“ባድመ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም የትግራይ ህዝብ ነው። ባድመ! የባድመ ድል የተገኘው በኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም በትግራይ ህዝብ ነው ወይም በኢትዮጵያ መንግስት አደለም።” – አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር የትግራይ በላሃብት ከተናገሩት የተወሰደ
አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ይባላሉ በጣም ታዋቂና የናጠጡ ትግራዋይ ባለሀብት ናቸዉ። አቶ ዳዊት ከአውራምባ ዌብሳት ባለቤት ከጋዜጣኛ ከዳዊት ከበደ ጋር ባደረጉት ቆይታ ባድሜ የትግሬ እንጅ የኢትዮጵያ አይደለም፣ ባድሜ ነጻ የወጠው በትግሬ እንጅ በኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ብለዋል። አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በትግረኛ የተናገሩት ቃለመጠየቅ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ቃል በቃል እነደሚከተለው ተተርጉሟል።
“ባድመ የትግራይ ነው፣ የኢትዮጵያ አይደለም። ባድመ መተዳደር ያለበት በትግራይ ፍላጎት እንጂ በኢትዮጵያ ፍላጎት አይደለም፣ መተዳደር ያለባት። ባድመ ባመጣው ውስጡን ሚስጥሩ በማናውቀው ከወንድሞቻችን ኤርትራዊያን ጋር ጦርነት አካሂደን። ከደርግ ውጊያ በእድል የተረፉትን ወንድሞቻችን እዛ ላይ ተሰውተዋል”
አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ባድመ ላይ የተሰዉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ደማቸውን ከደም አልቆጠሩትም። አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሔር የሚያስጨንቃቸው የትግራይ ትግሪኚ (ኣግኣዝያን) የወደፊት ግንኙነት ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ በሻብያ ተወረረ ተብለህ የአገርህን ዳር ድንበር ለማስከበር ብለህ ከደር እስከዳር ተንቀሳሰህ ወደ ትግራይ በመዝመት ከሻብያ ጋር ለተደረገው ጦርነትና ህይወትህን የከፈልከት ባድሜ የአንት አይደለም እየተባልህ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ልጅህን፣ ወንድምህን፣ እህትህንና ወዳጅህን እንዲሁም አካልህን በባድመ ጦርነት ያጣህ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ይኸውልህ ጉድህን ስማ።
እውነት ከትግሬ ህዝብ በቀር ለባድመ መሬት የሞተው የቆሰለውና አካሉን ያጣው ባድመ የኢትዮጵያ ነች ብሎ የዘመተውና ህይወቱን የከፈለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሞተው በማያገበው ነገር ነበር ማለት ነው? እውን ባድሜ ከትግሬ በቀረ የሌለው ኢትዮጵያዊ ግዛት አደለምን?
እውነት ትግራይ እንዲህ አይነት ድፍን ጭንቅላት ያላቸው ሰዎችን እንዴት ልትወልድ ቻለች? እውን እነዚህ ሰዎች ሌላው የኢትዮጵያን ህዝብ ኢትዮጵያ የእኛ ናት እንደሚያየው ሁሉ እነሱም ኢትዮጵያም የእኛም ናት ይሉ ይሆን? እነዚህ የትግራይ ባለባቶችን እና ምሁራ ተብየውች የሚያዮት ትግራይ ማለት የግላቸው ኢትዮጵያ ደግሞ የጋራቸው አድርገው ነው። እነዚህ ሰዎች ሲሞቃቸው ትግራዊ ሲበርዳቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
ለማንኛውን በባድሜ በተካሄደው ጦርነት ያገር ድንብረ ለማስከበር የተሰውት፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና የተለያየ መስዋትነት የከፈሉት የኢትዮጵያውያን ደም ይፋረዳቸው።
ቪዲዮውን ከዚህ በታች በትግርኛ ቋንቋ ያዳምጡ
