የቪኦኤ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍሎች የቋንቋውን ተናጋሪ ማኅበረሰቦቸ በሚገባ እንደሚያገለግሉ የታወቀ ሲሆን የአማርኛው ክፍል ግን ዐማራውን የረሳና ይባስ ብሎም ያገለለ መሆኑ በእጅጉ ሲገርመኝ የኖረ ነው። እንደነ አዳነች ፍስሃየና ሔኖክ ሰማእግዜር ያሉ ዐማራ ጠል አማርኛ ተናጋሪዎችን የያዘ ሚዲያ ከዚህ ያልተለየ አቋም ቢኖረው ብዙም የሚገርም አይደለም። በሁለቱም ሚዲያዎች በሁሉም ቋንቋ ፕሮግራሞቻቸው የሚያቀርቧቸውን እና ለውይይት የሚጋብዟቸውን ሰዎች ብትመለከቱ የፕሮግራሞቹ ሒደት ወዴት እንደሆነ ለመገመት አይከብድም። ምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ እንኳ የኮ/ል ደመቀ ዘውዱን የፍ/ቤት ሒደት እንዲዘግቡት የሁለቱንም ሚዲያዎች ስንት ጊዜ ማላጅ እንደላክን በሁለቱም ሚዲያዎች የሚሠሩ ሰዎች ያውቃሉ።
ያው ድምጽ ቢሆንን መልካም ነው ካልሆነም መቼም ተጋድሏችን ድምጽ ባለመኖሩ ብቻ ሊዳፈን አይችልም በሚል ተስፋ በመቁረጥ ትቻቸው ነበር፤ ሆኖም እርማቸውን አቻምየለህ ታምሩን የጋበዙት የቪኦኤ አማርኛ ዝግጅት ክፍል ሀሳቡን እንኳ በአግባቡ እንዳይናገር ሔኖክ ሰማእግዜር በሚባል ዐማራ ጠል ጋዜጠኛ የተደረገው አፈና አስገድዶኝ ነው ይህችን አጭር ኪታብ የጻፍኩ።
ሔኖክ እንደጋዜጠኛ የሁሉንም ሐሳብ እኩል መስማትና ውይይቱን ማካሔድ ሲገባው ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የአፓርታይድ ሥርዓት የለም›› ብሎ ቀይ መስመር አሰመረ። በአጪሩ በውይይታችን ለመሳተፍ ይህን የማይነካ መሥመር ማለፍ የለብህም የሚል ነው። ይህ ግለሰብ አቻምየለህን እንዳይናገር ከመገደቡም በተጨማሪ ያላለውን አለ ያለደረገውን አደረገ እያለ አቻምየለህን ከሀሳብ ውጭ ለማድረግ ያደረገው የካድሬነት አካሔድ ቢገርመኝም አቻምየለህ ታምሩን ግን ይህን ሁሉ ተቋቁሞ በመዝለቁ አድንቄዋለሁ።
በተለይ ጽዮን ግርማ ባትኖር ኖሮ ሔኖክ ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስብ በእጅጉ ይገርመኛል። ዶቼቨሌ የሞተው እነ አቶ ተክሌ የኋላ በጡሬታ ከተሰናበቱ በኋላ ነው።
Source – welkait.com