ዖውድዮ ቪድዮ ለማየት ይህን ይጫኑት⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads
/2018/02/28038631_395443797583911_3359145234175885312_n-1.mp4

ወያኔ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል የአማርኛ ጥላቻ ያለባቸው የአሥተዳደር አካላትና ወጣቶች አማርኛ ተጽፎባቸው ኦሮምኛ ያልተጻፈባቸውን እንዲሁም ኦሮምኛና አማርኛ  የተጻፈባቸውን የማስታወቂያ ሰሌዳዎች በቀይ ቀለም በማቅለምና እየገነጠሉ በማስወገድ ጥላቻቸውን አንጸባርቀዋል፡፡

ለዚህ የጥላቻ እርምጃቸውም ኦሮምኛው በአግባቡ አልተጻፈም!” የሚል የሽፋን ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ይህ ምክንያት ትክክለኛ ምክንያት እንዳልሆነ የሚያረጋግጠው በአግባቡ ያልተጻፉ የኦሮምኛ ማስታወቂያዎች ላይና በዓረብኛና በሌሎች ቋንቋዎች ብቻ በተጻፉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ አለመወሰዱ ነው፡፡

እንደምታውቁት በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም በየኢምባሲው፣ በየመስጊዱ፣ በየየቻይና ፕሮጀክት ቦታዎች ወዘተረፈ. በእንግሊዝኛ፣ በዓረብኛ፣ በቻይንኛና በሌሎችም ቋንቋዎች ብቻ የተጻፉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ማንም ግን ጽንፈኛ አቋም ይዞ ለምን?” በማለት እርምጃ ለመውሰድ የሞከረ አይደለም ያሰበ እንኳን የለም፡፡

ወያኔ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል ግን የሕዝባዊ ትግሉን አቅጣጫ ለማስቀየስ ፈልጎ ይመስለኛል መሰንበቻውን አማርኛ ባለባቸው የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፈጽሞ ሊገመት የማይችል ነው፡፡

እነኝህ ሰዎች ዛሬ የማስታወቂያ ሰሌዳ በኦሮምኛ አስተካክላቹህ አልጻፋቹህም የሚል ሽፋን አዘጋጅተው ይሄንን ያደረጉ ነገ ኦሮምኛን አስተካክላቹህ መናገር አትችሉም ወይም ከነአካቴው ኦሮምኛን አትችሉምና ብለው በሰዎች ላይ እርምጃ ላለመውሰዳቸው ምን ማረጋገጫ አለን???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com