06/03/2018

ስለሺ ሙላቱ

በጎጃም የዱርቤቴ ነዋሪ የሆኑትን ደርቤ አየለን ለመያዝ የትግራይ ነፃ አውጪው ሕገወጥ ኮማንድ ፖስት ሠራዊት ወደቤታቸው አቀና፤ እጅ እንዲሠጡም ጠየቃቸው። ሆኖም ጀግንነት ያደገበት ነውና ደርቤ መልስ የሰጣቸው የተወለወለ መሣሪያውን ደግኖ አመልካች ጣቱን ምላጭ ላይ በማሣረፍ ነበር። የለመደች ጣቱም አላሣፈረችውም፤ የተኩስ ድምፅ ከመሠማቱ ከተቃራኒው አቅጣጫ ከገዳይ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ተዘረረ። ደጋግሞም ተኮሰ። የተኮሠው ሁሉ በጠላቶቹ ላይ እንዳረፈ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። የቀደሞው የኢትዮጵያ ጀግና ሠራዊት አባል ነውና። አልሞ መጣል፤ ተኩሦ ማሥቀረት የሠለጠነበት፣ የደገበትና የካበተው ልምድ ነውና ሙትና ቁሥለኛውን ከመረው። ስምን መልአክ ያወጣዋል እንዲሉ ደርቤ ጠላቶቹን ደራረባቸው።
ደርቤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ጀግና አባል መሆኑን አስቀድመው ያወቁ አይመስለኝም።አውቀው ቢሆንማ በጉራጌ ዞን ያሠለፉትን ታንክ በእጥፍ ባሠለፉ ነበር። የወያኔ ሠራዊት ከ27 ዓመታት በፊት የረሡት የደርቤ ክንድ እንደገና ሲያርፍባቸው ምን እንደተሠማቸው መገመት ለማንም ዳገት አይሆንም። ግዳይ ሊጥል የሄደው ጭዳ ሆኖም የጀግናውን የሚፋጅ እጅ ለመያዝ አልታደለም። የገደለውን ገሎ ቀሪውን አቁሰሎ የደም ውርስ አለበትና የጀመረችውን ጣቱን ለመጨረሻም ትዕዛዝ ሠጣት ምላጩን ሣበችው። ይሕኛው ግና አፈሙዙ ከጠላት በተቃራኒው ነበር። እናም የቴዲን የክብር ሞት ተጋራ። እራሡን ለኛ ቤዛ አድርጎ ነፍሡ ወደ ገነት ሥጋው ወደ ተሠራበት ወደ አፈር ሊመለስ ተሠነባበቱ።
እዚሕጋ ልብ እንበል ትናንት ለሀገሩ ተዋድቆ ሣለ ያ ሁሉ በደል ሲፈፀምበት “የተዋደቅኩለትና የላከኝ ሕዝብ ዞር ብሎ አላየኝም” በሚል ዝም አላለም። ዛሬም ለዚሕ ትንታግ ትውልድ ምሣሌ ሆኖ በክብር ተሠዋልን። ከኛስ ምን ይጠበቃል? መቼ እነደምንሞት ቀነ-ገደብ ላልተሠጠንና ለማይቀር ሞት እንደዚህ የክብር ሞት መሞት ሕያውነት ነው። ጀግናው ደርቤ ሀገራችንን ከትግራይ ወራሪ ነፃ ለማውጣት ይታገል እንደነበረ አስረጂ የሚያሻን አይመስለኝም። አንድ ቀን የሆነው ሊሆን እንደሚችል ስለሚያውቅም ነው ያለቀጠሮ የሞት አለያም የቁም ሥቃይ ደግሠውለት እንዲታደም የጋበዙትን ተዘጋጅቶበት ያስተናገደው። አኩሪ ገድል። ሁሌም ሲዘከር የሚኖር ለቤተሠብና ለወገን የሚያኮራ ተግባር ከውኖ መሞት ታላቅነት ነው። እርግጥ ነው ሀዘኑ ልብ ይሠብራል። ነፍስ ይማር፤ ለቤተሠቡም ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጥ። ምንጊዜም አንረሳሕም።

ዘራፍ ዘራፍ
እታይቤት ያላችሁ እላይቤት ያላችሁ
ወያኔን ዘረረው ጀግናው አባታችሁ
አባቴን ሸኙልኝ ወርቁን አጥፍችሁ
የተጋሩ ልጆች አገደፉላችሁ
እልልበል ጎጃሜ ከግድህ በሃላ አይመጣም ሰፈርህ !
አላወቀም ነበር የዛ የቆፍጣናው የበላይ መሆንህ!!

ታውቅበታለህ በፍቅር ለመጣ እግዳ መቀበል
ማኛውን አሲዘህ ማር ቂቤውን ቀድተህ
ሊገልህ ሲመጣ እድህ እያደረክ ትቀጣልኛለህ!!!

የወንድማችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም።

ሞት ለትግራይ ነፃ አውጪ!!

