March 6, 2018
ሰሞኑን እየወጡ ያለ አንዳንደ አስተያየቶች እየሆነ ያለውን ተቃራኒ ነው፡፡ ለማ በበአዴን ተከዳ ከእንግዲህ ዋጋ የለውም ምናምን የሚሉ ወሬና አስተያየቶች ሲሰጡ እያየን ነው፡፡ እውነታውን ማስተዋል ካለመቻል ይሁን ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት ባይታወቅም ግን እኛ በለማና ቡድኑ አሁን እየሆነ ያለው ከመቼውም በላይ እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ እያየን ነው፡፡ ለማ ዛሬ ብቻውን አደለም፡፡ ሚሊዬን ሕዝብና ቆራጥ የሥራ አጋሮቹ ከጎኑ ናቸው፡፡ ለማ ዛሬ እራሱን ሚሊዮን ያረገ ሰው ነው፡፡ ወያኔ የምትይዝ የምትጨብጠውን አሳጥቷል፡፡ ለማ የአመክንዮዋዊ(ሎጂካል) ፍልስፍና ፖለቲካ መሪ እንጂ የድርጅታዊ አማላኪ ፖለቲካ መሪ አደለም፡፡ ከለማ ጋር ዛሬ ሁሉም እየተግባባ ያለው ፍልስፍናው ተፈጥሮአዊ ስለሆነ ነው፡፡ በአለፉት 50 ዓመት ያልታየ የፖለቲካ ጥበብ ይዞ ስለመጣ በድርጅታዊ እኩይ አላማ አምልኮና የሰይጣን ባሪያ በሆኑት ዘንድ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የማይሆነባቸው የእውር ድንብራቸውን አስቀርቶ በራሳቸው ጊዜ በነው ወደሚጠፉበት ሲኦል እያበነናቸው ነው፡፡
ላለፉት 50 ዓመታት የክፉ ፍልስፍና ልክፍታቸውን እያመለኩ ብዙ ፖለቲከኙች ተነስተዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ዘመን አገርንና ሕዝብን ወደ አዘቅት ጨምረዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ለማ አገርንና ሕዝብን ከአዘቅት ለማውጣት የሚያስችልን ልዩ ፍልስፍና ይዞ የመጣው፡፡ ብዙ ኦሮሞ አባቶቹ በደምና አጥንታቸው የአኖሯትን አገር ክዶ አባቶቹን እየረገመ የገዳዮቹን ሀሳብ ተቀብሎ ኢትዮጵያዊነቱን መቀለጃ በሆነበት ጊዜ ነበር ለማ ከአባቶችህ አገር ውጭ አገር ከኢትዮጵያዊነትህ ውጭ ሌላ ማንነት የጠላቶችህ ሴራ እንጂ የአንተ አደለም ብሎ ለማ በአባቶቹ መንፈስ የመጣው፡፡ ብዙዎች ያልገባቸው ለማ ጉልበቱና ኃይሉን ከጀግኖች አባቶቹ መንፈስ የወረሰው እንደሆነ ነው፡፡ አሁን የምናስተውለው እውነት ደግሞ ለማ ብቻም ሳይሆን ብዙዎች ናቸው፡፡ ለአለፉት በርካታ አመታት በአመክንዮአዊ ፖለቲካ በወጥነት የቆመው ፕ/ር መረራ የዘመናት ሕልሙ የተሳካለት ይመስላል፡፡ ይህን ዛሬ ለማ ከአፈር ላይ ያነሳውን የአባቶቻችንን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ዛሬ ላይ መላው የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ከፍታ እየመለሰው ነው፡፡ ዛሬ ላይ የኢትዮጵያዊነት ቁርጠኝነት እየመጣ ያለው ከዚህ ሕዝብ በመጡ ጠንካራ ፖለቲከኞች ነው፡፡ የመረራና በቀለ ነገር ወያኔን ከመጀመሪያውም ፈርታው ነበር፡፡ የፈራችው አልቀረም አውነታው አሁን ፈጥጦ መጥቷል፡፡ ተቃዋሚ የተባለው ኦፌኮ እና የወያኔው ቡድን በአባልነት እየሰራ ወያኔን ከመሠረቷ እያፈረሳት ያለው የለማ አዲሱ የኦፒዲዮ ቡድን እየተመራ ያለው በልዩ ፍልስፍና በመጡ መሪዎች ነው፡፡ ዛሬ ሕዝብ በእነዚህ መሪዎች እየተመራ ነው፡፡ ፍልስፍናቸውን ቀምሶታል ከዚህ በኋላ የወሮበላ ወንበዴ ሴራ አቅም የለውም፡፡ እየሆነ ያለው ይህ ነው፡፡
