ሰኞ March 05/2018
ሰዓት : 9:00 AM
ቦታ : State Department
አድራሻ: 2201 C St NW
Washington, DC. ላይ
የወያኔ ባለሥልጣናትን እግር ከወርች የሚያስረው፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ ለ27 ዓመታት ሲፈጽሙብን ለኖሩት ኢሰብአዊ ግፍ ክህደት ወንጀልና ዝርፊያ ተጠያቂ የሚያደርገው፣ ሕዝባዊ ትግሉን ለአንጸባራቂ ድል የሚያበቃው የHR. 128 ረቂቅ ሕግ እንዲጸድቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠትና ጫና ለማሳደር ደማቅና ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል፡፡
አደራ! ቀጠሮው እጅግ ወሳኝና የሞት የሽረት በመሆኑ በሰሜን አሜሪካ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የፈለገ ግላዊ ጉዳይ ቢኖርባቹህ “ከዚህ የሀገራችንና የሕዝባችን አንገብጋቢ ጉዳይ የሚበልጥ ነገር የለም!” ብላቹህ ንቅል ብላቹህ በመውጣት ሰልፉ ላይ እንድትገኙ በመከራና በሰቆቃ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በፈጣሪ ስም ይማፀናቹሀል???
የሚረባም የማይረባም ምክንያት እየጠቀሳቹህ ሰልፉ ላይ ላለመገኘት ያሰባቹህ ወገኖች ካላቹህ እጅግ እጅግ ያስተዛዝበናልና አደራ በሰማይ አደራ በምድር እንዳትሞክሩት???
እዚህ ሀገር ውስጥ ያለው ሕዝባቹህ ከግፍ አገዛዙ ነጻ ለመውጣት ስንት መራራ ዋጋ እየከፈለ እያለ እናንተ በሚረባና በማይረባ ምክንያት ሰልፍ ላይ ለመገኘት ከከበዳቹህና ካቃታቹህ በእውነት እራሳቹህን እንደ ሰው አትቁጠሩ! ፣ የማስብለት ሕዝብ፣ ወገን፣ ዘመድና ቤተሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ አለኝ እንዳትሉ! ፣ የምወዳት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብላቹህ ስሟን እንዳትጠሩ! ፣ ፊታቹህን ወደ ኢትዮጵያ እንዳታዞሩ!!! እንደ ዜጋ ባላቹህ የዜግነት ግዴታ ስንት ነገር ማድረግ ሲጠበቅባቹህ ይህችን ትንሽ ነገር ማድረግ ከተሳናቹህ መኖራቹህ ምን ሊረባን!!!
እናም እባካቹህ አደራ! ሰልፉ ላይ እንድትገኙ! እንዳትቀሩ!!! የቻላቹህ እንዲያውም ልጆቻቹህንም ይዛቹህ ተገኙ??? እግዚአብሔር ይርዳን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
