10/03/2018

ጨካኙና አረመኔዉ የወያኔ ጦር በኦሮሞ ሀዝብ ላይ የሚፈጽመዉን ፋሽስታዊ የግዲያ ኣድማሱን በማስፋት ዛሬ በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸመዉ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ በደቡባዊ የኦሮሚያ ክፍል ሞያሌ ዉስጥ በርካታ ዜጎች ላይ በተወስደ የጭካኔ አርምጃ በርካታ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ ብዙዎች ከፍተኛ የኣካል ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ተችሏል።
የሟቾች ቁጥር  እስካሁን የኣስራ ሶስት መድረሱ ሲታወቅ ከነዝያ መሃል ኣስከሬናቸዉ በሆስፒታል የሚገኘዉ የስምንት ስው ስም ይፋ ሆኗል
1.ተማም ነጌሶ የትምህርት ቤት ዳይረክቴር
2.ኤርሚያስ በዳኔ የሬስቶራንት ሰራተኛ
3.ካኑ ገሮ
4.ጎሎ
5.ሚሃመድ ኡርጌ
6.ካኑ ቃንጫሮ
7.መሃመድ ካምጴ
8.ታሪ ሻማ
ሲሆኑ ኣራት የሟቾች ኣስከሬን በወታደሮች ወደ ካምፕ ተወስዷል። ይህን በህዝብ ላይ የተፈጸመ ኣሳዛኝ ጨፍጨፋና የጉዳቱን መጠን እየተከታተልን እናቀርባለን።