02/03/2018;23:09
ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ የተነሳሳሁት ቅዳሜና እሁድ ሲካሄድ በነበረው Conference organised by People Alliance for freedom and democracy (PAFD)
Purpose: international conference on the current political crisis in Ethiopia and explore realistic alternatives. 24 to 25 February 2018 at Resource Centre Holloway, London.

በተጠራው ስብስባ ላይ ተገኝቼ ነበር :: በዚህ ቀን እጅግ ለማመን ያዳገተኝን : ክስተት ልነግራችሁ ነው ::
አንዳንድ ሰዎች ለሰልሳ ቆዳ ፣ያላቸው ነገር ግን መርዘኛ፣ ቅን የሚመስል :ገጽታ ያላቸው ነገር ግን ክፋትን ፣ የተሞሉ፣ ሃይማኖተኛ ፣ የሚመስሉ ነገር ግን ከዳተኞች !! ታማኝ የሚመስሉ ነገር ግን ቀማኞች ! እውነተኛየሚመስሉ : ነገር ግን ፍጹም ሐሰተኞች! ተቆርቋሪ፣የሚመስሉ፣ነገር ግን፣አፍራሾች! ሰላማዊ የሚመስሉ ፣ በውስጣቸው ግን ፀረ-ሰላም፣ የአንድነት ጠበቃ ፣የሚመስሉ ነገር ግን ከፋፋይ !! ወ .ዘ . ተ የሆኑና እንደ በርሃ እባብ ፣እንደ እስስት ተመሳስለው መርዛቸውን ሲረጩ የኖሩና የእራሳቸውን ጊዜ በመርዝ በተበከለ ሴራና በክፋት በተሞላ ተንኮል ፣ ተተብትበው ያለውጤት ያረጁ ፣ አዲሱን ኢትዮጵያዊ ትውልድም የሚበክሉ ፣ አርአያነት ፣የጎደላቸው ብዙዎች ናቸው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይታመን ሲቀር ፣ ወንበዴ፣ ቀማኛ፣ ሌባ፣ ሀገር ሻጭ፣ የእናት ጡት ነካሽ ወዘተ እየተባለ የመጥፎ ተግባር ጠንሳሽና መስራች ወያኔ ፣ በእራሱ የሥልጣን ዘመን ተወልደው ለአቅመ አዳም ከደርሱ አዲሱ ትወልድ ጀምሮ ከሽማግሌ አዋቂ ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተጠላ፣ የተነቀፈ በታሪክ ዝቃጭነት በከፍተኛ ደረጃ የተዋረደ በመጥፎ ምሳሌነት ፣ ተጠቃሽ እና የተጎሳቆለ፣ ስብዕና የሕይዎት፣ ገጽታ ባላቸው ሰዎች የተሞላው የህወሀት ትግሬ አገዛዝ ብቻ ነው።
ህወሀት ይህን የወንብድና ተግባሩን በህቡዕም ሆነ በገሀድ በዋናነት አስፈጻሚ አድርጎ የሚሾማቸው ወይም ካድሬ አድርጎ በሰላይነት አጥምቆ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚጠቀምባቸው ወይም የሚወክላቸው ከላይ ከመግቢያው እንደተጠቀሰው ለእራሱ እወነተኛ ገጽታ ተቀራራቢ ዝምድና አለኝ ብሎ የገመገማቸውን ወይም የመለመላቸው በምግባር የሚመስሉትን በተለይም ተለሳልሰው ጤነኛ መስለው በኅብረተሰቡ ማኅበራዊ የግኙኝነት ዕሴቶች ውስጥ ሠርገው በመግባት አደገኛ በሆነ መርዝ የመበከል ወይም የማፍረስ ወይም ዘርፎ የመጥፋት ልምድ ያላቸውን ወያኔያዊ ተግባሩን የሚያስፈጽሙ የአካልም ሆነ የስነ ልቡና እንዲሁም የታሪክ እስረኞችን ነው።
