አስቸኳ ጊዜ አዋጁ መጽደቅ ያለበት በ2/3ኛ ድምጽ ነው ከተባለ ልዩ የሒሳብ ችሎታ የሚጠይቅ ቀመር የለም፡፡ ደገፉ የተባሉት 346 ነው፡፡ ይም ቢሆን አዋጁን ለማጽደቅ ወስነው የገቡት አቶ አባዱላ 339 ድምጽ እንዳገኘ ነው የተናገሩት፡፡ አባላት ሞተዋልም ተብሏል 8 ማለት ነው፡፡ ሌላስ እሺ ተጨማሪ የሚዋሽ ነገር ከአለ ጨምሩበት፡፡ እሺ እሰኪ በትልቁ ቁጥር እናስላላቸው 346ቱ ማለት ነው 339ን ትተን፡፡ የሞቱትንም እናስብላቸው፡፡ በመሠረቱ አባላትን የመተካት ግዴታ እንጂ በሞቱ ሰዎች ወንበርን መቀነስ አሰራር አደለም፡፡ ይህም ይሁን ሞቱ፡፡ ለነገሩ የተሰበሰቡትስ መኖራቸው ይሆን? እንደዛም ሆኖ እንበልና 539 “ያልሞቱ” አባላት አለው እንበል፡፡ እንግዲህ በዚህ ሂሳብ 2/3 ማለት በትንሹ 66 በመቶ ድምጽ ሊገኝ ይገባል፡፡ 346/539 ትልቁን አገኘን የሚሉትን እና ጠቅላላ ድምሩን የሞቱትን ቀንሰንላቸው የሚሆነው 64 በመቶ ነው፡፡ በቃ ሒሳቡ ቢያንስ እዚሁ ጋር ያበቃል፡፡ በመሠረቱ ግን 346/547 ነበር አሰላሉ፡፡ በዚህ ስሌት ደግሞ ወደ 63 በመቶ ይወርዳል፡፡ በቃ ቀመሩ ፓርላማ አጸደቀ ጣለ አደለም፡፡ ወያኔ ፓርላማው ጣለውም አሳለፈውም አዋጁን ለመተግበር ቀድሞውንም ስለወሰነች ይሄ አሁን የምናየው ይጠበቅ ነበር፡፡ ከዛም ቁጥሩን ከፍ በማድረግ 395 ድጋፍ አገኘሁ አለች፡፡ ልብ በሉ የተሰበሰቡት 441 ናቸው የተቃወሙት 88 ተዓቅቦዎች እሱም ለወያኔ ይደመሩ እና እና ከ441 88 ብቻ ሲነሳ ቁጥሩ 353 ነው፡፡ 395 ድምጽ …… የተለመደው የወያኔ የወሮበላ ቀመር ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ተዓቅቦዎቹን ጨምሮ ቢደመር በትንሹ የሚጠበቀው 359 ስለነበር ሊያጸድቀው የሚችለው ድምጽ አሁንም ይወድቅ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ ግን የተወሳሰበ ሒሳብ አደለም፡፡ ግን ቢያንስ ቪኦኤና ዶቼቪሌ እንዴት የወያኔን ድምጽ ተቀብለው አዋጁ መጽደቁን አወጁብን፡፡ ሁለቱም ቢዲያዎች ጸድቋል ብለው በማረጋገጥ ዘገቡ እንጂ ጸድቋል ተብሏል እንኳን አላሉም፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ በአስቸኳይም ለሕዝብ ከይቅርታ ጋር እውነታውን በማስተካከል ሊናገሩ ይገባል፡፡ ይሄ የስነልቦና ችግር ነው፡፡ እውነትን በራስ መርምሮ ከመዘገብ አቶ እከሌ ተናገረ ብሎ እሱንው እንደ ትክክለኛ መረጃ ማውራት ስህተት ነው፡፡ መረጃው ግልጽ ነው፡፡ የአቶ እንቶኔን መናገርና አለመናገር አያስፈልገውም ነበር፡፡ በተለይ ቢኦኤ እንደሰማነው በፓርላማውም ተገኝቶ ሂደቱን ተከታትሏል፡፡ እንግዲህ በግልጽ ቁጥሮች የሚናገሩትን እውነት እንዲህ ከተዋሸን ሌላውንማ እንዴት ይሁን፡፡ ቪኦኤም ዶቼቪሌም ይቅርታ ሊጠይቁ መረጃውንም በትክክል እንደገና ሊዘግቡ ይገባል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ለእነ ቪኦኤዎችና ዶቼቪሌዎች የተቃዋሚው መብዛት ሲየስደምማቸው እኔ እጅግ አሳፋሪ የሕዝብ ተወካይ እንደሆነ ነው የተሰማኝ፡፡ ቢያንስ ኦህዴድ 178ና በዓዴን በድመሩ 137 በድምሩ 315 መቀመጫ አላቸው፡፡ እንበልና የሞቱትም ከእነዚህ ውስጥ ይሁን፡፡ እሺ የቀሩትም 110 እናርጋቸውና ከነዚሁ ይሁን አሁነም ቢያንስ 197 