በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።” ኤር31:15
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከሚመራው በስደት ላይ ከሚገኘው ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራችን ኢትዮጵያና በሕዝባችን ላይ አሸባሪው ወያኔ እያደረሰ ያለውን ገደብ የለሽ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ፤
ሀገራችን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የውጭ ወራሪ ኃይሎችና በተለይም በፋሽሽት ጣልያን ወረራ የደረሰባቸው ከባድ የመከራ ዓመታት፡ አሁን በዘረኛው የወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ እየደረሰባቸው ካለው ግፍ ጋር ሲነፃፀር የአሁኑ የወያኔ አረመኔያዊ የጭቆና አገዛዝ ከሁሉም እጅግ የባሰና የከፋ ተወዳዳሪም ያልተገኘለት በዚህ ጊዜ ይረሳል የማይባል የታሪክ ጠባሳና ከባድ ቁስል መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው።
ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት ታፍራና ተከብራ፡ የውጭ ጠላትንም አሳፍራ ሕያው ታሪክን በማስመዝገብ በዓለም የታወቀች የጀግኖች ሀገር መሆንዋን ታሪክ የሚመሰክረው እውነት ነው። አሁን ግን በኢትዮጵያዊነት ስም የኢትዮጵያዊነት መልክ እንጂ፡ የኢትዮጵያዊነት ሞራል ስሜትና ባሕርይ በሌላቸው የሀገራችንን ታሪክና ሕዝባችንንም አጥፍተው ለመጥፋት በተቀጠሩ ባንዳዎች ሀገራችን በጥፋት፡ ሕዝባችንም በሞት የገደል አፋፍ ላይ ይገኛሉ። …. (Read more)

