https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1860474453986177&id=1712191348814489
የኤውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር እየሱስ ተወለደ ከተባለበት የቀደመ መሆኑን የቀድሞው የሮማ ጳጳስ በቅርቡ በመጽሐፋቸው አስፍረዋል። የኢትዮጵያ ካሌንደር ወደ ትክክለኛው ሳይቀርብ ኣልቀረም በማለት ዶክተር ኣበራ ሞላ አመስግነዋቸዋል።
እድሜና ጤና ለኢትዮጵያዊው ዶክተር አበራ ሞላ በአፍሪካ ጥንታዊና ብቸኛ የሆነውን የኢትዮጵያ ግእዝ ፊደል ከ30 አመት በፊት ወደ ኮምፒተር አስገብተው ከዚያም በዩኒኮድ እውቅና እንዲያገኝ አስደርገዋል። ለኢትዮጵያ ግእዝ ፊደላችን የባለቤትነት መብት /ፓቴንት/ ከማስገኘታቸው በተጨማሪ በእጅ ስልኮቻችን በፊደላችን እንድንፅፍ አስችለውናል። ፊደሉ 1/ የአፍሪካ ህብረት መገልገያ እንዲሆን መታጨቱን እንዲሁም
2/ በእስራኤል
3/ በጃማይካ
4/ በትሪንዳድ ቶባጎ መታጨቱን
5/ በአሜሪካ ዋሽንግቶን ዲሲና አንዳንድ ከተሞች ከ10 አመታት በፊት ጀምሮ በማገልገል ላይ ነው።
ዶክተር አብይ የኦሮሞ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ፊደላችን ኢትዮጵያዊያንንና ከፍ ብሎም አፍሪካውያንን በአለም ህዝቦች ሁሉ ፊት የሚያኮራን ታላቅ ውርስና ቅርስ ነው።
የግእዝ ፊደል ለሌሎች ቋንቋዎች ከመታጨቱ ጋር ኢትዮጵያውያን በሙሉ በፊደላችን በመጠቀም አንድነታችንን ለዓለም እናሳይ።
አብርሃም ቀጄላ ዋሽንግተን ዲ
