኒስትርነት ቦታ አይመኝም፡፡ ቢመኝም ለራሱ ጥቅም፡ስም ፡እና ዝና ካልሆነ በቀር ለሚወክለው ህዝብ አንዲት ጠብታ ቁም ነገር አያመጣም፡፡
