ዋይ ዋይ አትበይ …የሀገሬ ባልቴት
ይልቅ ጨፍሪልን… አዉሬን ሲቀብሩት።

ይህች ምድር ብዙ አምባገነኖችን አስተናግዳለች። የደደቢት በርሃ የፈጠረቻቸዉን ባንዳ ህወኣትን ጨምሮ በርካታ የእንግዴ ልጅ ሊሆኑ የሚገቡ የፍጥረት ስህተቶችን ይህች ምድር ታዝባለች። ምነዉ ዉሃ ሆነሽ በቀረሽ ሊባሉ የሚገባቸዉን የሰዉ ልጅ አምሳያ ግን ግብረ ሳጥናኤላዊ የሰቆቃ ተዉሳኮችንም ታቅፋለች…..። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ የሌላዉ ሰላም ….. የሌላዉ ፍቅር…… የሌላዉ ሳቅ ……የሌላዉ ዉበት …. የሌላዉ ደስታ የሚያቃጥላቸዉና የማይዋጥላቸዉን ትናንሾች በየዘመናቱም …. በየቦታዉም አስተዉላለች ።
አርዮስ ተብለዉ የተወገዙና ለዘመናት በክፋታቸዉ ሲዘከሩ የሚዘልቁ ብዙ የበግ ለምድ የለበሱ የሰው ተኩላዎች የእልፍ አዕላፍ ንፁሐንን ሞት አዉጀዋል….. አሳዉጀዋል..…ፈፅመዋል …አስፈፅመዋል.። በኦሮሞ ….በአማራ…..በጉራጌ…. በጋምቤላ….. በአፋር…. በሶማሌና በሌላዉም ኢትዮጲያዊ ላይ የሞት ሳጥናኤላዊ ባንዲራ ይዞ ተሰይሞ ያለዉን የመለስ ዜናዊ ትግራያዊና ህወኣትዊ እኩይ ሰይፍ ጨምሮ በካምቦዲያ ፓል ፖት …..በቱርክ ፓሻ …….በሰሜን ኮርያ ኪም ሱንግ ………በቬተናም ኦቺ ሚን……..በፓኪስታን ያያ ካን…. እንዲሁም በጃፓን ቶጆ ሂዴኪ ለበርካታ ሚሊዮኖች ዜጎቻቸዉ በግፍ የመሰቃየትና የመሞት አሪዮሶች ሆነዉ አልፈዋል። ዛሬ መለስ ዜናዊን ጨምሮ የሁሉም ግብረ ሴጣኖች ስጋ አፈር ወስጥ አፈር ሆኖ ያለ ቢሆንም ዘለዓለማዊ ነፍሳቸዉ ግን የት እንዳሉ መገመት አይከብድም። ሁሉን ፈጥሮ መልካም ያለዉ አምላክ….በተለይም ለክብሩ መገለጫ በእራሱ ምስል የፈጠረዉን የሰዉ ልጅ እያሳደዱና እንደ ጭድ ዶጋመድ እያደረጉ የምድር ላይ ዘመናቸዉን ለሳጥናኤላዊ ምግባር ያዋሉትን ነፍሳት የክብር ቦታ ሰጥቶ ቅዱሳን ይላቸዋል ብለን አንጠብቅም። እርሱ በቃሉ “እኔ እንደ ወደድኃችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ የእኔ ትህዛዝ ይህቺ ናት። ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰዉ ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም።” ሲል ያሳሰበ አምላክ ለትግሬ የበላይነት በሚል ሳጥናኤላዊ የባቢሎንን የመለያየት ተምሳሌት ፈጥረዉ……የአህላፍ ኢትዮጲያዊያን ሕፃናት ወጣትና ጎልማሳ ሕይወት ያለጊዜው ይቋጭ ዘንድ ምክንያት የሆኑትን ህወኣትዊያንን ‘እሰይ የእኔ ደቀ መዘሙራን ትህዛዜን ፈፅማችኋልና ወደኔ ኑ!’ ሲል ያንቆለጳጵፀዉፃቸዉ ይሁን? መልሱን ፈጣሪ ያዉቃል።
አዎን!! እኛ ግን እናቶቻችንን እንላለን….
ዋይ ዋይ አትበይ ….የሀገሬ ባልቴት
ዋይ ዋይ አትበይ ….ኢትዮጲያዊ እናት
የሞተዉ ገዳይ ነዉ …የእንግዴ ልጅ …..ስህተት።

አቶ በረከት ስምኦን የሁለት ምርጫዎች ወግ በተሰኘዉ መፅሐፋቸዉ ላይ የጠቢብ ቀመር የመሰላቸዉን ግን ተራና ሳጥናኤላዊ አመለካከታቸዉን ሲገልፁ እንዲህ ብለዉ ፅፈዋል “የጭንቀት ክረምት ቢረዝምብን ወይም ቢያጥርልን የዚህ ሁሉ አድራጊ ፈጣሪ ኢኮኖሚዉ ነዉ። …..ኢኮነሚዉ ደልዳላ በሆነበት ማንም ስለፈለገ ብቻ ኢትዮጲያን ወደ ቀዉስ ሊመራት አይችልም” ገፅ 202።
የሰዉ ልጅ በሚበላና በሚጠጣ ብቻ አይኖርም የሚለዉን መንፈሳዊ አባባል ጨምሮ…. ሀብታምና ግመል ….. ወድቀህ ብትሰግድልኝ .. ዓለም ሁሉ ቢኖርህ ግን ፍቅር ከሌለህ…..የሚሉትን ለማብራራት መንፈሳዊ መሆንን ስለሚጠይቅ መተዉ ቢመረጥም በርካቶች ዓለማዊ ሊሂቃን ግን ተመሳሳዪን ብለዋልና የስህተቶች ቁንጮ የሆኑትን የአቶ በረከትን ተላላ ወይም መርዘኛ አባባል ማሳየቱ ይበጃል።። አዎን ሀብት ነፃነትን አይተካም። ዛሬ በሴይጣን ፈረሶች እንግልት ላይ ያሉት የዋልድባ መናንያን ለዚህ ምስክር ናቸዉ። አዎን!! ሀብት ነፃነት ወይም ሰላም አይደለም። ፈጣሪ ለፈጠራቸዉ አዳምና ሔዋን ሕይወት ይዘሩ ዘንድ የተነፈሰላቸዉ ፎቅ ወይም ቦቴ መኪና አይደለም፤ ይልቁንም ዘላለማዊ ነፍስን ነዉ። ስህተቶቹ እነ በረከትና አጋዚያን ግን አህላፍን በዘር ጥላቻና መክሊት ሰበብ ለሞትና ለስደት ዳርገዋል። የጥቁር አሜሪካዊያንና የመላዉ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ታጋይ የነበረዉ ሙሁሩ ዱ ቦይስ ጥቁሮች በሰሜን አሜሪካ በድህነትና በባርነት ተጨፍድደዉ ይኖሩበት በነበረበት ዘመን ሲፅፍ “ሁሉም የሰዉ ልጅ ነፃነት ይኖረዉ ዘንድ አምላክ እንደፈጠረዉ አምናለሁ…. ሁሉም የሰዉ ልጅ እጆቹንም መንፈሱንም እስከቻለዉ ድረስ የሚዘረጋበት ነፃነት ይኖረዉ ዘንድ አድርጎ ይኖር ዘንድ አምላክ እንደፈጠረዉ አምናለሁ…. የመተንፈስ ነፃነት …… አስተዳዳሪዉን የመምረጥ ነፃነት …….ጓደኞቹን የመምረጥ ነፃት….ነፃነት…” ብለዋል። በአንፃሩ እነ አቶ በረከት ግን የሁሉ አድራጊ ፈጣሪ ኢኮኖሚዉ ነዉ በማለት እያደነቆሩን ሁላችንንም በልቶ ጠጥቶ ብቻ እንደሚያድር የጋማ ከብት ያስቡናል ….ወይም እንድናስብ ይመኙልናል ። በእርግጥ እንደ ኃይሌ ገ/ስላሴና አባ ዱላ መሰሎች በመገኘታቸዉ ሕግዚሃብሔር በአምሳሌ ያለዉ ፍጡር ከብት ለመሆን መፍቀድ እንደሚችልም ታዝበናል።
ያም ሆነ ይህ ዛሬ ለዘመናት የገደሉን አርዮሳዊያን የቀብር ዋዜማ ነዉና አናነባም። የበደኖዉ….. የሞያሌዉ….. የወልድያዉ….. የአምቦዉ…. የባሕር ዳሩ….. የጎንደሩ የጋምቤላዉ ህልፍ አህላፍ ያለጊዜዉ የተቀጩ ነፍሳት ለዘመናት እየቆጨንና እየዘከርናቸዉ ብንኖርም ዛሬ ግን በእነሱ ቀብር ዋዜማ ላይ አናነባም!!…..
ስለዚህ የሞተዉ ገዳይ ነውና አታልቅሺ የሀገሬ ጉብል…….. የሞተዉ ዘረኛ የደደቢት እሪያ ነዉና አትዘን የሀገሬ ጎበዝ….
አዎን!!
ዋይ ዋይ አትበይ …የሀገሬ ጉብል
የሞተዉ ሌባ ነዉ …የሚዘርፍ የሚገድል።
ካልሰማሽ ጠይቂ ….ሞያሌ ትንገርሽ
ሟች ገዳይ መሆኑን ….አጋዚን ታስረዳሽ።
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!