ቀደም ሲል በለንደን ከተማ ወያኔን በመቃወም ደረጃ ከፍተኛ የተደራጀ መዋቅር አለ ተብሎ የሚታመነውን እና የሚፈራውን ያክል፤ ይህን ኃይል ቀስ በቀስ ሳይታወቅባቸው ሰርስረው እየገቡ ያዳከሙ ብዙ የወያኔ ግብረ-በላዎች መኖራቸው በስም ዝርዝር መዝገብ የተያዙ በተጨባጭ ማስረጃ የሚታውቁ ሲሆን፤ ወደፊት ዝርዝራቸውንና ማንነታቸውን ይፋ እናደርጋለን ::ለዛሬው ግን ከእነዚህ መካከል እንዱ እንደበርሃ እባብ ውስጥ ውስጡን እየተርመሰመሰ ተመሳስሎ ስውሩ የህወሀት ወያኔ እንባ ጠባቂና ምልምል ካድሬ ከሆኑት ዋነኛዎቹ በለንደን ከተማ የሚኖረው የቀድሞ” የመኢሶን “አባል የነበረ ዮስያስ ታደሰ ነጋሽ የሚባለው ግለሰብ የቀዳሚነቱን ድርሻ ይይዛል።
ዮሲያስ ታደሰ ነጋሽ እባባዊ ስውር የካድሬነት ተግብሩ በወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ የተጸናወተውና አብሮት ያደገ መለያው ባህሪው ሲሆን፤ በደርግ ዘመን የመኢሶን አባል ካድሬ በመሆን በተለይም በጎንደር አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን እየጠቆመ ሲያስጨፈጨፍ የነበረ የንጹኃን ደም እጁ ጭብጥ ውስጥ የሚጮህበት ቀንደኛ ጥሎ የማለፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበተ ስውር ካድሬ ሆኖ የኖረ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ነባር አንጋፋ የኢህአፓ አባላት እስካሁን በፀፀት ያስታውሱታል።
በደርግ ዘመን ሲያከናውን የነበረው ቀደም ያለ የክፋት ስብዕና ብዙ ዘመን ያስቆጠረ በመሆኑ ላለንበት ወቅታዊ የተቀጣጠለ ሀገርን የማዳን እንቅስቃሴ የሚጠቅም ሳይሆን የግለሰቡን ስነ-ባህሪ ለማስታዎሻ ከመነሻው ለመጠቆም ከዳግም ስህተት ለመዳን ካልሆነ በስተቀር አስፈላጊነቱ የጎላ አይደለም ::ይሁን እንጅ ከዚህ ሲያያዝ በመጣው ልምዱ መሠረት አሁንም በወያኔ ዘመን ወደ ለንደን ከተማ የገባው የህውሀትን የካድሬነት ሙሉ ውክልና ይዞ እንደሆነ በማስረጃ የተረጋጠውና በውል የታወቀው ቢበዛ ከአምስት ዓመት አይበልጥም።
ዮሲያስ እንደተጠቀሰው የካድሬነት ባህሉን ከወጣትነት እድሜው ጀምሮ አብሮት ያደገ በመሆኑ ተመሳሰሎ ተለሳልሶ በቀላሉ ሠርጎ የመግባትን ልምድን ያዳበረና በረቀቀ ሥልት በአንጋፋ የወያኔ ሰላይነት ተመልምሎ ፓስፕርቱን በኢትዮጵያ ኢንባሲው በኩል እያሳደሰ በለንደን የሚኖር የካድሬነት ተግባሩን የሚያከናውን ስውር ሰላይ ሆኖ ሲያገለግል የኖረ ነው።
ዮሲያስ ከሌሎች ካድሬዎች የሚለይበት ባህሪው ከየተኛውም አቅጣጫ በስሙ የተጻፉ ደብዳቤዎች እንዲደርሰው ወይም ስሙ ያለበት ማንኛውም ዶክመንት እንዲቀመጥ ወይም ከወያኔ ጋር ሲመክር ሲናገር የሚያሳይ አንድም የፎቶም ሆነ የቪዲዮ ምስል እንዲታይ ወይም እንዲመዘገብበት አይፍለግም። ይህም አፈር ለብሶ ተሰውሮ ሳይታወቅ በስላላ መረብ ውስጥ ለመቆየት ከሚጠቀምበት ስልቱ ዋነኛው ዘዴ ነው።
ዮሲያስ ታደሰ ነጋሽ ተቃዋሚዎችን በቀላሉ ማጥመድ እንዲችል ከህወሀት በሚደረግለት ድጋፍ በለንደን ከተማ ሰሜናዊ ክፍል «ካሊዶንያን ሮድ» ተብሉ በሚታወቀው አካባቢ ምግብ ቤት ከፍቶ የምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦችን ከሀገር ቤት በሚስቱ በኩል በገፍ እያስመጣ በመነገድ ተለሳልሶና ተመሳስሎ የተቃዋሚዎችን ስነ ልቦና በመግዛት መርጃዎችን በቀላሉ በማሰባሰብና አሳልፎ በመስጠት ለረጅም ጊዜ ሲሰልልና የተጠናከረውን የተቃዋሚ የአንድነት ኃይል በረቀቀና ሥውር በሆነ መልኩ ሲያፈርስና ከለንደኑ ኢንባሲ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሠራ የወያያኔ አንጋፋ ካድሬ ነው።