መቀመጫ ነበሩ፡፡ ልብ በሉ የሞቱትም የቀሩትም ሙሉ በሙሉ ከኦህዴድና በአዴን ነው ተብሎ ቢታሰብ ነው፡፡ ተቃወሙ የተባሉት በሙሉ ተደምሮ ግን 88 እሺ ተዓቅቦችንም ደምረን በድምሩ 96 መቀመጫ ነው፡፡ በዚህ ስሌት አሁንም አሁንም ይበልጠው ኦፒዲኦና በኣዴን የወያኔ ተወካይ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየን ነው፡፡ ለነገሩ ከኦፒዲኦ አንዱ አባዱላ አደል? ጭራሽ በጭብጨባ እናሳልፈው እጅ ማውጣቱን ትተን ሲል ነበር፡፡ አሁንም እንደሚሰማው አነሰም በዛም ከኦፒዲኦ የተሻለ ቁጥር ያለው ተወካይ ለሕዝብ ወግኗል፡፡ ከበዓዴን ምን ያህል እንደወገነ ለመገመትም ያስቸግራል፡፡ በተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙት በዓዴኖች ከወያኔ በላይ የዚህ የወሮበላ ስርዓት አከርካሪ ናቸው፡፡ ብዙዎቹም በቀጥታ ትግሬ ወያኔ የሆኑ በአማራነት የሚቆምሩ ናቸው፡፡ ብቻ ትዝብት ነው፡፡ እኛስ ከአሁን በኋላ ቆርጠናል፡፡
እንግዲህ ለማን ጠ/ሚኒስቴር እንዲሆን የተመኛችሁ ሁሉ ይህን ጎዳችሁን እዩት፡፡ እንኳን በወያኔ ትግሬ የተተበተበውን የመከላከያና ደህንነት ይቅርና የኦፒዲኦ የሕዝብ ተወካይም ዋና አደጋ እንደሚሆን፡፡ አብይን ዛሬ ምን እንደወሰነ አልሰማንም፡፡ እንግዲህ ከ88ቱ ከሆነ ጠ/ሚኒስቴር እንደማይሆን በግልጽ አይተናል፡፡ ከ346 ከሆነ እድል አለው፡፡ ሰሞኑን ለደ/ር አብይ ማስጠንቀቂያ ብዬ የጻፍኩት ከመጥፎ አደለም አብይ መልካም ቢሆን መልካም ግን በልቡ ተንኮል ከአለም ከወዲሁ ለማሳሰብና ሰዎች ስለእሱ በዚህም መልክ አንደሚያስቡ ለመጠቆም ነው፡፡ አንድ ስርጉት የምትባል አስተያየት ሰጭ ይሄንኑ የእኔን አስተያየት አስመልክቶ የጻፈች ድርሶኛል አመሰግናለሁ፡፡ ግን አንድ ነገር እንድታውቂልኝ የምፈልገው፡፡ አንቺ ስለወደድሽው ትክክል ነው ማለት አደለም፡፡ በአስተያየቶችሽም ብዙ የሰዎችን አባባል ጠቅሰሽልኛል፡፡ የታዋቂውን አይንሽታይንን(አይንስታይን) ጨምሮ፡፡ ግዴየለሽም የሰዎች ፍልስፍና ትክክል እንኳን ቢሆን እኔ የምኖረው በራሴ ነው፡፡ ከአይንሽታይንም በላይ የማደንቃቸው የሕየወት ፍልስፍና ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ሳይንቲስት ወይም ታዋቂ አደሉም ግን በእኔ ሕይወት ውስጥ ብዙ ቦታ አላቸው፡፡ ለማንኛውም ወደድንም ጠላንም ይሄ ፓርላማ ነው እንግዲህ ጠ/ሚኒስቴር አጽዳቂው፡፡ በቃ ሕዝብን የካደ መሆኑን በግልጽ ያስመሰከረ ፓርላማ፡፡ ቢያንስ አሁን የተፈጠረለትን እድል ተጠቅሞ ቢሆን ብዙ ክብር በተሰጠው፡፡ የሄን እያየን መንግስት፣ ተወካዮች ምናምን እንላለን፡፡ ከኦፒዲኦ የተወሰኑ ድምጻቸው በቁጭት ተሰምቷል፡፡ መልካም ነው! 88ቱን እናመሰግናለን ተዓቅቦች ደፋር ሁኑ፣ ደጋፊዎች ፈርታችሁ ከሆነ ከወያኔ በላይ ውክለንዋል የምትሉት ሕዝብ ሊያስፈራችሁ ይገባል፡፡ አድር ባዮች ከጌቶቻችሁ ጋር ቀጥሉ፡፡ እንደፈርዖን ልባችሁ ደንድኗልና እንደ ኖሕ ዘመን ሰዎችም ሊያጠፋችሁ የመጣውን ማዕበል ልታዩ አይቻላችሁም፡፡
በመጨረሻም ከአሁን በኋላ ወሬ ይቁም ከእነዚህ ከዛሬዎቹ 88 ጀግኖች በቀር በሕዝብ ላይ የሞት አዋጅ ያወጁን ሕዝብ በእነሱ ላይ ሊያውጅባቸው ይገባል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ
