ወደ ወገራና በለሳ የሔደው የሕወሓት ጦር በሽንፈት ተመልሷል፤
መጋቢት 01 ቀን 2010 ዓ.ም የሕወሓት ጦር የበለሳንና የወገራን ሕዝብ የጦር መሣሪያ ለመቀማት ተንቀሳቅሶ የነበረ ቢሆንም በእንቃሽ ገበሬዎች ጠንካራ መከላከል ዕቅዱ ከሽፎ ተመልሷል፡፡ በዚሁ ምክንያት በሰሜን ጎንደር ዞን የጎንደር ከተማን ጨምሮ ከሰዐት በኋላ እስከ እኩለ ሌሊት የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ ነበር፡፡ ከባድ መሣሪያን ጨምሮ በዘመናዊ ትጥቅ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጦር በወገራና በለሳ ገበሬዎች ድባቅ ተመቷል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ወረራ የፈጸመው የሕወሓት አገዛዝ መላ አገሪቱን የሽብር ቀጠና አድርጓታል፡፡
Source Muluken Tesfaw