ከጊዜ በኋላ የሚሠራው መሠሪ ተግባር ይፋ እየሆነና በሁሉም ዘንድ እየታወቀ ሲመጣ በከፈታቸው መግብ ቤቶች ተጠቃሚ የነበረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ሙሉ ለሙሉ ፣ዘመቻ በማድረግ ማዕቀብ ተደርጎበት የከፈተው ምግብ ቤቱ ሁሉ የዝንብ መዋያ ሆነ።
ይሁን እንጅ ዮሲያስ ከህወሀት ጋር ሥር የሰደደ ግኙነት ያለው በመሆኑ ለስለላ መረቡ ማጥመጃ አድርጎ የከፈታቸውን የንግድ ቤቶች በሙሉ በመሸጥ ለአገልግሎቱ ካሣ ይሆን ዘንድ በሚስቱ ስም የአበባ የእርሻ መሬት በርካሽ ዋጋ ገዝቶ የንግድ ሥራ የጀመረ ቢሆንም፤ አፍቃሪ ወያኔ የሆነችው ሚስቱ ንግስት አሊጋዝ መላ ገንዘቡን በቁጥጥር ሥር ካደረገች በኋላ በመንፈስም በሥጋም ታማኝ ልትሆለት አልቻለችም። እንደፈለጉ የሚዘርፉትን የትግሬ ካድሬ ባለሥልጣናት ልቧን ስላማለሏት ከዮስያስ ጋር ያለው ግኙኝነት በትዳር መልክ ሳይሆን የጌታና የሎሌነት ያክል እየተራራቀ መጣ።
በሰው ላይ ግፍ መሥራት ውሎ አድሮ በእራስ ላይ የሚደርስ በመሆኑ ተመሳስሎ በረቀቀ ሥልት ኢትዮጵያውያንን በመሰለል በወያኔ አጋፋሪነቱ የሰበሰበው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ በሚስቱ በመነጠቁ ዛሬ የታክሲ ሾፌር ሆኖ ከሚሠራው በስተቀር ምንም ዓይነት ምርጫ ሳይኖረው ድምጡን አጥፍቶ የቆየ ሲሆን፤ አሁንም የአንድነቱን ኃይል ውስጥ ውስጡን ከመሰለል፣ ከመቦርቦርና ከማፍረስ ወይም ደግሞ እንቅፋት ከመፍጠር አልተቆጠበም።
ዮሲያስ በአውሮፓ ተጠናክሮ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የመላው አማራ ድርጅት ውስጥ ውስጡን በመሰለል፣ መረጃዎችን ለወያኔ ኢንባሲ አሳልፎ በመስጠት በስውር ስም በማጥፋት ብሎም መዋቅራዊ መሠረት የነበረው የአንድነቱ ኃይል እንዲመናመን፣ እንዲዳከም እና በመጨረስሻም ውጤት አልባ እንዲሆን ካደረጉት ከሃዲዎች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ግለሰብ ነው።
ከላይ ከመግቢያው በዝርዝር እንደተጠቆመው ዮስያስ ታደሰ ነጋሽ በሁሉም አቅጣጫ ሳይታወቅበት ተመሳስሎ የመቅረብና ሠርጎ የመግባት ስውር የካድሬነት ባህሪ የተዋሀደው በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አካባቢም ነጠላ ዘቅዝቆ መንፈሳዊ መስሎ ብቅ በማለት አብዛኛው ሕዝብ የሚሰበሰበው በቤተ ክርስቲያን አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ስውር የህውሀት የመሠሪ ካድሬነቱን ሥራ ለመሥራት የተመቻቸና የተመረጠ ቦታ ሆኖ አግኝቶታል።
በወቅቱ የነበረው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ የሚሰበሰበው በለንደን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በወያኔ ዘንድ የተቃሚዎች ዋሻ በመባል እንድትመዘገብ ካደረጋት ሰዎች መካከል ዮስያስ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።
