March 13, 2018
ሸንቁጥ አየለ
——————————
በዘመነ ጌጤ: በለገሰ ወልደ ሃና : በመቶ አለቃ ማሰረሻ ሰጠኝ : በአግባዉ ሰጠኝ እና በሌሎችም እስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለ ግፍ እየበረታ መጥቷል
—-——————————————–
በእነ ለገሰ ወ/ሀና : በእነ ዘመነ ጌጤ :መቶ አለቃ ማሰረሻ ሰጠኝ : አግባዉ ሰጠኝ እንዲሁም በሌሎችም እስረኞች ላይ የሚፈጸመዉ ኢሰበአዊ አያያዝ እንደበረታ መረጃዎች እየደረሱን ነዉ::
1ኛ; ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርብላቸው ምግብ ለጤና እጅግ አደገኛ እየሆነ ነዉ። ምግብ ብለው የሚያቀርቡላቸው ጭራሽ እህል ብሎ ለመጥራት የሚከብድ ከግማሽ በላይ አፈርና አሸዋ እንደሆነ ታዉቋል::ወያኔ እስረኞቹን በጤና ጉድለት መግደል የፈለገ ይመስላል::
2ኛ;የመጠጥ ውሀውም ከዚያው ከማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የጉድጒድ ውሀ አፈርና አሸዋ ብጥብጥ እንደሆነ ይታወቃል::ይባስ ብሎ ግን አሁን የዉሃዉ ንጽህና የተበከለ እየሆነ ነዉ::
3ኛ; እጅግ በርካታ ታሳሪዎች የሚረዳቸዉ እና የሚጠይቃቸዉ የለም:: ለወገን ሲታገሉ ቢታሰሩም የሚጠይቃቸዉ ወገን ግን ፈጽሞ የለም::ይሄም እጅግ አሳዛኙ ነገር እንደሆነ ከእስር ቤት የሚወጡት መረጃዎች ያሳያሉ::
4. ማረሚያ ቤቱ የጭካኔ ምግባሩን በስፋት የሚያከናዉንበት የእስር ቤት ማስፋፊያ እየሰራ ነዉ::: ስራው ደግሞ የሚሰራው በእስረኛ ጉልበት ነዉ::ይሄም እስረኞች በባዶ አንጀታቸዉ ለበለጠ በሽታ ተጋላጭ ሆነዋል:: በእጅጉ ጎድቷችዋል::
5. በርካታ እስረኞች በሚፈጸምባቸዉ ድብደባ እና ኢሰበአዊ አያያዝ ብዙ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል::ለምሳሌ ዮናስ ጋሻዉ በተፈፀመበት ድብደባ አካሉ ሸባ በመሆኑ በክራች እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል:: ፈረደ ክንድሽ እና አስቻለዉ ደሴም በተፈፀመባቸዉ ድብደባ ብልታቸዉ ተኮላሽቷል::
6. እስረኞች የእምነት መብታቸዉ እንኳን አይከበርላቸዉም:: እንደማሳያም አባ ገብረ ስላሴ የምልኩስና ልብሳቸዉን እንዳያጠልቁ ብዙ ድብደባ ተፈጽሞባቸዉ በከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ናቸዉ::
7. የሚከተሉት እስረኞችም እጅግ ከፍተኛ መከራ እና ስቃይ ዉስጥ መሆናቸዉን መረጃዎች ደርሰዉናል::
– አሸናፊ አካሉ
– ዉብ አንተ
– ፀጋየ(አማኑኤል)ዘለቀ
-ወረታዉ ከበደ
– አባ ገበረጊዉርጊስ
– አገናኝ ካሱ
– ታደሰ መሸሻ(
-ደረጀ በላይ
-አዱኛ ካሳየ
-ነጋ ዘላለም
-መሀመድ ሸፋዉ
-;ፍቅረማርያም አስማማዉ
-ቀለምወርቅ ዘላለም
-ጋሻዉ ሙሉየ
-ደሴ አንዳርጌ
-ነጋዉ ተገኝ
-ጌታነህ አባይ
– ደሳለኝ ካሴ
-ቄስ ደመቀ
-ደረጀ አብረሃም
-ጌታ አስራደ
-ነጋ የኔዉ
-ፈጠነ ገብርየ
-ኤልያስ አደም ሀጅ
-ነጋሸ መሀመድ
-ጥላሁን አበጀ

