ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት

 ለውሽውሽ ሻይ ተክል ድርጅት መላው ወዛደሮች
 ለቴፒ ቡና ተክል ድርጅት መላው ወዛደሮች
 ለበበቃ ቡና ተክል ድርጅት መላው ወዛደሮች
 ለጉመሮ ሻይ ተክል ድርጅት መላው ወዛደሮች
 ለሊሙ ቡና ተክል ድርጅት መላው ወዛደሮች

 


እንዲሁም በሌሎች የደቡብ ምዕራብ የልማት ድርጅቶች የምትሰሩ አገር ገንቢ ወዛደሮች በሙሉ፣ የወያኔ መንግስት ላለፉት 27 ዓመታት ሲከተል በነበረው የአፈናና የጭቆና ሥርዓት በህዝብ ላይ ካደረሣቸው አሳዛኝና አሰቃቂ በደሎች አንዱ አንተና በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችህ የሚተዳደሩበትን እነዚህን ታላላቅ ድርጅቶች ጀሌዎቹ ለሆኑት በዝባዥ ባለሃብቶች በመሸጡ እየደረሰብን ያለውን ዘርፈ ብዙ በደልና ሰቆቃ አንተው ራስህ ታውቀዋለህ።

አንተና ቤተሰቦችህ ለዘመናት የለፋችሁበት እነዚህ አንጋፋና ታላላቅ ድርጅቶች የወያኔ ጀሌዎች ለሆኑ ባለሃብቶች ተሽጠው እነርሱና ቤተሰቦቻቸው በአውሮፓና በአሜሪካ የተንደላቀቀና የተመቻቸ ኑሮ ሲኖሩ አንተና ቤተሰቦችህ ደግሞ በረሃብ በእርዛትና በከፋ ድህነት ውስጥ እንድትኖሩ ተደርጓል።

በመሆኑም ዛሬ እንደሚታወቀው መላው የሃገራችን ህዝብ ይህንን አንባገነንና አስከፊ ሥርዓት እስከነአካቴው ለመግርሰስ ሠላማዊ አመፅና ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል።

እናም ከማንም በበለጠ የወያኔ ጭቆና በትር ያረፈብህ በአንተና በቤተሰቦችህ መሆኑን በመግንዘብ በያለንበት አፋጣኝ የሆነ የስራ ማቆምና ሌሎችንም ተዛማጅ ሰላማዊ ትግል አመፅ በማድረግ የተነጠቅነውን ዴሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ መብት እንድታስመልስ ድርጅታችን ጥሪውን እያቀረበ ለምታደርገው ትግል ሥኬታማነት ከጎንህ የምንቆም መሆናችንን በደስታ እንገልፃለን።

ድልና ሥኬት ለመላው ሕዝባችን !!!!

ዘሀበሻ