ይህ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ሆኖ ያመልከ የነበረና የተባበረ ኢትዮጵያዊ ክንድ አባላጫ ቁጥር ያለው ህወሀትን የሚቃወም ማኅብረሰብ በመበተንና ለሁለት ጎራ በመክፈል ተቃራኒ መፍጠር የወያኔ ተፈጥሮ፣ መሪ ዕቅድና ዓላማ በመሆኑ ይህን ተግባር ለማስፈጸም ተልዕኮ ከተሰጣቸው ስውር የወያኔ አንጋፋ ካድሬዎች መካከል ዋናው ዮሲያስ ታደሰ ነጋሽ ነው።
በዚህም ምክንያት በወቅቱ ከነበሩት የትግራይ ተወላጅ ጳጳስ ከሆኑት አባ ሙሴ እንዲሁም ተወልደ ገብሩ እና አቶ ዓይናለም ከሚባል የወያኔ ታማኞች እና ሌሎችንም አፈንጋጮችን በማሰባሰብ በግንባር ቀደም በማስተባበር የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ የሕዝቡን የአንድነት መንፈስ በማዳከም ደረጃ ለህወሀት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርገ ግለሰብ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የወያኔ ከኢትዮጵያ ተልከው የሚመጡትን ጳጳሳትን በማማከርና የኮሚቴ አባል ሆኖ በማስተባበር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ::
ዮሲያስ ታደስ ነጋሽ ዛሬ ወጣቱ በሚማርበት ትምህርት ቤቶች እና ከዩንቨርስቲዎች ጀምሮ በልዮ ልዩ የሥራ መስክና በማኅበራዊ የግኙኝነት ተቋማት እና በስፓርት ማዕከላት ሁሉ ወጣቱ ትውልድ እራሱን በእራሱ እያደራጀ እጅ ለእጅ ተያይዞ አስከፊውን የህወሀት አገዛዝ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በሚታገልበት ወቅት፤ ወጣቱን ለማጥመድና የሥር ነቀል ለወጥ ፋላጊነት ለማዳከም ከወያኔ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት በከፍተኛ ደረጃ ተንቀሳቅሷል :: በተለይም በወጭ ሀገር በአውሮፓ የኢትዮጵያ ስፓርት ፌደሬሽን ገንዘብ ዘርፎ የተባረረውና ሊቀመንበር በነበረው ፣ በአሁን ስዓት እህቱ የአንድ ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣን ሚስት የሆነችው ፣ ዮሀንስ መለስ የሚባል ግለሰብ ጋር በመተባበር የለንደኑን የስፓርት ፌዴሬሽን የጸሐፊነቱ ቁልፍ የሥራ ድርሻ ሰርስሮ በመያዝ፤ የወጣቱን የለውጥ አራማጅነት ወቅታዊ ብሔራዊ የለውጥ እንቅስቃሴ የሞራል ብቃት በስውር በመቆጣጠርና በማዳከም፣ ፌደሬሽኑ የወያኔ ሎሌዎች ማሰባሰቢያ ለማድረግ በሚችል እረቂቅ ዘዴ ሲሰራ መቆየቱን በመግለጽ ውስጥ አዋቂዎች በማህበራዊ የመገናኛ ብዙኃን እያሰራጩት ይገኛል።
ይህም በወያኔ ዘመን በእጅጉ፣የተጎዳውና የተመናመነው የማኅበረሰባችን ታሪካዊ ሠንሰለታዊ የግኙኝነት ባህሎች በተለይም በስደት ሀገር ሕዝባችን በመከራም በደስታም ተዛዝኖ፣ተፋቅሮ፣ ተረዳቶታና ተከባብሮ በአንድነት የመኖር ባህሉን መልሶ እንዳይጠግን የሚያመክን መሠሪ ታማኝነት የጎደለው ወያኔዊ ተግባር መሆኑን መረዳት ይኖርብናል።