ሊያፍኑት ከመጡት 55 የአጋዚ ወታደሮች 13 በመግደለ የተሰዋው የ72 ዓመቱ አዛውንት መቶ አለቃ ደርቤ አየለ

 

(ናትናኤል መኮንን)

የአርበኛ እና ጀግናው የመቶ አለቃ ደርቤ አየለ የቀብር ስነ ስርዓት በድምቀት ተከናወነ።

የ72 አመቱ አዛውንት አርበኛ እና ጀግናው የመቶ አለቃ ደርቤ አየለ

የህወሓት ት ወታደሮችና ባንዳዎች የካቲት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ለሊት ላይ ሲሆን በሰሜን አቸፈር ድርቤቴ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን የመቶ አለቃ ደርቤ አየለን ከመኖሪያ ቤታቸው ለማፈን 55 ሆነው የሔድትን የህወሓት ኃይሎች 13 ቱን በመግደል ከ30 በላይ በማቁሰል ከፍተኛ ጀብድ በመስራት ራሳቸውን ሰውተዋል።

የመቶ አለቃ ደርቤ አየለ የ72 ዓመት እድሜ ባለፀጋ የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል በሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን በመቃወም በድር ሲታገሉ ከቆዩ በኃላ በቀድሞው መንግስት ማለትም በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን ከፍተኛ ጀብድ ሰርተዋል በቀድሞው መከላከያ ሰራዊት ለ11 ዓመት ያገለገሉ ሲሆን በመጀመሪያ የ6ተኛ ክፍለ ጦር 14ተኛ ሻለቃ አባል በመሆን አኩሪ ታሪክ ሲሰሩ ቀይተው በመጨረሻም ወደ ኤርትራ አስመራ በመቀየር የ31ኛ ክፍለ ጦር አባል በመሆን ቡዙ ጀብዶችን ሰርተዋል በዚህ በሰሩት ጀብድ እንዳሁኑ ሳይሆን ማዕረግ እጅግ ውድ በሆነበት ወቅት ከምክትል የአስር አለቃ እስከ መቶለቃ ማዕረግ ደርሰዋል።

ከደርግ ውድቀት በኃላ ወደ ትውልድ ቦታቸው በመመለስ በግብርና እና በንግድ ስራ በመሰማራት ኑራቸውን የሚመሩ የነበረ ሲሆን እሳቸውም የአገሪቱ ሁኔታ እጅግ እያሳዘናቸውና በዘር በመከፋፍል ታሪክን ህወሓት ሲያበላሸው እጅግ ይቆጩና ያዝኑ ነበር ። በዚህም ምክንያት ህወሓቶችና የእሱ ጉዳይ ፈፃሚ የሆኑ ብአዴኖች እየተከታተሉ ያስቸግራቸው ነበር ፡ የኒህ ሰው ተሰሚነትና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው ያሳሰበው ወያኔ የካቲት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ከ55 በላይ የሚሆኑ ወታደሮቹን እና ፀረ ሽምቅ አባሎቹን አስከትሎ ወደ መኖሪያ ቤታቸው የሔደ ሲሆን ፖሊስ አዛዡ የመኖሪያ ቤታቸውን በርግዶ ሲገባ በፍጥነት ተኩሰው ግንባሩን በመመታት ሲገድሉት ተከታትለው የመጡትን 9 የመከላከያ አባላትን ተኩሰው ገድለዋል።

ከዚያም ከ30 ደቂቃ በላይ ከተታኩሱ በኃላ ጥይት ሲጨርሱ በያዛቸው ቦንቦች ከ30 በላይ የህወሓት ኃይሎችን ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል እነዚህ የቆሰሉ የህወሓት የፀጥታ ኃይሎች እጅና እግራቸው ተቆርጠው በባህርዳር ፈለገ ሔይወት ሆስፒታል ተኝተው ይገኛሉ።

በመጨረሻም በስልት እጃቸውን ከሰጡ በኃላ “እጅ ስጥ አለኝ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ፡ አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ ” በማለት ህወሓቶች የማረኩና በቁጥጥር ስር የዋሉ መስላቸው በደስታ ስሜት ወደ ተሽከርካሪ እንዳወጣቸው እኒህ ጀግና በኪሳቸው ደብቀው በያዛት የእጅ ቦንብ ከበው የያዛቸውን 4 የህወሓት ወታደሮቹን ጨምሮ እሳቸውን አጥፍተው በመስራት በጠላት ሳይሆን በራሳቸው እጅ ራሳቸውን አጥፍተዋል።

በመሆኑም የእኒህ ጀግና የቀብር ስነስርዓት የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሳዓት ሲሆን ዘመድ ወዳጆቻቸውና ጀግና አክባሪ የሆነው ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በተገኘበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅማል የ መቶ አለቃ ደርቤ አየለ ባልትዳር የነበሩ ሲሆን የ8 ወንዶችና የ2 ሴት በድምሩ የ10 ልጆል አባት ነበሩ ።

ከኒህ ጀግና ሁላችንምጠቡዙ ትምርት በመውሰድ ትጥቄን አልፈታም ለዘረኛና ለባንዳ እጄን አልሰጥም በማለት የሰሩትን አኩሪ ተጋድሎ በመቀበል የሞቱለትን አላማ ከግብ ለማድረስ እድንረባረብ ጥሪ እያቀረብን ፡ የኒህን ጀግና ገድል እና ታሪክ በቀጣይ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን ።
ድል ለሕዝብ !!!