
የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) አቢይ አህመድን (ዶ/ር) ሊቀ መንበር አድርጎ መምረጡን በፓርቲው ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ አስታወቀ፡፡ ዶ/ር አቢይ የሊቀ መንበርነት ሥልጣኑን ከአቶ ለማ መገርሳ በዛሬው እለት የተረከቡ ሲሆን አቶ ለማ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው እንደሚቀጥሉ ታውቋል፡፡
ዶ/ር አቢይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይታወሳል፡፡