ይህ በንዲህ እያለ ሰሞኑን የሀገራችን ወቅታዊ አጠቃላይ የለውጥ ፈላጊነትና ህውሀትን ከሥሩ ከእነ መርዙ መንግሎ ለመጣል በሚደረገው ሀገር አቅፋዊ የተጠናከረ እንቅስቃሴ በማዳመጥ፤ ለሀያ ሰባት አመታት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ከሚኖሩበት ቀያቸው በግፍ ሲፈናቀሉ፣ በጠራራ ፀሐይ አስከፊ በሆነ መንገድ ሲገደሉ፣ በሀገራቸው የመኖር ተስፋቸው ተሟጦ ዜጎች በየበርሃው ተሰደው ሲያልቁ የሚቀብራቸው አጥተው የአውሬ ቀለብ ሆነው ሲቀሩ፣ ሀገር ተረካቢው ወጣት በጀምላ እየታሰረ እራሱን እየተላጨ ሲደበደብና ለተላላፊ በሽታ ሲጋለጥ፣ የሰባዊ መብትና የፓለቲካ ለወጥ ፈላጊ አንጋፋ መሪዎች ታስረው ሲደበድቡ፣ ብልታቸው ሲኮላሽ መራር የሆነ ስቃይ ሲደርስባቸው፣ ሴቶች እህቶች ሳይቀር በእስር ቤት ጥፍራቸው እየተነቀለ የእራስ ፀጉራቸው እየተነጨ የሚዘገንን መከራ ሲቀበሉ፣ ታቦት በቆመበት ሕጻናት በመትረየስ ሲጨፈጨፉ፣ ካህናት በመርዝ ጢስ ሲታፈኑ፣ መነኮሳት ከገዳማቸው ውስጥ ታፍነው በእስር ቤት የመከራ ጽዋ ሲጎነጩ በስደት ሐገር የሚንከራተቱ ኢትዮጵያኖች በብርድና በበሮዶ ምሀል የእራሀብ አድማ እያደረጉ የወያኔን ስርአት በአለም አቀፍ መድረክ ሲጋልጡ ” የታጠቅ ኢትዮጵያ ” መሪ ነኝ በማለት እራሱን ያስተዋወቀን:: አቶ ዮሲያስ ታደሰን አይተነው አናውቅም ::
ምንም ዓይነት ድምፅ ሳያሰማ በለንደን የሚኖረው የህወሀት እንባ ጠባቂና ስውሩ ካድሬ ዩሲያስ ታደሰ ነጋሽ ሰሞኑን ተቃዋሚወች በጠሩት ስብሰባ ላይ መድረክ ላይ ወጥቶ ዘራፍ ያለበት ምክኒያት ለማናችንም ግልፅአይደለም ?:: ጥያቄውን ግን ለታዛቢው ህዝብ ትቸዋለሁ :: እኔ ግን በስብሰባው ላይ እንደታዘብኩት ፍጹም በሆነ ሐሰት ተመልቶ የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆንና ቢሳካም ባይሳካም አንድ ድርጅት ይዤ ተደራዳሪ ሆኜ ኢትዮጵያ እገባለሁ ብሎ የህልም ስንቅ ሰንቆ መሆኑ ግልፅ አድርጎልናል :: ያልጠረጠረ ተመነጠረ ይባል የለ ::
ሌላው የገረመኝ ግን ማንነታቸው ያልተገለፁ የወያኔን ካድሬዎቹን፣ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸውን ተራ ወሮበላዎችን ሰብስበው ፤ «ታጠቅ ኢትዮጵያ» የሚባል ለአሥር ዓመት በህቡ ስንታገል የቆየን ድርጅቶች ነን ማለቱ አስገርሞኛል ::
“በህቡ ” ለመሆኑ በህቡ የሚታገሉት የወያኔ አጋዚ ጦር መጥቶ እንዳይገላቸው ፈርተው ነው ? ወገኖቼ ? እኔ በስብሰባው እለት ይህን ገለፃ ሲያደርግ ስሰማ እራሴን ማመን አቃተኝ :: እናንተ ብትሆኑ ምን ትላላችሁ ? :: እሱ እንደሚለው የዚህ ድርጅት መሪ እንደሆነ በማስመሰል፤ አሁን ግን በይፋና በገሀድ እየተንቀሳቀሰ እየታገለ የሚገኝ መሆኑን ሳያፍር በድፍረት በመድረክ ላይ ሲቃዥ አይተነዋል። ይህም እንደተለመደው ተቆርቋሪ መስሎ ሠርጎ በመግባት ተፋፍሞ፣ በየአቅጣጫው የሚንቀስቀሰውን የለውጥ ኃይል ለማደናገር ለመከፋፈል የህወሀት ካድሬነቱን ተግባር ለማስፈጸም ከህውሀት ይልቅ በግልፅ እራሱን ይፋ እያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ጉልህ ማስረጃ ነው።