ይህ አውነት ሳይታያቸው ሥጋት ሆኖባቸው ይሁን በሕቡዕ የእነ ለማ አዛኝ በመምሰል የወንበዴው ወሮበላ ወያነን ለመታደግ የሚነዛ ፕሮፓጋንዳ ባይገባኝም ሰሞኑን ለማ ብቻውን ቀረ በአዴን ከዳው፡፡ ደመቀ መኮንን ከዳው ጉድ ሰራው የሚሉ ወሬዎች እየናኙ ነው፡፡ ሲጀምር እንደነ ደመቀ መኮንን ያሉትን ሆድ አደሮች ለማ ከመሠረቱ ያውቃቸዋል፡፡ አንዴ በሱማሌ የወሮበላው ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመጎብኘት ሄደና ደመቀ መኮንን የእነለማ ወዳጅ መስሎአቸው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ ሲጀምር ሄደ የተናገረውን አወራ እንጂ አንድም ነገር ያደረገው ነገር የለም፡፡ ደመቀ የወሮበላው ወያኔ ቅጥር እንደሆነ ለለማ አልጠፋውም፡፡ ግን በአማራና ኦሮሞ ሕዝብ መካከል እንዲኖር የፈለገውን ሕብረት ለማሳካት ሲል በዓዴንን ከወከሉ ጋር አድር ባይም ቢሆኑ አገልጋይ እስከሆኑ ድረስ ሊጠቀምባቸው እንጂ፡፡ ከበዓዴን ከገዱ በቀር ሌላ ሰው ምን ያህል እንዳለ አናውቅም፡፡ አነሰም በዛም ጥቂት ሰዎች ይኖራሉ፡፡ በአለፈው አርብ ስብሰባም እንዳይገቡ የተደረጉ እንደነበሩ እናስባለን፡፡ ምክነያቱም ከገቡ የወሮበላውን ጸረ-ህዝብ አዋጅ እንደሚቃወሙት ሲለሚታወቅ፡፡ ከኦፒዲኦም ብዙ የቀሩ እንዳሉ ይታሰባል ልብ በሉ 106 ዓባል ነው በዚህ ወሳኝ ስብሰባ እንዳይገኝ የተደረገው፡፡ እነዚህ ደግሞ በሌላ ምክነያት የሚቀሩ ጥቂት ቢኖሩም አብዛኞቹ ይህን ጸረ-ሕዝብ አዋጅ እንደሚቃወሙ የተረጋገጡ አንደሚሁን እንገምታለን፡፡ አይን በአይን ጀግኖቹ የጣሉትን አዋጅ እኮ ነው አልፏል ብለው ሙጥኝ ያሉት፡፡ ወሮበላ ሥርዓት የት ያውቅና ነው ድሮስ፡፡ ብዙ ሊቃወሙ የሚችሉ ከስብሰባው እንዳይገቡ እንደታገዱ ነው አሁን የምናየው እውነት፡፡ መጀመሪያማ የሚቃሙንን በሙሉ አስቀርተናል ብለው አስበው ነበር እኮ በጭብጨባ እናሳልፈው ያሉት፡፡ ምን አልባትም ድንገት ሾልኮ የገባ ተቃዋሚ ከአለ ድምጹ እንዳይሰማ፡፡ አንበሶቹ ግን ገብተው ነበር፡፡ ጭብጨባ ሲል አጨብጫቢው አዳራሹ በአንበሶቹ ድምጽ ሲመላ አባ ዱላ ደንግጦ ነበር፡
አልጠበቀም ነበርና፡፡ ከዛም አይተናል እጁን አውጥቶ አንገቱን አዙሮ ሊውጡት የተዘጋጁትን ነብሮች ሲያይነበር ምድረ ወንበዴ፡፡ የወሮበላው ቡድን አንበሳ የወራዳ ወንበዴ አይን የሚፈራ መስሎት፡፡ እድሜ ለለማ ከአረመኔነት በቀር ወኔ የሌለው ተራ ወንበዴ እንደሆነ ለሕዝብ ይፋ አድርጎታል፡፡ ከአስታወሳችሁ የአዲስ አበባን አዋጅ ለመወያየት በሙል የተሰበሰቡ ጊዜ ነገሩን የለኮሰው የፓርላማው አባል ሳይሆን የኦሮሚያው ቃል አቀባ የለማ አጋር አዲሱ አረጋ ነበር፡፡ ወያኔ ስለአዲስ አበባ ለኦሮሞ አዋጅ ልታወጣለት!!! ይገርማል ይሄን ነበር እነ ኦነግ ምናም የሚሏቸው በሕገ-መንግስት እንዲገባ ያደረጉት፡፡ በዚህ የሴራ ሕግ ወያኔ ኦሮሞን ከአዲስ አበባና አካባቢዋ 25 አመት ስታጸዳ የኖረችበት ሳያንስ አሁንም ለኦሮሞ ቅድሚያ የሚል ኦሮሞን አዋጅ አውጥታ ልታጃጅል፡፡ ይገርማል፡፡ 27 ዓመት ይበቃናል፡፡ እነ ገብረየስ ቤኛን የመሳሰሉ ታላላቅ የኦሮሞ በለሀብቶች ከአዲስ አበባ አደለም ከአገር ሳይቀር አሰድዳ ዛሬ ምድረ ትግሬን አስፍራበታለች፡፡ ኦሮሞ ፍትህ እንጂ ጥቅማጥቅም አደለም የሚፈልገው፡፡ እንደማንኛው ሌለው ሕዝብ እኩል መብት እንጂ ልዩ ጥቀም አይፈልግም፡፡ ይህ ሆኖ በነጸነት ሲወዳደር በተለይ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ኦሮሞ ሆነ ጉራጌ የተሻለ ተጠቀሚ ይሂናሉ፡፡ እስከ ወያኔ ዘመን ድረስ ያለው እውነትም የሚያመለክተው ይሄንን ነበር፡፡ እነ ገብረየስ ቤና እኮ ለአዲስ አበባ ቅረበታቸው ነው ከምንም ተነስተው አለምን ያነቃነቀ ነጋዴ የሆኑት በወያኔ እስከ ሚከስሙ ድረስ፡፡ ዛሬ ጸረ-ሕዝብ አዋጁ የታወጀው በግልጽ ከወሮበሎች ተነጥቆ ለሕዝብ የተሰጠውን የአዲስ አበባና አካባቢዋ መሬት ለመውረር እንደሆነ እኮ ጀግናው ነገረን፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያ መሪዎቿን ከቀደሙት አባቶቻችን ልጆች እያገኘች ትመስላለች፡፡ ዛሬ አደለም የኦሮሚያ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ሊመራ የሚችል ፍልስፍና እየመጣ ያለው ለዘመናት በወያኔ ሴራ ታሪካቸው ከሕዝብ አእምሮ እንዲጠፋ የተደረገው የቀደምት አባቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን የለበሰ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን ጎንደር እስከ ሞያሌ ከጋመቤላ እሰከ በቢሌ በወጥነት እየተዜመለት ያለ ነው፡፡ ፍርሀት አያውቅም፡፡ አደረጃጀቱም ማንም እንቆቅልሽ ነው፡፡ ግን ለሕዝብ ግልጽ ነው፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር ሕዝብ መረራን በአምቦ ስቴዲየም ሲቀበል ያስደነገጣቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ የእነ ለማ ቡድን ግን ለዚህ ክስተት በቂ የደህንነትና ሌሎች ግብዓቶችን አሟልቶ ነበር ያስተናገደው፡፡ በቀለ ከእስር ሲለቀቅ የተቀበለችው የኦፕዲኦዋ የአዳማ ከንቲባ ነበረች፡፡ ከአዲስ አበባ ቤቱም በኦሮሚያ ፖሊስ ታጂቦ እንደ ልዩ መሪ ነበር የገበው እንጂ ወያኔ አሸባሪ እንዳለቸው አደለም፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እጅግ አየተቃጠሉ ያሉት ወያኔ ብቻ ሳትሆን ብዙ ሌሎች አጋሮቿ ነበሩ፡፡ ለማ መቼ በዚህ ብቻ አበቃ ወሮበላዋ ወያኔ በአገር ፕሬዘደንትነታቸው ሙሉ ጥቅማቸውን የአገሪቱ ሕግ የሚፈቅድላቸውን ዶ/ር ነጋሶን አዎ የዚህች አገር ፕሬዘዳንት ነህ ወሮበሎች የከለከሉህን መብት እኔ ሰጥቼሀለሁ ያሉ፡፡ ኧረ ስንት የማይታሰብ የማይደፈር ቁምነገር ነው ለማ የሰራው፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገ ጀግናን ዛሬ ተራ ሰዎች ፖለቲካ አልገባውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ ከአለማወቅ ከሆነ ችግር የለም ግን ሴራ እንደሆነ ነው የምንረዳው፡፡ አገሪቷን ወደሥርዓት የሚወስዳትን መንገድ ስለመረጠ እንጂ ለማ ብዙ ሊሰራው የሚችል አቅም አለው፡፡ በአጠቃላይ ዛሬ ለማ በኦሮሚያ አልፎም በአገሪቱ የፈጠረው መንፈስ ወያኔን ከአፈር እንደሚቀላቅላት እሷም አውቀዋለች፡፡ በትመከርም አልሰማም ብላለች እንግዲህ የማይቀረውን ልተጎነጭ ጊዜዋ ሩቅ አደለም፡፡
