March 13, 2018
According to the report by the Amhara Mass Media Agency (AMMA), Bahir Dar University is conducting a curriculum design to start Oromiffa language teaching program.

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሮሞኛ ቋንቋን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ባህር ዳር፡ መጋቢት 3/2010 ዓ/ም(አብመድ) የዩኒቨርሲቲው የሂዩማንቲ ፋኩልቲ ዲን ዶክተር ዳዊት አሞኘ እንደተናገሩት የግዕዝ ቋንቋን ከጥንታዊቷ ኢትዩጵያ ታሪክ ጋር በማቀናጀት ማስተማር ለመጀመር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡
ከግዕዝ በተጨማሪ የኦሮምኛ ቋንቋን ለማስተማር የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና ሌሎች ጥናቶች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡
ፋኩልቲው ቲያትር እና ፊልም ለማስተማርም ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም ከፍቶ በአማርኛ ቋንቋ እድገት ላይ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው፡፡