ህወሀት በየአቅጣጫው ተጠናክሮ የሚደርስበትን የተጠናከረ ኃይል ከፍተኛ ጥቃት ለማዳፈን ለመከፋፈል በተለይም በውጭ ሀገር ያለውን የተቃዋሚ ኃይል በልዩ ልዩ ዘዴዎች ተመሳስሎ አፍኖ ለመያዝና ለማኮላሸት ከፍተኛ መጠን ያለው የውጪ ምንዛሬ በመመደብ እንደ ዮሲያስ ታደሰ ነጋሽና መሰል ካሀዲዎች
ተልዕኮ እየሰጠ ነው :: አዛኝ ቅቤ አንጏች እንደሚባለው ሁሉ ፣ በስሩ በሚታዘዙ አፍቃሪ ወያኔዎች ለንደን ላይ ቀይ ምንጣፍ አንጥፈው በእርዳታ ስም ሕዝብን ለመዝረፍ የተጀመረውም ዘመናዊ ሌብነት ፣ ህብረተሰቡ እነማን እንደሆኑ አይኑን ከፍቶ ሊከታተለው የሚገባ ጉዳ መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም :: እነዚህ ወገኖች ህብረተሰቡ በሚሰበሰብባቸው ማኅበራዊ የአንድነት ተቋማት ጥርሳቸውን እየገለፈጡ ተለሳልሰው ሠርገው በመግባት ማኅበረሰባችን ግራ በማጋብት የትግል አቅጣጫውና ኢትዮጵያዊ ስሜቱን ለማጨለም፣ በማደናገር የሐሰት ወሬዎችንና ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያሰራጩ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ አምስት ለአንድ የተደራጁ የወያኔ ሎሌዎች ለንደን ላይ እንደልባቸው እዬፏለሉ ይገኛሉ ።
ወደፊት ባንዳዎች እና ካድሬዎችን በዝርዝር የሚያጋለጡበት አምድ ከፍተን አንድ በአንድ ስማቸውን እየጠራን በተጨባጭ ማስረጃ የህወሀት ካድሬዎችን የማጋለጡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ትግላችን መጀመር ያለበት ካፍንጫችን ስር ያሉትን መርዘኛ ከድሬዎችን ሐሰተኛ ግበረ በላዎችን ለሕዝብ ማጋላጥና ከአጠገባችን የማጽዳት ተግባር የሚያጠቃልል መሆኑ ሊታመበት ይገባል። እነዚህን መርዘኞች አንድ በአንድ በማጋለጥና በየትኛውም ማኅበራዊ የግኙኝነት መድረኮች ምንም ዓይነት የኃላፊነትና የታማኝነት ድርሻ እንዳይኖራቸው በማድረግና የህወሀትን የስለላ መረብ መበጣጠስ ገዴታች ነው።
ስለዚህ ህወሀትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሽቀንጥሮ ለመጣል ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባትን ሀገራችን ኢትዮጵያን መጠነ ስፊ የሆነ አድሎ መከፋፈል፣ ስደት፣ ግድያ፣ የጀምላ እስራት፣ ስቃይና እንግልት የሚፈጸምበትን ሕዝባችንን መልሶ በአንድነት ለማቆየት በኢትዮጵያዊ ታሪክ አሻራ መሠረት ላይ የታነጸ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመተካት የሚደረገውን ሀገር አቀፋዊ ትግል መተባበር በተለይም ቄሮ፣ ፋኖ፣ ነብሮ፣ ዘርማና የመሳሰሉትን ትኩስ ኃይሉን የወጣቱን የተጠናከረ ትግል በሚቻለው መጠን ሁሉ በመርዳት ግፈኛውን የህወሀት ትግሬ አገዛዝን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሥሩ መንግሎ ለመጣል የተባበረ ክንዳችን የሚጠይቀበት የቁርጠኝነት ጊዜ አሁን ነው። በመጨረሻም ማሳሰብ የምወደው ተቃዎሚዎች እንዲጠነቀቁና ቤታቸውን እንዲፈትሹ ነው ::
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር፤
ሙላቱ ተመስገን
ከለንደን፤