እስኪ ግን ከኦፌኮ በቀር ሌሎች ተቃዋሚ ተብዬዎች የት ገቡ፡፡ የሚገርመው ኦፌኮ የመድረክ አባል ነው፡፡ ዛሬ ያወጣውን መግለጫ ከመድረክ ጋር ሊያወጣው እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ምክነያቱ ደግሞ ኦፌኮን የሚመሩት መረራና በቀለን የመሰሉ ከአውነት ወደኃላ የማይሉ በመሆናቸው እንጂ አድርባዮች እንዲሀ ያለ መግለጫ ማውጣት አይፈልጉም፡፡ ለነገሩ እኮ መድረክ የወያኔ ባለስልጣናት የነበሩ እንደነ ገብሩ አስራትንም ያሉትን ጨምሮ ነው፡፡ አዋጁን በግልጽ እንቃወማለን ሕዝብ ትግሉን አንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን ሊል የሚቸል የሕዝብ አጋር መሪ የኦፌኮ መሪዎች ብቻ ሆነው አግኝተናል፡፡ያ ግንቦት ሰባትም አንዴ ከአገር ጠላት ከሆነው ኦጋዴን ነጻ አውጪ ሌላ ጊዜ ከሻቢያ እየተባበረ የኢትዮጵያን ሕዝብ እያስፈጀ እንደው ለይስሙለ እንኳን ትፍሽ አላለም፡፡ ሕዝቡን አዚም አድርጎበት ነው መሰለኝ ዛሬም ግንቦት 7 እያለ የሚጮኸውን ብዛት ሳይ ይገርመኛል፡፡ ህዝብ ከዳር እዳር ነቅሎ በባዶ እጁ ጠላቱን እየተፋለመ ከሻቢያ በኩል በሚመጣ ሌላ ወንበዴ ተስፋ የሚያደርግ ምን እንደሚባል አይገባኝም፡፡ ሰሞኑን ሌላ አስገራሚ ነገር የአማራ ደርጅት ነኝ ባይ ሌላው እዛው አስመራ ሄዶ ሻቢያ የሚባል ጣዖቱን ተሳልሞ ከጠንቋዩ ኢሳያስ ምርቃት ተቀብሎ እነደመጣ ስሰማ ምን ጉድ ነበር ያልኩት፡፡ በኋላ ስበው ስንት በአማራ በተባለው ህዝብ የሚነግድ ወያኔ እንዳለ ታወሰኝ፡፡ ክልሉን በሙሉ አማርኛ በሚናገሩ ትግሬ ወያኔዎች እየተመራ እያየን አንድ የሆነ ቡድን በአማራ ሥም አደራጅቶ ውዥንበር መፍጠር ኢምነት ነገር ነው፡፡ ለማንኛውመ ለጎንደሬዎች የምለው በሚቀጥለው እጩአችሁን በቀለን አድርጉ ነው፡፡ በቀለ ውድድር ቢኖር መወዳደር ያለበት ወለጋ ሳይሆን ጎንደር ነው፡፡ ጎንደር ጠንካራ ሕዝብ እንደሆነ ከሌሎች ሁሉ ለየት ብሎ ታይቷል ሆኖም የታወቀ መሪ የለውም፡፡ ደመቀ ዘውዱ የፖለቲካ ድርጅት እንዳላቸው አላውቀም፡፡ ይህን የምለው ለቀልድ አደለም እንዲሆን የምመኘውን ሀሳብ ማቅረቤ እንጂ፡፡
በማጠቃለየ መሪዎች ከኦሮሚያ እየወጡልን ነው፡፡ በሴረኞች እጅ ወድቆ የነበረው የኦሮሞ ፖለቲካ ዛሬ በጠቢባን እጅ ገብቷል፡፡ አሁንም እየተፍጨረጨሩ ያሉ አሉ፡፡ ሰሞኑን ስለ ዶ/ር አብይ ውዝግብ ነገር ብዝቷል፡፡ አብይ ለራሱ ሲል ጥሩ ይሁን እንጂ የእሱ መኖር አለመኖር የሚያመጣው ነገር የለም፡፡ ሕዝብና መሪዎች (አፌኮና ኦሕዴድ) አንድ ሆነዋል፡፡ የተነሱትም ለመንድር ፖለቲከኝነት ሳይሆን ኢትዮጵያን በሙሉ ነጸ ሊያወጣ በሚችል መንፈስ ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ነን፡፡ ሰራዊቱም ከእኛ ጋር እየቆመ ነው፡፡ መቼም መጥፊያዋ እነዳይሆን ሆኖ እንዲያልቅ እግዚአብሔር ስለወሰነ ወያኔን እንደፈርኦን አደንዝዟታል፡፡ የወያኔ ደጋፊዎችም እንደኖሕ ዘመን ሕዝብ ዛሬም እየታወቃቸው አደለም፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይታደግ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ
