ይህ ጀግና ህዝብ በልፋቱና በጥረቱ ያካበታቸዉን ኢትዮጵያዊ ኩራቶቹን እንንጠቅህ ቢባል እንቢኝ አሻፈረኝ በማለቱ በብርቱ እየተደቆሰ ይገኛል ዛሬ ጉራጌ ልጆቹን ሁሉ አሰናብቶ ሂድ ከዘርማ ጋር ሐገርህን ነጻ አዉጣ ኢትዮጵያ ሳትጠፋ ድረስላት ያለበት ምክንያት ምንድን ነዉ?
በደሎቹ . . .
1. ጉራጌ በህዝብ ቁጥር ብዛት በህወሃት ወያኔ መጭበርበር ተደርጎበት ከአጠቃልይ ሐገራችን ኢትዮጵያ ማግኘት ይገባዉ የነበረዉን መብት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ተነጥቋል።
2. ማንኛዉም የጉራጌ ማሕበረሰብ ምንም አይነት ጉዳዮችን ማስፈጸም ቢፈልግ ከሚኖርበት ቀየዉ ተነስቶ አዋሳ ድረስ በመሄድ በቋንቋ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጉላላ ከመሆኑ በተቸማሪ አላስፈላጊ ለሆኑ የግዜ የገንዘብና የጉልበት ብክለቶች እየተዳረገ አመታትን አስቆጥሯል። በተለይም በአዋሳ የቢሮ መስተንግዶ ላይ በሚደርስበት ቢሮክራሲ ምክንያት እጅግ የተማረረ ሲሆን ጉዳዩ በህዝብ ፍላጎትና እድገት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል እያደረሰም ሲገኝ ሁኔታዉ በጉራጌ ህዝብ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እና እድገት ላይም አሉታዊ ተጽኖ አሳድሯል፤፤
3. በአጠቃላይ በሐገራችን ደረጃ ሁሉም ብሄሮች በቴሌቶን ገንዘብ ሰብሰብስበዉ የተወለዱበትን ቀየ እንዲያለሙ ሲደረጉ የጉራጌ ማሕበረሰብ በቴሌቶን የሰበሰበዉን 283 ሚሊዮን ብር በላይ በህወሃት ወያኔ በመነጠቁ እና ገንዘቡ የት እንደገባ እንዳይታወቅ ሆን ተብሎ ደባ ተሰርቶበታል። ያንን ያህል ገንዘብ የሰበሰበዉ የጉራገ ህዝብ በመሰረተ ልማት እድገት ዘርፍ ላይ ምንም ለዉጥ ሳያመጣ የባሰዉን በከፍተና ችግር ላይ ሲገኝ 283 ሚሊዮን ብር እንዳይጠይቅ በአስገዳጅ ሁኔታ ታፍኖ ኖሯል።
4. ባጠቃላይ በጉራጌ ክልል ላይ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ የ አጣጥ ሆስፒታል ብቻዉን በሚገኝበት ሁኔታ ጉዳዩ ያሳሰባቸዉ ወገኖች በቀረጹት ፕሮጀክት አማካኝነት በአለም አቀፍ ካቶሊክ ቤ/ክርስቲያን በጎ ፈቃደኝነት በከፍተኛ ሚሊዮን ዶላር ተመድቦለት ሊገነባ ፈሰስ የተደረገበት የወልቂጤ ሆስፒታል መሰረተ ልማቱ ወደ ትግራይ እንዲዘዋወር በመደረጉ የጉራጌ ህዝብን ጨምሮ መላዉ ኢትዮጵያዊያን ልባችዉ ተሰብሯል
5. ከምርጫ 97 በኃላ የህወሃትን ቡድን ያልመረጠዉ የጉራጌ ህዝብ በስረቱ ከፍተኛ ቂም ስለተያዘበት ከአጠቃላይ የሐገራቱ ከስራና ከንግድ ዘርፍ እንዲወገድ ተደርጓል። በዚህም የተነሳ ከአነስተኛ የስራ ዘርፎች ጀምሮ እስከ ትልልቅ መደብሮችና ድርጅቶች ከጉራጌ ህዝብ ተነጥቀዉ ለስርአቱ ደጋፊዎች በችሮታ መልክ ተላልፈዉ ተሰጥተዉበት እንደ መርካቶ ከመሳሰሉት የአፍሪካ የንግድ ማእከላት ላይ እንዲወገድ ተደርጓል። ይህ ተንኮልና ደባ ጠናካራዉና የኢኮኖሚ አለኝታ የነበረዉን የጉራጌ መሐበረሰብ በታሪኩ አይቶት የማያዉቀዉን ስደት እንዲጠናወተዉ ከማደረጉ ባሻገር የግንቦት 7ደጋፊ እየተባለ በደረሰበት ስፍራ ሁሉ
በእስር በድብደባና በእንግልት እንዲሰቃይም ተደርጓል እየተደረግም ነዉ
6. በመላዉ የጉራጌ ክልል ሊባል በሚችል ሁኔታ ከአዲስ አበባ በአንድ መቶ ኪ/ሜ ቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘዉ የጉራጌ ህዝብ መብራት ተነፍጎት እንደ ዘመነ ጋርዮሽ ዛሬም ድረስ ኩራዝ እየተጠቀመ ባለበት ሁኔታ በብዙ ሺዎች በሚቆጠር እርቀት የምትገኘዉ የትግራይ ክልል ብቁ የኤሌክትሪክ መጠን እየፈሰሰላት በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከአፍሪካ ተጠቃሽ ሆና ሳለ ሱዳን እና ኬንያ ከጉራጌ ህዝብ በልጠዉ በመገኘታቸዉ ገመዱ ተወጥሮላቸዉ ለተመለከተ ህዝባችን ያለበትን ችግር መገመት አይዳግተዉም
7. በመጠጥ ዉሃ አቅርቦት በኩል ጨርሶ የለም በሚባል መልኩ እናቶች ዉሃ ሊቀዱ በሄዱበት ከእነ እንስራቸዉ ወድቀዉ እንደሚቀሩ እወነታዎች ያረጋግጣሉ ዛሬም የጉራጌ ህዝብ ከከብት ጋር እየተጋፋ ዉሃ ሲቀዳ መመልከቱ ልብን የሚነካ ጉዳይ ነዉ።
8. በትምህርት ደረጃ ከፍተኛ ዉጤቶችና ደረጃዎችን በማስመዝገብ ጥሩ የማለፊያ ዉጤት በማምጣት ጭምር የሚታወቀዉ የጉራጌ ህዝብ ዛሬ ከሁሉም ጀርባ ጭራ ጨባጭ ሆኖ እንዲጓዝ ተደርጓል። በመላዉ ሐገራችን ላይ እዉን ሆኖ በመተግበር ላይ የሚገኘው የትምህርት ፖሊሲ ህዝባችንን ከመደቆሱ በተጨማሪ በክልሉ ላይ አንድም ደረጃዉን የጠበቀ ላይብረሪ ባለመኖሩ በአጥንቶ ማለፍ ሂደት ላይ ትልቅ ሳንካ ፈጥሮበታል።በገጠር የሚኖሩ ህጻናት በትምህርት ቤቶች እረቀት ምክንያት ዛሬም ድረስ ትምህርት ያልቀመሱ ከመሆኑ ባሻገር አቅማቸዉ ይችላሉ የተባሉት በእግር እረጅም መንገድ ተጉዘዉ በድካም ምክንያት ደረጃዉ የወረድ ትምህርት ቤ/ት ዉስጥ አንቀላፍተዉ ወደ ቤት ሲመለሱ የሚደርሰባቸዉ ድካምና መከራ በቀለም ትምህርቱ ላይ በርትተዉ እንዳይቀጥሉ አድርጓቸዉ ትዉልዱ ባክኖ ቀርቷል።
9. በህወሃት ትእዛዝ በአማራዉ ክልል ላይ በተፈጸመ አይነት የዘር ማጥፋት ወይም ማምከን ሂደት ላይ ከፍተኛ ስራ በመሰራቱ እናቶች በድጋሚ እናዳይወልዱ ተደርገዉ ዘር አልባ ሆነዋል
10. በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ፊት አዉራሪ የነበረዉ ጉራጌ በነ ወልደ ስላሴ በረካ የጉራጌ ህዝቦች መንገድ ስራ መሐበርን መስርቶ ለኢትዮጵያ የመንገድ ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጭምር አጋር የነበረ ህዝብ ዛሬ በመንገድ እጦት ምክንያት እንዲንከራተት ተደርጓል። በተለያዩ አመታት ላይ በደቡብ ክልል ስር በጀት የሚበጀትለት የጉራጌ በትራንስፖርት ችግር የመጣ በንግድና በተለያዩ መንገዶች የሚያገኛቸዉ ኣምንኛዉም ጥቅማ ጥቅሞች የሌለዉ ሲሆን በወሊድ ወቅት እናቶች በምጥ ሲኣይዙ እንኳን ትራስፖርት ባለመኖሩ ብዙሃን ከነልጆቻቸዉ ተቀጭተዋል እየተቀጩም ነዉ።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ባጠቃላይ ይህ በጥቂቱ በጉራጌ ህዝብ ላይ የተፈጸመ ግፍ በሁላችንም ላይ እንደተፈጸመ ዘርማ ጠንቅቆ ያዉቃል። በመሆኑም ዛሬም ከላይ የዘረዘርናቸዉ መብቶች እንዲከበሩ በሰላማዊ ትግል ብንጤይቅም የተሰጠን ምላሽ ኮማንድ ፖስት ሆኖ በማገኘታችን የተሰማንን ሐዘን እየገለጽን ከእንግዲህ መላዉ የጉራጌ ህዝብ ከመላዉ የኢትዮጵያን ወገንህ ጋር በመተባበር 1 ለ 5 እየሆንክ በመደራጀት እራስህን ተከላከል! መብትህን አስከብር! ሐገርህን ነጻ አዉጣ !።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ድል ለዘርማ!
