
አቶ ታዬ ደንዳዓ
የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ህዝብ ግኑኘነት ሃላፊው አቶ ታዬ ደንዳዓ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ ታዬ ዛሬ ጠዋት አዲሱ ገብያ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ሥራ ቦታቸው ሲያቀኑ ነው በታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተወሰዱት።
አቶ ታዬ በቅርቡ ‘በሞያሌ ከተማ የተፈጸመው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም‘ ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን አስተያየታቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።
የአቶ ታዬ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ባለቤታቸው መታሰራቸውን እንጂ የት እንደሚኙ እንደማያውቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለመታሰራቸው የቀረበ ምክንያት ባይኖርም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ መመሪያ መሰረት ከኮማንድ ፖስቱ ውጭ በፀጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት አይችልም። ሆኖም አቶ ታዬ ‘የሞያሌው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም‘ ማለታቸውን ተከትሎ ሳይታሰሩ እንደማይቀር በርካቶች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ ታዬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳሉም ለበርካታ ጊዜያት ለእስር ተዳርጓል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ 16 ዓመታት አስፈልጓቸውም ነበር።
አቶ ታዬ ከጥቂት ወራት በፊት ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እዚህ ጋር ይመልከቱ።
