ለምለም ፀጋው

ለምለም ፀጋው

 

በዙፋን ተቀምጦ፣ አጃቪው በአደራሽ
ጠጁን እየጠጡ፣ ጮማ ሲቃመጡ፣
አፈ ሙዝ አንግተው፣
ማን አለብን ብለው እንጦጦ ላይ ወጡ።
ልጆቻቸው ሁሉ ኢሮፕ፣ አሜሪካ
ትምሀርትን በመቅሰም ሲንደላቀቁብን፤
እባክህ አዳምጠኝ ጋሻ ጃግሪ አተሁን።
ጭጭ ማለትም ይብቃ፤
ወንድምህ፣ እህትህ፣ በጥይት ሲወቃ።
አዕምሮህን ግዛው የምልህን አዳምጥ፤
ጊዜያዊ ለሆነው ለእንጀራ አትቋምጥ። አንተ እንደ መርዶክዮስ ሁን እኔም እንደ አስቴር ልሁን።
በኢትዮጵያ ምድር ሰባዊነትህ ሲጣስ፤
አትሁን እባክህ ፍሪ የለለው ገብስ።
የሚቀጥለውን ጥቅስ አንብበህ ተረዳ፣
-2-
ባንተ አልተጀመረም በሥጋዊ ምድር፤
የሰው ዘር ለማጥፍት
ጥረት መደረጉ አዋጅ በማስነገር። “መርዶክዮስም አክራትዮስን፦ ሂድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው። አንቺ፦ በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ። በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? አስቴርም እንዲህ ብሎ ለመርዶክዮስ እንዲመልስ አዘዘችው። ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፤ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ። መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር እንዳዘዘችው ሁሉ አደረገ።” [መጽሐፈ አስቴር 4:1317]
እስኪ ጎራ እንበል ወደ ኢትዮጵያ ምድር
ሞያሌን ተመልከት፣ ቤሻንጉልንም አስብ፣
ደግሞም እንዳትረሳ ወልቃይት ጠገዴን፤
ወልድያን በወሎ፣ ጎንደር አርማጭሆን።
ተው እናንተ “ታዛቦች” ከንቱ አታታልሉኝ፣
ቀለሙ ቀለሜ ቤመስል፣ እኔ ምን ቸገረኝ፤
እሱ ጮማ ሲቆርጥ በጥይት ከቆላኝ።
ታረቂ እያላችሁ ተው አታበሳጩኝ፣
ሰውነቴን ንቆ እንደ ከፍቶች ሲያርደኝ፤
ይልቅስ አደራ ወደ ፍርድ አምጡልኝ።
አዕምሮህን ግዛው የምልህን አዳምጥ፤
ጊዜያዊ ለሆነው ለእንጀራ አትቋምጥ።
-3-

አንተ እንደ መርዶክዮስ ሁን እኔም እንደ አስቴር ልሁን።
እንግዲህስ በቃ በኢትዮጵያ ምድር፤
ሐዝቧን አንከልልም በጎሣና “በዘር።”

© ለምለም ፀጋው የመንግሥትን ግድያና “የጸጥታ አዋጁን፣ February 17, 2018” በመቃወም የተጻፈ